Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  SOCIETY  የኪንታሮት ሕመም (Hemorrhoid) እና የባሕል ሕክምናው መዘዙ
SOCIETY

የኪንታሮት ሕመም (Hemorrhoid) እና የባሕል ሕክምናው መዘዙ

Ethioreview newsEthioreview news—September 5, 2023
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

(ከታች የቀረቡት ሁለት ታሪኮች በእውነታኛ ገጠመኞች የተመሠረቱ ሲሆን ‘አቶ አበበ’ እና ‘አቶ ከበደ’ የሚሉት ስሞች እውነተኛ የታካሚዎች ስም አለመሆኑን እንገልጻለን)

አቶ አበበ የ60 ዓመት አዛውንት ሲሆኑ የ5 ልጆች አባት ናቸው፡፡ የሚኖሩት በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን ላለፉት 2 ዓመታት በኪንታሮት (Hemorrhoid) በሽታ ታመው ከነገ ዛሬ ይሻለኛል ሲሉ ቢቆዩም ሕመሙ ግን እየተባባሰባቸው መምጣት ጀመረ፡፡ ሕመሙ ሲብስባቸው ጎረቤታቸውን በማማከር ወደ ባሕል መድኃኒት ቤት ያመራሉ፡፡

ባለመድሃኒቱም የሚቀባ የባሕል መድሃኒት ይሰጣቸውና እንደሚያድናቸው አረጋግጦላቸው ይሸኛቸዋል፡፡ አቶ አበበ የተሰጣቸውን መድኃኒት እንደተባሉት መቀባት ይጀምራሉ፡፡ በሦሥተኛው ቀን ኪንታሮቱ ይፈነዳና መግል ማውጣት ጀመረ፡፡ በአራተኛው ቀን አቶ አበበ ራሳቸውን ይስታሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ልጆቻቸው ተደናግጠው ወደ ሆስፒታል ያመጧቸዋል፡፡

ሆስፒታል ሲደርሱ የአቶ አበበ የልብ ምት በጣም ይፈጥናል፡፡ የደም ግፊታቸው በጣም ወርዷል፡፡ በድንገተኛ ክፍል ያሉ የጤና ባለሙያዎች በመረባረብ በመርፌ መድሐኒቶችን ፣ ግልኮስ፣ ፈሳሻ ንጥረ ነገርና የተለያዩ ምርመራዎችን ቢያደርጉላቸውም ቁስሉ ኢንፌክሽን ፈጥሮ በደም ውስጥ ስለተሰራጨ የደም ግፊታቸው ሊስተካከል አልቻለም፡፡ ከዚህም የተነሳ አቶ አበበ ጽኑ ሕሙማን ክፍል በአስቸኳይ እንዲገቡ ተደርጎ የተለያዩ የሕክምና እርዳታ ቢደረግላቸውም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም፡፡

More stories

ወገኛ ምርኮዎች !!

August 27, 2021

በዓለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግሥት የሚተገበር የ550 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ይጀመራል

January 29, 2022

በድንገተኛ የሞተር ብልሽት የፖላንድ አውሮፕላን አዲስ አበባ አረፈ

September 18, 2021

ኤርትራዊያን ስደተኞች “አሸባሪው ወራሪሃይል ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ፈጽሞብናል” ሲሉ የዓለም ሕብረተሰብ ተማጸኑ

February 23, 2022

ሌላኛው ታካሚ አቶ ከበደ ናቸው፡፡ እድሜያቸው 58 ሲሆን የባሕርዳር ኗሪ ናቸው፡፡ ከ5 ዓመት በፊት ጀምሮ የኪንታሮት ሕመም (Hemorrhoid) ጀምሯቸው በየጊዜው እየተባባሰቸው ይሄዳል፡፡

