በግብጽ ካይሮ ሲካሔድ የቆየው ሶስተኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት እና አለቃቀቅ ደንቦች እና መመሪያዎች የሶስትዮሽ ድርድር ተጠናቀቀ።
ለሁለት ቀናት በተካሔደው መድረክ የሶስቱ ሃገራት ተወካዮች ጠንካራ ድርድር ማድረጋቸው ተገልጿል።
በድርድሩ ላይ በኢትዮጵያ በኩል በሚኒስትር ማዕረግ ዋና ተደራዳሪ በአምባሳደር ስለሺ በቀለ ፣ በግብጽ በኩል የውሃ ሃብትና መስኖ ሚኒስትሩ በፕሮፌሰር ሃኒ ሰዊላም እንዲሁም በሱዳን በኩል በተጠባባቂ የመስኖና ውሃ ሃብት ሚኒስትር በዳወልበይት አብደልራህማን የተመሩ አባላት ተሳትፈዋል።
የሶስቱ ሃገራት ተደራዳሪዎች ወደጋራ መግባባት በሚያደርሱ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ተወያይተዋል።
በመጨረሻም ቀጣዩን ዙር ድርድር ለማካሔድም በፈረንጆቹ ወር ዲሴምበር 2023 አዲስ አበባ ላይ ለመገናኘት ተስማምተዋል።
ኢትዮጵያ በአባይ ውሃ አጠቃቀም ላይ ሁሉንም ወገን አሸናፊ የሚያደርግ ስምምነት ላይ ለመድረስ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
- አጭር ዳሰሳ ሌንጮ ለታ፤ ትግል ሕይወቱበዙፋን ኡርጋ ደራሲነት የተጻፈውን ሌንጮ ለታ ትግል ሕይወቱ መጽሐፍን አነበብኩት። መጽሐፉ በ471 ገጾች እና በሦስት ክፍሎች ተቀንብቧል። የመጀመሪያው ክፍል… Read more: አጭር ዳሰሳ ሌንጮ ለታ፤ ትግል ሕይወቱ
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው







