Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  ማህደር  የረቂቅ ሙዚቃ ስፔሻሊስት (ጥቁሩ ኮዳይ)
ማህደር

የረቂቅ ሙዚቃ ስፔሻሊስት (ጥቁሩ ኮዳይ)

Ethioreview newsEthioreview news—June 9, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የመጀመርያውን የረቂቅ ሙዚቃ ትምህርት ተምረው ከመጡት ውስጥ ግንባር ቀደሙ ሰው፣ የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ትምህርት ታሪክ ማስጀመርያ መሰረት ይሏቸዋል የሙዚቃ ባለሞያው ሰርፀ ፍሬስብሃት።

ለዛሬ የሀገራችን የሙዚቃ ዕድገት ትላንት ላይ ሆነው እሩቅ ተመልክተው ሰርተዋል። ለዚህም ነው በጊዜው ብሄራዊ የሙዚቃ ትምህርት ቤት በመክፈት 7 ክፍሎችንም ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በመዋስ ማስተማር የጀመሩት በማለት ያስረዳሉ የሙዚቃ ባለሞያው።

በዚህ የማስተማር ጥረት ውስጥ ሀገራችን ትልቅ የሙዚቃ ትምህርት ቤት እንደሚያስፈልጋት አይተውና ወጥነው ነበር። ይህን ውጥናቸውንም የያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት እንዲመሰረት በማድረግ አስምረውታል።

የሀገራችን የሙዚቃ ዘርፍ ትልልቅ የምርምር ስራዎች እጥረት አለበት የሚሉት ሰርፀ ፍሬ ስብሀት እሳቸው ይህንን በመመልከት በሀገራቸውና በአህጉራቸው ሙዚቃ ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጹሁፎችን ጽፈዋል።

More stories

ጊዜ መስታወቱ!! ተስፋዬ ገብረአብ ማነው?

January 1, 2024

ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም

September 10, 2023

የኤሮስፔስ ቴክኖሎጂ ለኢትዮጵያ – እንዴት አንገብጋቢ ሆነባት?

June 22, 2024

Astonishing feet — barefoot Abebe Bikila becomes Ethiopia’s first gold medallist at the Games

June 9, 2024

እኝህ ሰው ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ ናቸው። ለመሆኑ እኚህ ሰው ምንድነው ያበረከቱት አስተዋጽዖ? በጥቂቱ እንመልከት።

የረቂቅ ሙዚቃው ሊቅ ትልቁን የኢትዮጵያ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የሆነውን ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት በማቋቋም ስማቸው በጉልህ የሚነሳ፣ የባለዋሽንቱ እረኛ ሙዚቃ ፈጣሪ፣ ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ ግንቦት 8 ቀን 1930 ዓ.ም ተወለዱ።

አባታቸው ግራዝማች ከበደ አድነው ሲሆኑ የሙዚቃ ፍቅር ከልጅነታቸው ጀምሮ እንዲያድርባቸው ያደረጓቸው ደግሞ እናታቸው ወ/ሮ ፈንታዬ መሆናቸው ይነገራል።

መሰረታዊ የሚባለውን ትምህርታቸውን በዳግማዊ ምኒሊክ ት/ቤት እና በቀዳማዊ ኃይላ ሥላሴ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት (ኮከብ ጽባሕ) ካጠናቀቁ በኃላ በሐረር የመምህራን ማሠልጠኛ ኮሌጅ ተመርቀዋል።

ከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በኒው ዮርክ ከሚገኘው የሮቼስተር ዩኒቨርሲቲ “ኢስትማን የሙዚቃ ት/ቤት 1954 ዓ.ም በመጀመሪያ ዲግሪ ከተመረቁ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው የያሬድ ሙዚቃ ት/ቤትን መሠረቱ።

የሙዚቃ ትምህርት ቤቱ የመጀመሪያው ዳይሬክተር ከመሆናቸውም ባሻገር በአዲስ አበባ የወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማህበር (ወ.ወ.ክ.ማ) በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የበጎ አድራጎት ድርጅት መርሓ – ዕውራን ት/ቤት እና በመሳሰሉ የወጣቶች ማህበራት እየተገኙ የሙዚቃ ትምህርት ይሰጡ ነበር።

