Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  “ለኢትዮዽያ ያልሰጠናት ምንም ነገር አለ ብለን አናምንም” አንዷለም አራጌ
News

“ለኢትዮዽያ ያልሰጠናት ምንም ነገር አለ ብለን አናምንም” አንዷለም አራጌ

Ethioreview newsEthioreview news—June 24, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

አቶ አንዱዓለም አራጌ ዛሬ የ2013 ዓ.ም. የምርጫ ተሳትፎዋቸውን እና ውጤቱን በተመለከተ ፓርቲው አዘጋጅቶት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የማጠቃለያ ንግግራቸው ላይ ቃል በቃል የተወሰደ…..

የሚቆጫችሁ ነገር አለ ወይ ? ለተባለው፡- ለኢትዮዽያ ያልሰጠናት ምንም ነገር አለ ብለን አናምንም፡፡ በጣም ፈታኝ በሆኑ፣ በጣም ስሜትን በሚፈትኑ ሁኔታዎች ወስጥ ስሜታችንን ገዝተን ሀገር አስቀድመን ነው የተጓዝነው፡፡

ያንን ሁሉ ያደረግነው ለሀገራችን ብለን ነው፡፡ የትልቅነት መገለጫ ነው፡፡ የትልቅነት መገለጫም የሰዎችን ሁኔታ መናገር ሳይሆን በራስ ውስጥ ያለን ስሜት መግዛት ነው፡፡ እንደ ግለሰብ ቀላል ሊሆን ይችላል፡፡ እንደ ድርጅት ግን የተለያዩ አባላቶቻንን ስሜት አርመን ከፊታችን የምናየውን ተስፋ ፣ በትዕግስት ፣ በፅናት መሥራት ያለብንን ሁሉ እንድንሰራ የመጣነው መንገድ በእጅጉ ከባድ ነው፡፡

በኢትዮዽያ ፖለቲካ ውስጥ ሠላማዊ ትግል እንደ ባህል ያልተለመደ ነው፡፡ ያንን ያልተለመደ ያልተሄደበት መንገድ ስንሄድ የገጠመን ፈተና ከባድ ቢሆንም ለሀገራችን ስንል ያላደረግነው፣ ያልወጣነው ያልወረድነው ነገር የለም፡፡

More stories

“ዛሬ እኛ ነን ነገ ደግሞ እናንተ ትሆናላችሁ” ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሤ

May 5, 2023

ሰላም፣እርጋታና የዜጎች ደህንነት ለኢትዮጵያውያን ፍትሃዊ እድገት ወሳኝ ናቸው – በአሜሪካ የህዝብ ዲፕሎማሲ አማካሪ ምክር ቤት

May 17, 2021

ትግራይ በራሷ ልጅ አንደበት ምስክርነት

June 28, 2021

“ኑ ! የወልቃይት ምድር ነጻ ወጥቷል” በስደት የሽሽት ኑሮ ላይ የነበሩ አማሮች ወደ ወልቃይት ጠገዴን ሰቲት ሁመራ ተመለሱ

June 17, 2021

እያንዳንዱን ነገር እያንዳንዱን የኢዜማ ተወዳዳሪ ፣ እያንዳንዱን አባል ብታዩ ፡ ህይወቱን ሰቶ ነው የተወዳደረው፡፡ ለሀገሩ የከፈለው መስዋዕትነት በጣም ከፍ ያለ ነው፡፡እያንዳንዱን ዜጋ ለመድረስ፣ እያንዳንዱን ሕዝባችንን ለማንቃት፣ ህይወታችንን አደጋ ላይ ጥለን ለህይወታችን እንኳን አልሳሳንም፡፡

እውነት ለመናገር እዚህ ባልተረጋጋ ሀገር ውስጥ በየአካባቢው ራሳችንን ፊት ለፊት አጋፍጠን በሠራዊት ታጅበን አይደለም ራሳችን ከሁሉም ሰው መሀከል ላይ አድርገን ሞትን በየደቂቃው ተጋፍጠናል፡፡ ለሀገራችን ያላደረግነው ነገር የለም፡፡

