Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ኤርትራን ትህነግ የኢትዮጵያ መንግስትን ማስጠንቀቂያና አቤቱታ በጋራ አስተባበሉ
News

ኤርትራን ትህነግ የኢትዮጵያ መንግስትን ማስጠንቀቂያና አቤቱታ በጋራ አስተባበሉ

Ethioreview newsEthioreview news—October 11, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን መንግስትና ትህነግ በጋራ ጦርነት ሊከፍቱ መሆኑን ማስረጃ ዘርዝሮ ላቀረበው ክስ ሁለቱም ምላሽ ሰጥተዋል። በተለይም ትህነግ ሰሞኑን “የትግራይ ሕዝብ ኮንፍረንስ ” ሲል በጠራው ስብሰባ ላይ በግልጽ ከተነገረውና በይፋ ከተገለጸው አቋሙ ጋር የሚጣረስ ምላሽ ነው የሰጠው።

በዚሁ ትህነግ ባዘጋጀውና በመራው ኮንፍራንስ ላይ ከኤርትራ በቂ መሳሪያ ማግኘታቸውን፣ አብረው እንደሚሰሩ፣ ከፋኖ ጋር ወልቃይትን ዳግም ለመውሰድ መስማማታቸውንማ አንብረው እንደሚሰሩ፣ ይፋ ማድረጋቸውን ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

ሰሞኑን በወልደያ መግቢያ በሮችና በዚያው አካባቢ በተከፈተ ድንገተኛ ጦርነትና ከሕዝብ ጋር አብሮ በሚኖር አንድ የመከላከያ አሃዝ ላይ ጥቃት መሰነዘሩን ተከትሎ የፋኖ ደጋፊ ሚዲያዎች፣ የትህነግና የሻዕቢያ ሚዲያዎች ዜናውን በሰበር ሲያውጁ፣ ወልደያና አካባቢው በፋኖ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሲያስታውቁ ጦርነቱን ትህነግ፣ ሻዕቢያና ፋኖ በጋራ ማካሄዳቸውን ይፋ አድርገው ነበር። አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉ ውጊያዎችን በተመሳሳይ በጋራ እያካሄዱ መሂናቸውን ደጋፊዎቻቸው እየዘገቡ ነው።

በዚሁ “የትግራይ ህዝብ ብሔራዊ ኮንፍረንስ” በተሰኘው መድረክ፣ ሶስት ሺሕ የሚሆኑ ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የተወከሉ የትህነግ አባላት፣ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች፣ ወታደራዊ መሪዎችና ሌሎች አካላት መሳተፋቸው በድርጅቱ መግለጫ ተመልክቷል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

በኮንፍረምሱ ለኤርትራ ሕዝብ በሚል ተላለፈ በተባለው ስልታዊ ጥሪ “በአፍሪካ ቀንድ አንዣቦ ያለው ጦርነት ለማስቀረት” በጋራ እንስራ ጥያቄ በገሃድ ቀርቧል።

ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ቴሌቪዝን ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ከፕሪቶሪያው ስምምነት ጎን ለጎን በዶክተር ደብረጽዮን የሚመሩት የትህነግ አንድ ፍንካች ከኤርትራ ጋር ይፋዊ ግንኙነት ጀምሮ እንደነበር አስታውቀዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ የክልሉ ጊዜያዊ መሪ በነበሩበት ወቅት ትህነግና ሻዕቢያ ግንኙነት መጀመራቸውን በመቃወም፣ የሻዕቢያ ወታደሮች የኢትዮጵያን ግዛት አስፍተው መያዛቸውና መኮንኖቻቸው ከትግራይ ታጣቂ አመራሮች ጋር በይፋ እዛና እዚህ እየተመላለሱ አብረው መስራት መጀመራቸውን መግለጻቸው አይዘነጋም።

ራስይን የትግራይ ሰላም ኃይል የሚለውና በሐራ መሬት የሰፈረው አፈንጋጭ ታጣቂ ኃይል የልዩነቱ መነሻ የትግራይን ሕዝብ ያረደው፣ በጅምላ የጨፈጨፈ፣ የደፈረና የዘረፈ፣ ትግራይን ያወደመና ፋብሪካዎችን ነቅሎ ካጋዘ ወንጀለኛ ቡድን ጋር የተጀመረውን ግንኙነት በመቃወም እንደሆነ አመራሮቹ ለቢቢሲ ማስታወቃቸው ይታወሳል። በሻዕቢያ ትዕዛዝ በወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲፈርስ መደረጉ የልዩነቱ ሌላው ነጥብ ነው።

ይህንና መስል ጉዳዮችን ያላካተተው የትግራይ ኮንፍረንስ መጨረሻ ላይ የወጣው መግለጫ “በትግራይና ኤርትራ ህዝብ አንዣቦ ያለው እና የአፍሪካ ቀንድን ከመጥፎ ወደ ከፋ ችግር ሊያስገባ የሚችል የጦርነት አደጋ በሩቁ ለማስቀረት የሚቻለን እንደምናደርግ ስናረጋግጥ በእናንተ በኩልም ጮክ ብላችሁ ድምፃችሁን በማሰማት ሚናችሁ እንድትወጡ እንዲሁም ለሰላም አብረን እንድንሰራ ጥሪያችን እናቀርባለን” ይላል። ይህን ለሕዝብ ቀረበ የተባለ ጥሪ። ጻድቃን ይህን መሰሉን ስልት ” ማጭበርበሪያ” ሲሉ የትግራይን ሕዝብ ፍላጎት በማስታወቅ ሰሞኑን አስረድተዋል።