የያሬድ ት/ቤት ዳይሬክተር ሆነው ከ 1955 እስከ 1958 ዓ.ም ድረስ ባገለገሉበት ወቅት በንጉሠ ነገሥቱ “ብሔራዊ የሙዚቃ አቀናባሪ” ተብለው ከመሠየማቸው ሌላ ለባህላዊ ጉዳዮች ላደረጉት የላቀ አስተዋፅዖ በ1954 ዓ.ም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጎ አድራጎት ድርጅት ተሸላሚ ሆነዋል።

የቀ.ኃ.ሥ የ75ተኛ የልደት በዓል በተከበረበት በዚሁ ዓ.ም በሀንጋሪ መንግሥት ተጋብዘው ወደ ቡዳፔስት በመጓዝ የሚታወቁበትን “እረኛውን ባለዋሽንት” እና “ኢትዮጵያ ሲንፎረያ” የተባሉትን ሁለት ድርስቶቻቸውን በአቀናባሪነት በኦርኬስትራ መሪነት አቅርበዋል፣ በሸክላም አሳትመዋል።

ታዲያ በጉርምስና እድሜያቸው በብዙዎች አዕምሮ ውስጥ የማይጠፋውን “እረኛው ባለዋሽንት” የሚል መጠርያ የሰጡትን ረቂቅ ሙዚቃ ደረሱ። ደርሰውም አላበቁም በሀንጋሪ ፊሊሀርሞኒ ኦርኬስትራ ለህዝብ ለማስደመጥ ወደ አዳራሹ አቀኑ።

ታዲያ ሀንጋሪያውያን በጥቁሩ የረቂቅ ሙዚቃ አዘጋጅና “ኮንዳክተር” ላይ ሊስቁ ወደ አዳራሹ ተመሙ። እንስቃለን እንሳለቃለን ብለው ወደአዳራሹ የገቡት ሃንጋሪያውያኑ በፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ ስራ ተደንቀው እጃቸውን በአፋቸው ጭነው በሀገራቸው በጊዜው ታዋቂ በነበረው ሙዚቀኛ “ኮዳይ” ስም ይጠሯቸው እና ያደንቋቸው ተያያዙ።

“ጥቁሩ ኮዳይም” በሀንጋሪ የፕሮፌሰሩ መጠርያ ሆነ።

ለወትሮው በረቂቅ መሳርያ የተቀነባበረ ሙዚቃ በአውሮፓውያን ዘንድ ብቻ ተወዳጅ ሆኖ ይሳል ነበር። ነገር ግን የፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ “እረኛው ባለዋሽንት” ሥራ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ለጥሞና የሚደመጥ፣ የፕሮግራም ማጀቢያ በመሆን አየር ላይ በመዋል ለዘመናት ተወዳጅነትን ያተረፈ ረቂቅ ሙዚቃ ለመሆን በቃ።

ብዙዎች “እረኛው ባለዋሸንት” የተሰኘው ሙዚቃ በኢትዮጵያውያን ዘንድ እንደዚህ እንዲወደድ ያደረገው ፕሮፌሰር አሸናፊ በሀገረኛ ለዛ ስላዘጋጁት ነው ብለው ያምናሉ።

እውነት ነው እኝህ የሙዚቃ ሊቅ ለሀገርኛ የሙዚቃ እድገት ትልቅ አስተዋፅዖ ያበረከቱ ናቸው። ከእረኛው ባለዋሽንት በተጨማሪም፦

የኢትዮጵያ ሰላም

የፍቅር አንሰር

የሳት እራት

የተማሪ ፍቅር

የሀገራችን ሕይወት

ኒርቫኒክ ፋንታሲ የተሰኙ ረቂቅ ሙዚቃዎችን ለአድማጭ ጆሮ ያደረሱ የሙዚቃ ደራሲ አቀናባሪና ኮንዳክተር ናቸው።

እናታቸው በሚጫወቱት በገና ተማርከው ወደ ሙዚቃው አለም እንደገቡ የሚነገርላቸው ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ ሙዚቃን ከሰው ልጅ አኗኗር ጋር በሚያጠናው “ኢትኖሚውዚኮሎጂ” ዘርፍ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ሰርተዋል።

