Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  በመካነ ሰላም መስጂድ ታጣቂዎች ሰላት ላይ የነበሩ ሰላማዊ ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ረሸኑዋቸው
News

በመካነ ሰላም መስጂድ ታጣቂዎች ሰላት ላይ የነበሩ ሰላማዊ ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ረሸኑዋቸው

Ethioreview newsEthioreview news—October 4, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ በስምና በድርጅት መለያቸው የሚታወቁ ታጣቂዎች መስጂድ ውስጥ በመግባት ጭፍጨፋ መፈጸማቸውን ነዋሪዎችና በስፍራው የነበሩ እማኞች አስታውቀዋል። ድርጊቱ የተፈጸመው በግልጽ ሆኖ ሳለ ለወትሮ መሰል ዜናዎችን የሚሰሩ የጀርመን ድምጽና ቢቢሲ አለመዘገባቸው ቅሬታን ፈጥሯል።

መስከረም 23፣2018 ዓ.ም በመስጂድ ኑር በኢሻ ሰላት ወቅት ወደ መስጂድ የታጠቁ ኃይሎች በመግባት ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን ወይም የሶላት ስርዓት እየፈጸሙ ባሉ ንጹሃን ላይ ገድያ መፈጸሙን በርካታ ዜጎች በማህበራዊ ገጾቻቸው ይፋ አድርገዋል። ግድያው በተጠቀሰው ቀንና ስፍራ መፈጸሙን ያስተባበለ አካል ስለመኖሩ አልተደመጠም።

በአማራ ክልል በተለያዩ ጊዜያት ሙስሊም ዜጎች ላይ የተፈጸመውና እየተፈጸመ ያለው ግድያና በደል “በዛ” በሚል የአሁኑን ድርጊት በማውገዝ በርካታ የዕምነቱ ተከታዮችና ፍትህ ወዳድ ዜጎች ተቃውመዋል። ድርጊቱን ፈጸሙ የተባሉት ታጣቂዎች በምን ምክንያት በጅምላ እርምጃ እንደወሰዱ፣ የሶላት ሰዓትን እንደመረጡና የተጠቀስወን መስጂድ ዒላማ እንዳደረጉ ይህ እስከታተመ ድረስ የተባለ ነገር የለም።

በኢትዮጵያ እያደፈጡ የዕምነት አባቶችን፣ ምዕመኖችን፣ ቤተሰቦቻቸውንና በዙሪያቸው ያሉትን ማፈን፣ መግደል፣ ማገትና ገንዘብ መቀበል፣ ገዳማትን ማጥቃት ትርጉሙ በግልጽ ያልተቀመጠ ተደጋጋሚ ወንጀል ከሆነ ሰንብቷል። ከሁሉም በላይ ተመሳሳይ ወንጀል በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጽሙትና ተበዳዮች በምስክርነት ማንነታቸው ጠቅሰው የሚወነጅሏቸው አደረጃጀቶች ስለሚፈጽሙት ወንጀል ኃላፊነት አይወዱም። በዚህም ሳቢያ የዜጎች እልቂት ተራ ጉዳይ እየሆነም ነው።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ሃማስ፣ ሂዝቦላ፣አልቃይዳ፣ ቦኮሃራም፣ የሃውቲ ተዋጊዎች፣ አይሲሲ ወዘተ ጥቃት ሲፈጽሙ ኃላፊነት በመውሰድ ድርጊቱን የፈጸሙበትን ዋና ምክንያት ይፋ እንደሚያደርጉት ሁሉ፣ በኢትዮጵያ የሚታወቁ ታጣቂዎች እገታ፣ ግድያ፣ አፈና፣ ወዘተ ሲፈጽሙ ምንም እንዳልተፈጠረ ዝምታን መምረጣቸው ስጋቱን ያገነዋል። ከምንም በላይ እነዚህን የሚታወቁ ታጣቂዎች የሚደግፉ፣ የሚመሩና በውጭና በአገር ውስጥ ሆነው የሚያደራጁ በድጋፍም ሆነ በውግዘት ምንም ሲሉ አለመደመጣቸው ሌላው ጉዳዩን ውስብስብ የሚያደርገው ቁልፍ ጉዳይ እንደሆነ በርካቶች በተደጋጋሚ አስተያየት የሚሰጡበትና መስልስ የማይገኝለት አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል።

እንደውም በተቃራኒ የሰለባዎች ቤተሰቦች፣ ከግድያና አፈና ያተረፉ ምስክሮች ስም ጠርተው በሲቃ ድምጽ ወንጀሉን የፈጸሙትን ሲያጋልጡ ማስተባበያ በመስራት ወንጀሉን ወደ ሌላ ወገን የማስተላለፍ ልምድ በዝቶ ይታያል። በዚህ አግባብ ቪኦኤ በዋናነት የሚጠቀስ ሲሆን ቢቢሲም ስላታዊ ሪፖርት በማቅረብ በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲቀርበበት እንደነበር ይታወሳል።