ከዚህም የተነሳ አንድ ታዋቂ የባሕል ሕክምና አዋቂ ጋር ይሄዳሉ፡፡ ባለመድኃኒቱም ከመረመራቸው በኋላ በመርፌ የሚወጋ መድኃኒት አዘዘላቸውና ያበጠው ኪንታሮት ላይ መድኃኒቱን በመርፌ ይሰጣቸዋል፡፡ ከዚያም እንደሚድን ነግሯቸው ይሰነባበታሉ፡፡

ወደ ቤት ከሄዱ በኋላ ኪንታሮቱ እብጠቱ እየጨመረ ይሄድና በሳምንቱ ይፈነዳል፡፡ ከዛም ተመልሰው ሲሄዱ ባለመድኃኒቱ እየቆየ እንደሚድንላቸው ነግሮ ይሸኛቸዋል፡፡ ይሁንና ቁስሉ ከመዳን ይልቅ እየሰፋ፣ መግል እያመንጨና እየተባባሰ ይሄዳል፡፡ የዚህን ጊዜ ቁስሉን በጨውና በውሃ እያጠቡ በቤት ይቆያሉ፡፡ ቁስሉ እየሰፋ በመሄዱ ከጥቂት ወራት በኋላ አቶ ከበደ ሰገራ መቆጣጠር ያቅታቸዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ዳይፐር መጠቀም ይጀምራሉ፡፡

ከዚህም በኋላ ወደ ሆስፒታል ሲሄዱ የሕመሙ ደረጃ ከሆስፒታሉ አቅም በላይ በመሆኑ አቶ ከበደ ለተሻለ ሕክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተልከው በተደረገላቸው ምርመራ የፊንጢጣ መቆጣጠሪያ ጡንቻዎቹ ሙሉ በሙሉ በመጎዳታቸው በሆዳቸው በኩል የሰገራ መውጫ (Permanent colostomy) እንዲሠራላቸው ተወሰነ፡፡

ከነዚህና መሰል ብዙ ታሪኮች እንደምንረዳው ለኪንታሮት ተብለው ከትልልቅ ከተማ እስከ ገጠር የሚሰራጩ የባሕል መድኃኒቶች በኅብረተሰቡ ላይ ምን ያህል ጉዳት እያስከተሉ እንደሆነ ነው፡፡

የባሕል ሕክምና በአግባቡ ትኩረት ተሰጥቶት ከዘመናዊ ሕክምና ጋር ቢዛመድ ለማኅበረሰባችን አስተዋፅኦ ሊያበረክት እንደሚችል ቢታመንም የዕለት ተዕለት ገጠመኞቻች ይህ ዓይነቱ የኪንታሮት የባሕል ሕክምና ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ለመናገር ያስደፍረናል፡፡

የኪንታሮት በሽታ (hemorrhoids) ምንድነው?

የኪንታሮት በሽታ (hemorrhoids)፦በፊንጢጣ ላይ የሚገኙ ደም መላሽ የደም ስሮች ሲያብጡ የሚፈጠር በሽታ ሲሆን በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኝ ቢሆንም ከ45 – 65 ዓመት ባሉት ሰዎች ላይ በብዛት ይከሰታል

የኪንታሮት በሽታ በዋናነት በሁለት (types) ይከፈላል

፩. ውጫዊ ኪንታሮት (external hemorrhoids)፦ በውጨኛው የፊንጢጣ ክፍል ላይ የከሰት ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ሕመምም (Pain) ያስከትላል፡፡

፪. ውስጣዊ ኪንታሮት (internal hemorrhoids)፦ በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ሕመም አይኖረውም