ከአውሮፓውያኑ 1970ዎቹ ጀምሮ በረዳት ፕሮፌሰርነት የኢትኖሚውዚኮሎጂ ፕሮግራም ዳሬክተር በመሆን በኒውዮርክ ዩኒቨርስቲ “ኪዊንስ ኮሌጅ እና በማሳቹሴትስ ብራንዲስ ዩኒቨርስቲ” በረዳት ፕሮፌሰርነት ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድርስ ለ19 ዓመታት በፍሎሪዳ ዩኒቨርስቲ መጀመሪያ በፕሮፌሰርነትና በኋላም የዩኒቨርስቲው “የጥቁር አሜሪካውያን የባህል ማዕከል” ዳሬክተር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

የሙዚቃ ደራሲና አቀናባሪው ፕሮፌሰር አሸናፊ የሙዚቃ ሰዋሰው የመማርያ መፅሀፍ በአማርኛ፣ ኮንፌንሽን ልቦለድ እንዲሁም Root of Black Music የተሰኙ መጽሐፍትም ለአንባቢያን አድርሰዋል።

የሙዚቃ ሊቁ ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ በ1990 ዓ.ም በ 60 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ህይወታቸው አልፏል።

ታዲያ እኝህ የሙዚቃ ሊቅ በማቋቋም ረገድ ትልቁን ሚና በተጫወቱበትና በመጀመርያ ዳሬክተርነት ባገለገሉበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚገኘው የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት በስማቸው የተሰየመው ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ የፐርፎርሚንግ አርት ማዕከል በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

ከዓለም የሙዚቃ ቀማሪዎች ቀድሞ ሙዚቃን ያወቀ እና የቀመረው ቅዱስ ያሬድ በዓለም ዘንድ በስራው ልክ የሚታወቅ አይደለም። ይሁን እንጂ በስራው ደግሞ ዛሬም የሚያበራ ኮኮብ እንደሆነ ነው። በዚህ ድንቅ እና ቅዱስ ሰው ስም የተሰየመው የሙዚቃ ትምህርት ቤትም የመጀመሪያው ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉት ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደም ድንቅ ስራ ሰርተዋል።

በዚህ መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) “ሙዚቃ የማይታይ ነገርን ማሳየት ነው፤ ያልገባን ነገር እንዲገባን ማድረግ ነው” ብለዋል። ለዚህም ወደኋላ በአንድ ዐይን መመልከት ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅዱስ ያሬድ ስም የተሰየመ ትምህርት ቤት አለን ብሎም ይህ ማዕከል ደግሞ በታዋቂው የረቂቅ ሙዚቃ ባልሞያው ስም ተስይሟል ብለዋል። ይህ በአንድ አይን ወደኋላ መመልከት መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ደግሞ የኋላውን አይቶ ወደፊት ማሻገር እነድሚገባ እና ለዚህም አሁን ላሉ ባለሞያዎች አደራ ብለዋል።

የአንጋፍው የሙዚቃ ትምህርት ቤት የመጀመርያው ዳሬክተርና የሙዚቃ ሊቅ የነበሩት ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ውስጥ ትልቅ አሻራ ያሳረፉ እና ዘመን አይሽሬ ሥራዎችንም ያበረከቱ ሊቅ እንደሆኑ በትውልድ ውስጥ ተቀምጠው ይኖራሉ።

በናርዶስ አዳነ EBC

FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የሻዕቢያ ውጥን ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ “የዋሁ” ሕዝቧ – ኤርትራዊያን ይህን ስሙ
Astonishing feet — barefoot Abebe Bikila becomes Ethiopia’s first gold medallist at the Games
Related posts
  • Related posts
  • More from author
Events

የመደመር መንግሥት አዕማዶች – የመጽሐፍ ዳሰሳ

October 8, 2025
ማህደር

የሦስት ሊቃውንት የአሻራ ቅብብሎሽ

October 5, 2025
ማህደር

“ኦሮሞ ‘ፈጣሪ ጥቁር ነው’ ይላል” የዋቄፈና እምነት

October 4, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2