ለግማሽ ክፍለ ዘመን ራሱን በተገንጣይነት የሚጠራው ትህነግ፣ ያደራጀው ተዋጊ ኃይል ጦርነትን በመቃወም እየኮበለለ መሆኑ ተሰማ። ኃይሉ እየተናደበት ያለው ትህነግ የቤት ለቤት አሰሳ እያካሄደ መሆኑም ተሰምቷል።
ትህነግ ለሁለት ሲከፈል ጥለውት ከወጡትና በተለዩት የቀድሞ ፓርቲያቸው ውስጥ ስለሚከናወነው ሁሉ በቂ መረጃ እንደሚያገኙ ካስታወቁ ክፍሎች፣ እንዲሁም የትህነግን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ከሚከታተሉ አግባብ ያላቸው አካላት መረጃ ያሰባሰቡ እንዳሉት ተዋጊዎቹ ኩብለላ የመረጡት ለውጊያ የሚደረገውን ዝግጅት በመቃወም ነው።
ትህነግ የትግራይን ሕዝብ በጅምላ ከጨፈጨፈ፣ ከዘረፈ፣ ከደፈረና ካወደመው ሻዕቢያ ጋር የጀመረውን አዲስ ግንኙነት በመቃወም፣ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ላይ ጠብ መንጃ በማንሳት እንዲፈርስ መደረጉን ተከትሎ በተፈጠረው ልዩነት ሳቢያ ሃራ መሬት የወጡ መኖራቸው የሚታወስ ነው።
በእነ ዶክተር ደብረጽዮን የሚመራው ትህነግ ዳግም ወደ ስልጣን ለመመለስ በሚል የጊዚያዊ አስተዳደሩን በጠብመንጃ ካስወገደ በሁዋላ በትግራይ የተለያዩ ዞኖች ሕዝብ ቅሬታ ማሰማቱ፣ ቅሬታቸውን ባሰሙ ነዋሪዎች ላይ ከግድያ ጀምሮ የተለያዩ እርምጃዎች መወሰዳቸው አይዘነጋም። በዚህም ሳቦያ በታጣቂዎቹና አመራሮቻቸው መካከል መከፋፈል መፈጠሩን ከትግራይ የሚወጡ መረጃዎች ያስረዳሉ።
ይህ ሁሉ ከሆነ በሁዋላ ከትግራይ የትህነግ ጽህፈት ቤት በተገኘር መረጃ እንደተረጋገጠው፣ ከተለያዩ የአርሚ ምድቦች የኮበለሉት ታጣቂዎች ብዛት ታውቋል። በዚሁ መሰረተ አርሚ 24፣ 26 እና 43 የከዱ ሃይሎች ዝርዝር በአሃዝ ይፋ ሆኗል።
ከአርሚ 24 ኮር 241 ከሚሰኘው ምድብ በጠቅላላ ከነበሩት አባላት 1149 አባላት ወስጥ 538 ሲኮበልሉ 611 አባላቱ ብቻ ቀርተዋል።
ከኮር 242 በጠቅላላ ከነበሩት 1256 አባላቱ መካለ 621 ጠፍተዋል። 635 የሚሆኑት ቀርተዋል። ከኮር 243 አጠቃላይ 1214 አባላት መካከል 572 ሲኮበልሉ፣ የቀሩ አባላቱ 642 እንደሆኑ ታውቋል።
የአርሚ 24 በጠቅላላ 297 ስታፍ የነበሩት ሲሆን 21 አባላት ከምድብ ስራቸው ጠፍተው በአሁኑ ሰዓት 276 አባላት በስራ ላይ ሲገኙ ከነበሩት 196 የሜካናይዝድ አባላት ውስጥ 19 ጠፍተው በስራ ላይ 177 አባላት መሆናቸውን መረጃው ያስረዳል።
አርሚ 26 ኮር 261 ጠቅላላ አባላት 907 የነበሩ ሲሆን፣ 302 ከድተዋል። 605 ቀርተዋል። ኮር 262 ከነበሩት 930 ታጣቂዎች ውስጥ 392 ሲጠፉ 538 ቀርተዋል።
ኮር 263 የነበሩት ጠቅላላ አባላቱ 888 የነበረ ሲሆን 285 የሚሆኑት ኮብልለዋል የቀሩ አባላት ደግሞ 603 ብቻ መሆናቸው ታውቋል።
አርሚ 26 በጠቅላላ 126 ስታፍ የነበሩት ሲሆን 29 አባላት ከምድብ ስራቸው ጠፍተው በአሁኑ ሰዓት 97 አባላት በስራ ላይ ሲገኙ ከነበሩት 278 የሜካናይዝድ አባላት ውስጥ 34 ጠፍተው በስራ ላይ 244 አባላት ይገኛሉ።
አርሚ 43 ከኮር 431 ጠቅላላ አባቱ 1196 ሲሆን። 311 ጠፈትዋል። 865 መቀረታቸው ታውቋል። ከኮር 432 ጠቅላላ አባላት ማለትም ከ1233 ውስጥ 402 ሲከዱ፣ 831 ቀርተዋል። 1119 አባላትን ከነበሩት ኮር 433 ውስጥ 309 በመክዳታቸው 810 ብቻ እንደቀሩ መረጃው ያስረዳል።
አርሚ 43 በጠቅላላ 285 ስታፍ የነበሩት ሲሆን ዘጠኝ አባላት ከምድብ ስራቸው ጠፍተው በአሁኑ ሰዓት 276 አባላት በስራ ላይ ሲገኙ ከነበሩት 126 የሜካናይዝድ አባላት ውስጥ 12 ጠፍተው በስራ ላይ 124 አባላት ናቸው።
የትህነኝ ጽህፈት ቤት መረጃ ዋቢ አድርገው ሚስጥሩን ያጋሩት ክፍሎች እንዳሉት ትህነግ በአሁኑ ሰዓት ያለው ተተኳሽና ጥቅል መሳሪያ ዝርዝር መረጃ ታውቋል። መረጃውን ያሰራጩት ይፋ ባያደርጉትም የትህነግ አመራሮች እጅግ ታማኝ በሚሏቸው አማካይነት የቤት ለበኤት ብርበራ ማካሄድ ጀመረዋል።
በአብዛኛው ሓራ መሬት ሰፍትረዋል የተባሉትን የትግራይ የሰላም ኃይሎች እንደተቀላቀሉ ለማወቅ ተችሏል።
ሰሞኑን በወልደያ አካባቢ ዒላማውን እንዳልመታ በተነገርለት ጦርነት የሻዕቢያና የትህነግ ኃይሎች ከፋኖ ጋር ግንባር ፈጥረው መሰላፋቸው በማስረጃ በተገለጸ ማግስት ይፋ የሆነው ይህ መረጃ ትህነግ ወደ ጦርነት ለመግባት ፍላስጎት ቢኖረውም መሬት ላይ ያለው ዕውነታ እንደማይፈቅድለት አመላካች እንደሆነ አመላካች ተደርጎ ተወስዷል።