በፖሊሲ ዝግጅት ፣ አዲስ ባህል በማስተዋወቅ፣ በወረዳ ደረጃ ዲሞክራሲን በማለማመድ፣ፓርቲያችን ውስጥ ጭምር ራሳችን በመለማመድና አንደበታችንን በማቀብ ብዙ ነገር ብዙ ናዳ ችለን ነው የተወዳደርነው፡፡ የኢዜማ አባል ብዙ ዱላ ችሎ ፣ ኢዜማም ኢትዮዽያን እያሰበ ወደ ፊት እየተራመደ ያለ ድርጅት ነው፡፡

ስለዚህ እውነት ለመናገር ይሄን ጥያቄ እንኳን አነሳኸው፡፡ ነገር ግን ራሳችሁን ራስህን መጠየቅ የምትችለው ጥያቄ ይመስለኛል፡፡ ኢዜማ የመጣበት አስቸጋሪ መንገድ ያልተገራ የፖለቲካ ስርዓት፣በልተገራ ባህል ውስጥ ኢዜማ ተገርቶ ለመሄድ ያንን ባህልም ለማለማመድ የሄደበት መንገድ ጠመዝማዛ ነበር፡፡

ግን በድል ተጉዘነዋል፡፡ ስለዚህ ለሀገራችን ያልሰጠናት የማንሰጣትም ነገር የለም ወደፊትም፡፡ እና ምንም የሚቆጨን ነገር የለም፡፡

ግልፅ ነው እንግዲህ እኔ ነገሮችን በድፍረት መናገር እውዳለሁ እና ብዙ ጊዜ ሲባል የነበረው ነገር ለምሳሌ ኤሮሚያ ላይ 178 ወንበር ወደ ቁጥር ወደ 547 ወንበር ብትቀይሩት በፐርሰንት 36 ወየም 35 ፐርሰንት አካባቢ ይሆናል፡፡ አንድ የመቶ ሜትር ሯጭ 36ኛው ሜትር ላይ ቆሞ እንወዳደር እና ካሸነፍከኝ እጨብጥሀለሁ ፣ እያለህ አዲስ ባህል ነው እና አሁን እንለማመድ የሚል ተረት ተረት ቀልድ ነው፡፡

ስለዚህም ከመጀመሪያ ማናችሁም ይህንን መጠበቅ ትችላላችሁ፡፡ ህይወት ስናጣ ፣ህይወት ስንገብር ኦሮሚያ ላይ መሳሪያ ሲቀባበል አበበ አለ በህይወት መሳሪያ በት በነበረበት ሁኔታ መቀስቀስ አትችሉም ሲባል፣ መድረስ አትችሉም ሲባል መንገዱ ሁሉ ሲዘጋ ውጤቱ ወደ ማን ሊያጋድል እንደሚችል የታወቀ ነው፡፡

ፖለቲካሊ ኮሬክት ለመሆን ጊዜ እንውሰድ ካላላችሁ በስትቀር መጀመሪያ ምን ዓይነት አቅጣጫ ? እንደተወሰደ በደንብ ያስታውቃል፡፡ ግን የኛ ዓላማ እኛ እንደ ፓርቲ ከማሸነፍ በላይ ደጋግመን ያልነው ቃላቱን እነርሱ እየተቀበሉ እየደጋገሙት ነው፡፡

እኛ ሁልጊዜ የምናመጣው ኢትዮዽያ እንድታሸንፍ ነው፡፡ እኛ ጠዋትና ማታ የምንብሰለሰለው ኢትዮዽያ እንዴት ታሸንፋለች እንጂ እህል ውሃ ፍለጋም ሥራ ፍለጋም እንዳልሆነ ብዙዎቻችሁ የምታውቁ ይመስለኛል፡፡ኢዜማ ውስጥ እሱ አይደለም፡፡

ኢዜማ የሚቃትትለት ዓላማ ኢትዮዽያ እንደ ሀገር አሸንፋ ህዝቧ አንገቱን ቀና አድርጎ የሚኖርበትን ስርዓት ዘመን እንዲመጣ ማድረግ ነወ፡፡

