ቪኦኢ ዜና – የኢትዮጵያ መንግስት በመጪው ሰኔ ሰላሳ የምግብ ሉዐላዊነት ለማወጅ እቅድ መያዟን ቪኦኢ ሰምታለች። አዋጁን እያንዳንዳቸው ክልሎች በግል የሚያውጁ እንደሆነም ተመልክቷል።
ቪኦኢ ያናገራቸው አንድ ባለስልጣን እንዳሉት ከትግራይ ክልልና አማራ አንዳንድ አካባቢዎች በስተቀር የምግብ እርዳታ እንደማይቀበሉ የሚያውጁት ክልሎች ናቸው።
በኢትዮጵያ ያሉትን ስደተኞች ሳያካትት ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ የምግብ ተረጂዎች እንዳሉ መረጃዎች ያስረዳሉ። እርዳታ አንድ የፖለቲካ ጫና ማሳረፊያ በመሆኑ የተለያዩ ተቋማት በኢትዮጵያ ያሉትን ተረጂውች በጥቅሉ በማስላት ቁጥሩን ከፈ አድርጎ ለማሳየትና በአገሪቱ የተጀመረውን በምግብ ርሳን የመቻል ሩጫ ለማደብዘዝ የሚጥሩ እንዳሉም ተመልክቷል።
በማንኛውም ዓለም እንደሚታየው ልዩ ወይም ከፍተኛ ቀውስ እስካልተፈጠረ ድረስ ኢትዮጲያ ምግብ እንደማትለምን በይፋ ለዓለም ለማሳወቅ ሰኔ ሰላሳን እንደምትጠብቅ ያስታወቁት ኃላፊ፣ በአዲሱ ህግ ችግር ቢፈጠር ክልሎች ራሳቸው ሰባ ከመቶ የሚሆነውን ድጋፍ በማድረግ ህዝባቸውን ይታደጋሉ። አስፈላጊ ሲሆንና ድጋፍ ሲጠየቅ ፌደራል መንግስት ሰላሳ በመቶውን ድጋፍ ያደርጋል።
እንደ አርባ ምንጩ ዓይነት ድንገተኛ አደጋ ሲኖር የፌደራል መንግስት ሙሉ በሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጥ ያስታወቁት ኃላፊ በቂ የመጠባበቂያ እህል እና ዝግጅት ስላለ ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ ስንዴ ለማኝ እንደማትባል አመልክተዋል። በረሃብ ኢትዮጵያን ምሳሌ በማድረግ የቃላት መፍቻና ትርጓሜ እስከማድረግ የደረሰው የስንዴ ልመና ለኢትዮጵያ ትልቁ ድል እንደሆነም ተመልክቷል።