ዛሬም ይህ እስከታተመ ድረስ ቢቢሲና ጀርመን ድምጽ ይህን ግፍ እያወቁ አለመዘገባቸው በስፍራው የነበሩትን፣ በጥቅል ሙስሊም ዜጎችን እንዲሁም ፍትህ ወዳዶችን አነጋግሯል። የኢትዮሪቪው የአዲስ አበባ ዘጋቢ በዚህ ጉዳይ ተገርመው ሲነጋገሩ የነበሩትን ጠይቆ “እስኪ አድረን እናያለን” በማለት ትዝብታቸውን አጋርተውታል።

ምስክሮች እንዳሉት ታጣቂዎቹ (በስም ይታወቃሉ) በመስጂዱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ገብተው የፈጸሙት ግድያ እጅግ ሰብአዊነት የጎደለው ሲሆን፣ በአንድ አገር ዜጎች ላይ በራስ ወገን ይፈጸማል ተበሎ የሚታሰብ እንዳልሆነ አመልክተዋል። ለጥንቃቄ ሲባል ከመጻፍ ተቆጥበን እንጂ ድርጊቱ ዘግናኝ ነው። ለዚህ ነው ምክር ቤቱ ” …. የሃይማኖት ተቋማት እና መሪዎች ድርጊቱ አብሮ የመኖርን እሴት የሚሸረሽር በመሆኑ እንዲያወግዙና እንዲቃወሙ የሚመለከታቸው አካላትም ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ አሳስባለሁ” ሲል ጥሪውን ያሰማው። ከስፍራው እንደተሰማው ከሆነ ድርጊቱ ከተፈጸመ በሁዋላ መከላከያ አካባቢው በመድረስ የማረጋጋትና የአሰሳ ስራ እየሰራ መሆኑ ታውቋል።

ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ!

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ መስከረም 23፣2018 ዓ.ል በመስጂድ ኑር በኢሻ ሰላት ወቅት ወደ መስጂድ የታጠቁ ኃይሎች በመግባት ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን በመወጣት ላይ በነበሩ ፦

ፎቶ – ከተገደሉት መካከል በከፊል

1 የመስጂድ ዋና ኢማምና የወረዳው መጅሊስ ም/ሰብሳቢ
2 የመስጂድ አመራሮች
3 የመስጂድ ኻዲሞችን አሰቃቂ እና አረመኔያዊ በሆነ ሁኔታ መግደላቸውን የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አረጋግጦልናል።

እነሱም ሸሂድ ሆነዋል አላህ ጀነተል ፍርዶስ ይወፍቃቸው ።

ጠቅላይ ምክርቤቱ የእምነት ተቋማት የተከበሩ ቦታዎች በመሆናቸው ሊጠበቁ እንጅ እንዲህ አይነት አፀያፊ ተግባር የሚፈፀምባቸው መሆን የለባቸውምና ድርጊቱን በፅኑ ያወግዛል።

መላው የሃይማኖት ተቋማትም በእምነት ቦታዎች የሚደረጉ ትንኮሳዎች እና በእምነት ተከታዮች ላይ የተቃጣ መሰል የጅምላ ግድያ ሊያወግዙና ሊያስቆሙ ይገባል።

ህዝበ ሙስሊሙ ይህንን በሀይማኖት ተቋማት ላይ የተቃጣ አደጋ ለመከላከል መረጃ በመለዋወጥ የሃይማኖት ተቋማትንና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጠቅላይ ምክርቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ብዝሃ ሀይማኖት ባለባት ሀገራችን በተለያየ እምነት ውስጥ ያሉ ህዝቦች ለዘመናት ያቆዩተን ሰላማዊ እና መልካም መስተጋብር ሆን ተብሎ ለመናድና ማባሪያ ያጣ ቀውስ ውስጥ እንድንገባ የሚፈልጉ አካላት የፈፀሙት መሆኑን ጠቅላይ ምክር ቤቱ ይገነዘባል።

በመጨረሻም ሁሉም ሃይማኖት ተቋማትና መሪዎች ይህ ጉዳይ አብሮ የመኖር እሴት እንዳይሸረሽር ብሎም እንዳያጠፋ ድርጊቱን እንድታወግዙ እንዲሁም በፅኑ እንድትቃወሙ እየጠየቅን መንግስትም ይህንን ተግባር በእምነት ቦታዎችና አባቶች ላይ የፈፀሙት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን።

መስከረም 24 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ኦሮሞ ‘ፈጣሪ ጥቁር ነው’ ይላል” የዋቄፈና እምነት
የሦስት ሊቃውንት የአሻራ ቅብብሎሽ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2