ይህ የኪንታሮት ዓይነት 4 ደረጃዎች (grades) አሉት።

  • አንደኛ ደረጃ (Grade-1) ይህ ደረጃ በፊንጢጣ ግድግዳ ላይ እብጠት ሲኖር ነው፡፡ እብጠቱ በዋናነት በስተ ግራ፣ በፊት ለፊትና በስተኋለኛው የፊንጢጣ ግድግዳ ላይ ይከሰታል፡፡
  • ሁለተኛ ደረጃ (Grade-2) በዚህ ጊዜ የእብጠቱ መጠን ጨምሮ ለሽንት ሲቀመጡ በሚኖር ማማጥ እባጩ ወደውጪ ሲወጣና በራሱ ጊዜ ወደውስጥ ሲመለስ ነው፡፡
  • ሦሥተኛ ደረጃ (Grade-3) – በዚህ ጊዜ እባጩ ለሽንት ሲቀመጡ ወደውጪ ይወጣና በራሱ ስለማይመለስ የግድ በእጅ መመለስ ሲፈልግ ነው፡፡
  • አራተኛ ደረጃ (Grade-4) በዚህ ጊዜ እባጩ ላይመለስ በፊንጢጣ ይወጣና ይቀራል፡፡

አጋላጭ ሁኔታዎች (risk factors)

  • የሆድ ድርቀት -አነስተኛ የፋይበር መጠን ያላቸው ምግቦችን ማዘውተር (ፓስታ፣ ማኮሮኒ፣ ነጭ ዳቦ…) እና በቂ ውሃ አለመጠጣት
  • እርግዝና
  • የትልቁ አንጀት ካንሰር
  • ሽንት ቤት ተቀምጦ ለረጅም ጊዜ ማማጥ
  • ረጅም ጊዜ የቆዬ ተቅማጥ (chronic diarrhea)
  • ዕድሜ መጨመር

ምልክቶች (clinical features)

  • ሕመም የሌለው ከፊንጢጣ የሚፈስ ደማቅ ቀይ ደም
  • በፊንጢጣ አካባቢ ማሳከክ
  • ከፊንጢጣ የወጣ ሥጋ መሳይ እባጭ
  • በፊንጢጣ አካባቢ የህመም ስሜት መኖር

የኪንታሮት መዘዞቹ (complications)

  • ኪንታሮቱ ውስጥ የደም መርጋት (thrombosis)ና ከፍተኛ ሕመም
  • ወጥቶ አለመመለስ (irreducible)ና መበስበስ (Necrosis)
  • መመርቀዝ (infection)ና መግል መቋጠር
  • ያልተለመደ የሰውነት ክፍተት (fistula)
  • የሰውነት መሰንጠቅ (fissure)
  • ሰገራን አለመቆጣጠር (Incontinence)
  • የተለመደ ባይሆንም የደም ማነስ ሊያስከትል ይችላል፡፡

ኪንታሮት እንዴት ይታከማል?

በመጀመሪያ ሕመሙ ያለበት ሰው እንደማንኛውም ሕመም ወደ ሐኪም ቤት ሄዶ ለመታከም ፍርሃትን/ሐፍረትን ማሰወገድ ይጠበቅበታል፡፡

፩. በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን (አትክልትና ፍራፍሬ..) መመገብ

፪. ፈሳሽ በበቂ ሁኔታ መውሰድ

፫. ለብ ባለ ውሃ ጨው ጨምሮ 20- 30 ደቂቃ በቀን ሁለቴ ወይም ሦሥቴ መዘፍዘፍ (በበረዶም ሊሆን ይችላል)

፬. ሁሌም ከተፀዳዱ በኃላ በንጹሕ ውሃ መታጠብ

፭. ሻካራ የመፀዳጃ ወረቀቶችን አለመጠቀም

፮. የሰገራ ማለስለሻ መድኃኒት

፯. የሚቀቡ የሕመም ማስታገሻ መድኃኒት መጠቀም

አብዛኛውን ጊዜ ከላይ በተጠቀሰው መንገድ ብቻ ሕመሙ ሊሻሻልና ሊጠፋ ይችላል፡፡በእነዚህ ሕክምናዎች ካልተስተካከለ

  • ቀለል ያለ ቀዶ ሕክምና ሊያስፈልግ ይችላል፡፡

መከላከያ መንገዶች

  • በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ፣ ፈሳሽ በበቂ ሁኔታ መውሰድና የሆድ ድርቀትን ማስወገድ
  • ሰገራ በሚመጣ ጊዜ ጊዜውን ሳያሳልፉ ወደ ሽንት ቤት መሄድ
  • መፀዳጃ ቤት ለረጅም ሰዓት አለመቀመጥ
  • ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶችን ሲያዩ ወደ ሕክምና ተቋም መሔድና ሐኪም ማማከር ያስፈልጋል።

ዶ/ር ዮሐንስ ክፍሌ ፤ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና ሬዚደንት

ቴሌግራም: t.me/HakimEthio Hakim


  • አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት
    መነሻው ቀላል ነው፡፡ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን፡፡ “UTI” ይሉታል የጤና ባለሙያዎች፡፡ ለዚህ ምርመራ ነበር ታካሚዋ ጤና ጣቢያ የሄደችው፡፡ ቢሆንም ግን… Read more: አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት
  • በ2018 ጓደኞቼ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ በድህነት ከተማ ሄዶ መማር ይልቻለው ታዳጊ ለቅሶ!
    “የአስረኛ ክፍል ተማሪ ነኝ። ላለፉት ሁለት ዓመታት ወደ ትምህርት ቤት አልሄድኩም። ትምህርት ባይቋረጥ ኖሮ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ዩኒቨርሲቲ የምገባበት… Read more: በ2018 ጓደኞቼ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ በድህነት ከተማ ሄዶ መማር ይልቻለው ታዳጊ ለቅሶ!
  • “በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ እንስሳት እየሞቱ ነው፤ ሕዝብ እየተሰደደ ነው”
    “ትርጉም አልባ” በሚባልና ሕዝቡን ባሰላቸ ጦርነት ሳቢያ አማራ ክልል ቁልቁል እየሄደ እንደሆነ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ እየተናገረ ነው። ዝርፊያ፣ እገታ፣… Read more: “በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ እንስሳት እየሞቱ ነው፤ ሕዝብ እየተሰደደ ነው”
  • ማርታ አምስት ቀን በላስቲክ ጀልባ በባህር – ደባርቅ፣ ጣሊያን፣ ኖርዌይ፣ አዲስ አበባ – የባከነ ሕይወት
    የዛሬ እንግዳችን አስከፊውን የሕገወጥ ስደት ገፅታ ታስቃኘናለች። ‹‹ሕይወታችንን የሚያሻሽልልን አንዳች ተዓምር እናገኛለን›› በሚል ቀቢፀ ተስፋ ባሕር ማዶን መናፈቅ ማቆም… Read more: ማርታ አምስት ቀን በላስቲክ ጀልባ በባህር – ደባርቅ፣ ጣሊያን፣ ኖርዌይ፣ አዲስ አበባ – የባከነ ሕይወት
  • ጡት የሚያሳድጉ ኢምፕላንቶች ምን ስለሚያስከትሉ ነው ብዙ ሴቶች ከሰውነታቸው እያስወጧቸው ያሉት?
    የ32 ዓመቷ ዩክሬናዊት ካታሪና ክሩፒካ የጡቷን መጠን ለመጨመር በቀዶ ሕክምና የገባላትን ኢምፕላንት እንዳስወጣች በማኅበራዊ ሚዲያ ስትናገር በርካቶችን አስገርሟል። የሰውነትን… Read more: ጡት የሚያሳድጉ ኢምፕላንቶች ምን ስለሚያስከትሉ ነው ብዙ ሴቶች ከሰውነታቸው እያስወጧቸው ያሉት?
SOCIETY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
Netanyahu wants immediate deportation of Eritreans after Tel Aviv violence
ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
SOCIETY

አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት

August 23, 2025
News

በ2018 ጓደኞቼ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ በድህነት ከተማ ሄዶ መማር ይልቻለው ታዳጊ ለቅሶ!

August 22, 2025
SOCIETY

“በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ እንስሳት እየሞቱ ነው፤ ሕዝብ እየተሰደደ ነው”

August 18, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2