ከፊት ለፊት አቶ ልደቱ እንደሚመሩት የሚታወቀው የአብሮነት ኢትዮዽያ ሃያ አንድ አባላት ያሉት ቦርድ እንደሚያቋቁም ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። ቦርዱ ቃዳሜ ባደረገው የመጀመሪያው ስብሰባ ላይ አቶ ልደቱ በቀጣይ የሚመረጡት ሰባት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ማንነት ይፋ እንደማይገለጽ ማስታወቃቸው ተሰምቷል። ይህ የሚሆነው ምን አልባትም አቶ ጃዋርን ጨምሮ የኦሮሚያ ተወላጆች ከህብረቱ በመውጣታቸው ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተመልክቷል።
አቶ ታምራት ላይኔ የተካተቱበት ቦርድ ባደረገው ስብሰባ እንደታየው የብሄር ስብጥር ያለው ቢመስልም፣ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑና ህብረቱ ሲጠነሰ ጀምሮ አብረው የነበሩ በስተመጨረሻ ራሳቸውን አግልለዋል።
አቶ ጃዋር፣ ዶ/ር ሚልኬሳ፣ ዶ/ር ኢታና፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ የመሳሰሉት የኦሮሞ ፖለቲከኞች ከአብሮነት ራሳቸውን ያገለሉበትን ምክንያት ባያስታውቁም፣ አካሄዱን የማይደግፉ የኦሮሞ ተወላጆች ከውጭና ከአገር ቤት ባስደሩባቸው ጫና እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ አስታውቀዋል።
በቦርዱ ስብሰባ ላይ እንደሚገኙ በስም ተገልጸው የነበሩት ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ስብሰባው እንደተጀመረ በጽሁፍ መልዕክት አውሮፕላን ማሳፈሪያ አካባቢ በመሆናቸው እንደማይችሉ፣ ሲመቻቸው እንደሚገቡ ማስታወቃቸውን አቶ ልደቱ አስታውቀው ነበር። የሶማሌው ተወካይ ሆነው የቀረቡት ፈይሰል ሮበሌ ኬንያ ሆነው የዙም ስብሰባውን እየተሳተፉ እንዳስታወቁት ኬንያ የተለያዩ ታላላቅ ስብሰባዎች ስላላቸው ሶስት ሳምንት እንደሚቆዩ ጠቅሰርው ፕሮፌሰር ሕዝቅኤልም በቅርቡ ይመጣል ብለዋል። ይህ ንግግራቸው ሕዝቅኤል በሶማሌ ያለውን እንቅስቃሴ እንደሚመሩ በሻዕቢያ የመወከላቸውን ዜና የሚያጠናክር ሆኗል።
ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል በግብጽ በጀት በምስራቅ ኢትዮጵያ ጦርነቱን ለመለጠጥ የተያዘውን ዕቅድ የሚያስፈጽሙ መሆናቸውን፣ ለዚሁ ስራ ሞቃዲሾና ቱርክ በተደጋጋሚ ሲመላለሱ እንደነበር ገልጸን መዘገባችን ይታወሳል። አብሮነት ሰላማዊ ትግልን የሚያበረታታና የሚከተል ተቋም እንደሆነ ቢገልጽም በዚህ መልኩ የሚነቀሳቀሱ የተካተቱበት መሆኑ ከሚታማበት ጉዳዮች መካከል ግንባር ቀደሙ ነው።
አብሮነት ሃያ አንድ ቦርድ አባላትን ከመሰረተ በሁዋላ ባደረገው በዚሁ ስብሰባ እንደተመለከተው በቀታይ ሳምንት በሚደረግ ስብሰባ ሰባት አባላት ያሉት ስራ አስፈጻሚ ይሰይማል።
በዚህ ስብሰባ የሚመረጡት ሰባት ሰዎች በይፋ የሚገለጹ እንደማይሆን አቶ ልደቱ አስታውቀዋል። አቶ ልደቱ እንዳሉት ሰባቱ የስራ አስፈጻሚ አባላት ማንነት በሚስጢር ይይያዛል።
በስብሰባው የተገኙ እንዳሉት ምርጫ ካለ የሚመረጡ ይታወቃል። የሚታወቁ ከሆነ እንዴት ሰዎቹ ሚስጢር ሊሆኑ እንደሚችሉ አይገባቸውም። ሚስጢር እንዲሆን የተፈለገበትም አግባብ እንዳልገባቸው አክለዋል።
በመጪው ስብሰባ በመተዳደሪያ ሀገ ደንቡ ላይ አስቀድሞ መዘጋጀት እንዲቻል ረቂቁ ቀድሞ እንደሚበተን ታውቋል። ውይይት ተደርጎበትም ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በሲያትሉ የኦሮሞ ተወላጆች ሕብረት ምስረታ ላይ ከተገኙት መካከል አክራሪ አቋም ያላቸው፣ ኢትዮጵያን ቅኝ ገዢ አድርገው የሚያስቡ ወዲያው ህብረቱን መሰናበታቸውን ጠቅሰርን ሪፖርት ማቅረባችን አይዘነጋም። ለዘብተኛ የተባሉት ወደ አብሮነት ቢያመሩም፣ በስተመጨረሻ አካሄዱ “ኦሮሞን ከቤተመንግስት እናስወጣ” የሚሉ ሃይሎችና ከሻዕቢያና ወያኔ ጋር የሚሰሩ በህብረቱ ውስጥ ዋና ተዋኛን በመሆናቸው የኦሮሞ ተወላጆች ራሳቸውን ለማግለል እንደቻሉ ታውቋል።
በኢትዮጵያ አንድ ፓርቲ ወይም አደረጃጀት ለሁለት ተፍሎ አንዱ ሰላማዊ፣ ሌላኛው የትጥቅ ትግል አራማጅ መሆን የተለመደ መሆኑ የተለያዩ ድርጅቶችን ስም በመጥቀስ ተናበው እንደሚሰሩ ያመለከቱ አብሮነትም ከዚያ የተለየ ሚና እንደሌለው ይገልጻሉ። አብሮነት በበኩሉ ኢትዮጵያን አሁን ካለችበት ቀውስ ለማውጣት እንደሚሰራ ይናገራል።