በዚሁ መግለጫ “አደገኛ የጦርነት ደመና አንዣቦ” ይገኛል እንደተባለና ለዚህም በተለይ የአሜሪካ መንግስት፣ አፍሪካ ሕብረት እና ሌሎች አካላት ለወቅታዊ ፖለቲካዊ ችግር ትኩረት እንዲሰጡ የጠየቀው ትህነግ፣ በመግለጫው ላይ በይጠቅሰውም ወልቃይትን ለርመውረር ከፋኖ ጋር መስማምቱን ማስታወቁ የጦርነት ስጋት አባባሽ ስለመሆኑ ያለው ነገር የለም።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ በምርጫ ቦርድ ህጋዊ ሰነቱ የተገሰሰውን ድርጅታቸውን አስመልክቶ ትህነግ ላይ ያነጣጠሩ ያሏቸው ጥቃቶች አውግዘው፣ ትህነግ ሊድን ወይም ሊጠፋ የሚችለው በውስጡና በአባላቱ መሆኑን ሲናገሩ መሳሪያና ድጋፍ ከኤርትራ ማግኘታቸውን በኮንፍረንሱ ላይ ማስታወቃቸውን በረካታ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

በዚህ መልክ ከትግራይ የጦርነት ዝግጅት መኖሩን፣ የወታደሮች ምልመላና ስልጠና በስፋት መካሄዱን፣ የሰራዊት ደሞዝ ለመጨመር ዕቅድ መያዙ፣ የኤርትራ መኮንኖች በይፋ መቅለ ማዘዣ ጣቢያ መስርተው እየሰሩ መሆኑ በስፋት ሲገለጽ መንግስት ዝም ማለቱ የተቃዋሚ የትግራይ ፓርቲዎች፣ የትህነግ ስንጣቂ የሆኑት አካላት ቅሬታ ሲያሰሙ መቆየታቸው አይዘነጋም።

በስተመጨረሻ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተባበሩት መንግስት ድርጅት ስጋቱን ገልጾ፣ ትዕግስቱ መሟጠጡን ምክኛት ያላቸውን ዘርዝሮ ለተመድ ካስታወቀ በሁዋላ ትህነግ ባሰራጨው የምላሽ ደብዳቤ፣ ክሱን ከዕውነት የራቀ ነው ሲል አስተባብሏል። ትህነግ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ እና ሌሎች አካላት ካሰራጨው የምላሽ ደብዳቤ ጎን ለጎን ኤርትራም የቀደም ግዛት የማስመለስ የጦርነት አዋጅ ስትል የኢትዮጵያን መግለጫ አስተባብላለች።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ የፃፈው እና የኤርትራ መንግስት እና ትህነግን የሚከሰው ደብዳቤ ተከትሎ ሁለቱም አካላት በረድፍ ተቀርራርቢ ምላሽ ሰጥተዋል።

ትህነግ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ እንዲሁም በግልባጭ ለአፍሪቃ ኅብረት፣ ኢጋድና እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የላከው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው በኢትዮጵያ በኩል የቀረበው ክስ አደገኛ እና እውነትን የገለበጠ፥ በተጨማሪም በዳዩ እንደተበዳይ፣ ተበዳይ ደሞ እንደበዳይ የሚያስቀምጥ ብሎታል ።

የኢትዮጵያ መንግስት የፕሪቶሪያን ስምምነት ከመተግበር ይልቅ በፈጠራ ታሪኮች ህወሓት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ በማካሄድ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትኩረት ለማሳት እየሞከረ እንዳለ ፓርቲው ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ በላከው ደብዳቤ አመልክቷል። ከዚህ በተጨማሪ የፕሪቶርያ ስምምነት እየተጣሰ ነው ብሎ የተለያዩ ነጥቦች ያነሳው ህወሓት፥ ተፈፃሚነቱ ለማረጋገጥ አዲስ ዓለም አቀፋዊ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ዐሳውቋል ።

በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ እየተወዛገቡ ያሉት የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ወደሌላ ዙር ጦርነት ተመልሰው እንዳይገቡ በበርካቶች ዘንድ ስጋት ተፈጥሮ ይገኛል ። በመቐለ ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች ይህንኑ ስጋታቸውን ይገልፃሉ፥ ሰላምን ዘላቂ የሚያደርጉ ርምጃዎች እንዲወሰዱም ይጠይቃሉ ።

ኤርትራ ክሱን ወታደራዊ ፀብ አጫሪነት ስትል ውድቅ አድርጋለች ። የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል “የቀድሞ ግዛትን ለማስመለስ ያለመ” ያሉትን ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑ ዘመቻም ፀብ አጫሪነት የታከለበት ነው መናገራቸውን ተገልጿል።


NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የኤርትራን የሃገርነት እውቅና መሻር አይቀሬ ይሆን?
“መሃል ሰፋሪው” ታደሰ ወረዳ ተከሰሱ፤ ትህነግ የትግራይ ተፈናቃዮች እንዲመለሱ አልፈግልም” አለ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2