ስለዚህ ውጤቱ ቀድሞ አቅጣጫ ስቶ ነበር ማለት በእውነት ፣ በድፍረት መናገር ይቻላል፡፡

አብራችሁ ትሰራላችሁ ወይ ? ለሚለው ብዙ የምንመክርበት ነገር ነው፡፡ እንደ ፖሊሲ እንደ መርህ ኢትዮዽያ ውስጥ ኢትዮዽያዊነታቸውን ተቀብለው፤ለኢትዮዽያ ይጠቅማል የሚሉት ሃሳብ ያላቸውን የተለየ መንገድ ያላቸው፣ የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ሁሉ እልህ አስጨራሽ ውይይት በማድረግ ፣ ደርድር በማድረግ ስለሀገራችን አብረን እንሰራለን፡፡ ስለሀገራችን እንመክራለን፡፡

በአፈሙዝ ጨክነን እንደ ምንገዳደለው ሳይሆን እሰከመጨረሻው በአንደበት መከራከር የባህላችን አንኳር ምሰሶ መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ ኢዜማ በዚህ በኩል ፋና ወጊ ሆኖ ነው የሚቀጥለው፡፡

ፓሊሲዎቹን ለማስፈፀም ሃሳቦቹን ወደ ፊት ለመግፋት ከየትኛውም አካል ጋር ተቀራርቦ ለመስራ ቅድም አቶ የሺዋስ ብሎታል የኢትዮዽያን አንድነት ፣ የኢትዮዽያን ሰላም የኢትዮዽያን ሀገራዊ ተስፋ የማያጨልም መንገድ ለኢትዮዽያ የሚጠቅመውን መንገድ የማያጨልም መስመር ላይ ሁልጊዜ ኢዜማ ይኖራል የሚለውን ነገር እንድትወስዱልን እንፈልጋለን፡፡

አንድ ጥቅል ነገር መጨረሻ ላይ ልናገር እና ላብቃ፡፡

ኢዜማ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ይሄ ምርጫ በነገራችን ላይ በገንዘብ ደረጃ እንኳን ከምን ዓይነት ፓርቲ ጋር እንደምንወዳደር ታውቃላችሁ፡፡የሚያስፈልገንን ገንዘብ ለማምጣት ከእያንዳንዱ አባል ኪስ ጀምሮ በውጪ ሀገር ካሉ ዜጎች ጭምር ቀን ከሌት የተከፈሉት ዋጋ በጣም የሚያስደምም ነው፡፡ ለኢትዮዽያ ለሀገራቸው ሲሉ፡፡

ስለዚህ አሁንም ኢዜማዊያን እንፀናለን፡፡ ገዝፈን እንቀጥላለን፡፡ ኢዜማ ከዚህ በኃላም ይገዝፋል፡፡ እስከ አሁን መሠረት እየጣለ ነው የመጣው፡፡

ከዚህ በኃላ የኢትዮዽያን መልካ ምድር ሞልቶ ፣ በኢትዮዽያ ፖለቲካ ተንሰራፍቶ ገዝፎ ኢዜማ ውስጥ ያለን ሰዎች የምንታወቀው በታጋይነት ነው፡፡ ትናንት ታጋዮች ነበርን፡፡ ዛሬም ታጋዮች ነን፡፡ ነገም ታጋዮች ነን፡፡ ይሄ ጽናታችን መለያችን ነው፡፡

ስለዚህ ገዝፈን እንቀጥላለን !! ያነገብነውን ራዕይ ለህዝባችን እናስረዳለን!! ሃሳባችንን በያንዳንዱ ልብ ውስጥ እንዲሰርፅ አንዲጋባ እናደርጋለን!!

ኢዜማ ይፀናል ይገዝፋል!! ለኢትዮዽያ ይታገላል!! በምንም ዓይንት መንገድ ወደ ኋላ አንመለስም፡፡

ኢዜማ ውስጥ ያለን ሰዎች…..

ከ Yemisrach Atnafu ፌስ ቡክ

  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
    by Ethioreview news
    ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
    by Ethioreview news
    አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር።… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
    by Ethioreview news
    ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
    by Ethioreview news
    ቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
    by Ethioreview news
    ቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
በኦሮሚያ ያለፈቃድ ምርጫ እንዲካሄድ ያደረጉ በህግ ይጠየቃሉ፤የ100 ምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ ውድቅ ሆነ
የእልቂት ዳንኪራ – ስጋቱ ብዙ ነው
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2