Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  ማህደር  የፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ አጭር  የህይወት ታሪክ
ማህደር

የፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ አጭር  የህይወት ታሪክ

Ethioreview newsEthioreview news—August 30, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ፕሮፌሰሩ ‹‹ በልጅነቴ በጣም የታደልኩ ነበርኩ፡፡ ሶስት ቤተሰቦች ናቸው ያሳደጉኝ ማለት እችላለው ይላሉ ›› በገዛ አንደበታቸው ስለ ራሳቸው ሲናገሩ፡፡ የፕሮፌሰሩ ታሪክ ከዚህ ይጀምራል፡፡

የዛሬው ፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ ከወላጅ እናታቸው መንበረ ገብረ ማርያም እና ከወላጅ አባታቸው ከእሸቴ ተሰማ ተወልደው በመሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ልጅነታቸውን አሳልፈዋል፡፡

ከእናት እና አባታቸው በመቀጠል ያሳደጓቸው አጎታቸው ጀማነው አላብሰው ወጣትነታቸውን ደግሞ በፓንክረስት ቤተሰቦች ውስጥ እንደ ልጅ በመሆን ትምህርታቸውን እየተከታተሉ በእንክብካቤና በንባብ ራሳቸውን በእውቀትና በልምድ ማጎልበት ችለዋል፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ የዘመናዊ ትምህርት ቤት ፋናወጊ በመሆን በሚጠቀሰው ዳግማዊ ምንሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ህይወታቸውን  ብለው የጀመሩት የያኔው አንድሪያስ እሸቴ በዊልያምስ ኮሌጅ ትምህርታቸውን ተከታትለው ከየል ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን እስካገኙበት ጊዜ ድረስ ሰፊ የንባብ ልምድና የፍልስፍና ሕይወት ውስጥ አልፈው ከሀገር ውጪ በተለያዩ ቦታዎች ከሰሩና በበርካታ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ካስተማሩ በኋላ ወደ ሀገር ውስጥ በመመለስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት በመሆን አገልግለው ቀጥለውም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ አማካሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡ በ1995ዓም የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ሲረቅም በአባልነት የራሳቸውን ሚና አበርክተዋል፡፡

ፕሮፌሰሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት በነበሩበት ወቅት በርካታ ለትውልድ የሚሻገሩ ስራዎችን የሰሩ ሲሆን በፕሬዘዳንትነት ጊዜያቸው ካበረከቷቸው አስተዋፅኦ መካከል በፖሊሲ ደረጃ ውሳኔን በማሳለፍ ዓይነስውራን በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ገብተው ትምህርታቸውን መከታተል እንዲችሉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ምሁር እንደሆኑ ይጠቀሳሉ፡፡ በጋይዳንስ እና ካውንሲሊንግ ስር የነበረውን ለብቻው በማውጣትና ቦታ ሰጥቶ ህንፃ በማሰራት የመጀመርያውን የአካል ጉዳተኞች ተማሪዎች ማዕከል ወይም ( የልዩ ፍላጎት ድጋፍ ማዕከል) ያቀዋቀዋሙት ፕሮፌሰሩ ናቸው፡፡

ለብቻው ሞደርን አርት ሙዚየም በመባል የገብረ ክርስቶስ ስራዎች አሁን ባሉበት መልኩ ተለይተው እንዲቀመጡና እንዲጎበኙ ተያይዞም ጥናትና ምርምር እንዲሰራባቸው አስደርገዋል፡፡ እንዲሁም ከሰባ ዓመታት በላይ ባስቆጠረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው ታሪክ ውስጥ የመጀመርያዋ ሴት ምክትል ፕሬዘዳንት የዛሬዋ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደ ማርያም የተሾመችው በዚሁ ጊዜ ነው፡፡ በርካታ በፒኤችዲ ደረጃ አዳዲስ የትምህርት ዘርፎች እንዲከፈቱ አበርክቷቸው ይነሳል፡፡

ኢትዮጵያ የመጀመርያዋን የሴት ፕሮፌሰር፡ ፕሮፌሰር የዓለምፀሀይ መኮንን ያገኘችው በዚሁ በፕሮፌሰሩ የፕሬዘዳንትነት ጊዜ ነበር፡፡ በዕለቱም በሽልማት ሁሉ በማበረታታት በደስታ ብዛት ዕንባ ተናንቋቸው ነበር ይላሉ በዕለቱ በመድረኩ የታደሙ ታዳሚዎች ሲመሰክሩ፡፡

ሴቶችን ከማብቃት ጋር ስማቸው በተደጋጋሚ ተያይዞ ይነሳል፡፡ በተጨማሪም በፕሬዘዳንትነት ዘመናቸው ከሰሯቸው ስራዎች ሌላው ከትምህርት ክፍሉ ወጥተው  ሙዚቃ፡ቴአትርና ስዕል አንድ ላይ በመሆን ራሳቸውን ችለው እንደ ኮሌጅ ቢቋቋሙ በማለት የተለያዩ ምሁራንን በመጋበዝ ኮሌጁን በእግሩ እንዲቆም ሲያደርጉ ለቴአትር ትምህርት ቤት ታላቁን አዘጋጅ አባተ መኩርያን ወደ ዩኒቨርሲቲው በማምጣት አዲሱ ትውልድ ልምዱን እና እውቀቱን እንዲቀስም ያደረገውም ይኸው ፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ ነው ይላል ታሪካቸው፡፡ 

አንድሪያስ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በዋነኝነት በህግ ፍልስፍና ዙርያ ከፍተኛ የራሱን አስተዋፅኦ በማድረግ በርካታ የህትመት ውጤቶችን ከማሳተም ባለፈ ህግና አዋጅ በማርቀቅና የፖሊሲ ማሻሻያ በማድረግ ለሀገርም ሆነ ለአፍሪካ የራሱን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረግ የቻለ ፈላስፋ ነው ይሉታል ሌሎች የሀገራችን ምሁራን ሲገልፁት፡፡ 

አንድሪያስ ገና በወጣትነቱ በመጀመርያ ያሳተመው ሪቻርድ ፓንክረስት በሚያሳትሙት ‘’ Ethiopia observer ‘’ የተሰኘው መፅሔት ላይ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ብዙም ያልተወራለት የኢትዮጵያ የመረዳጃ ሀብቶች ስለሆኑት ስለ እድር፤ እቁብ እና ማህበራት ዙርያ ከሪቻርድ ፓንክረስት ጋር በመሆን ‘’ self-help in Ethiopia “ በሚል ርዕሰ አርቲክል በመፃፍ ባህላችን ከሌላው ዓለም ጋርም ምን ዓይነት መስተጋብር እንዳለው በመዳሰስ እና በመዘርዘር በተጨማሪም አገር በቀል እውቀትና ባህልን አጉልቶ በማሳየት አንድሪያስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ነበራቸው፡፡

አንድሪያስ በስራ ዘመናቸው በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለም ዓቀፍ የስራ ተሞክሯቸው በዩኔስኮ የሰብአዊ መብት፣ የሰላም እና የዲሞክራሲ ሊቀ-መንበር በመሆን አገልግለዋል፡፡ ብራውን ዩሲኤልኤ፡ዩሲ-በርክሌይ እና ፔን በማስተማር ያገለገለባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡

በአሜሪካን ሀገር በነበሩበት ወቅት በሰበዓዊ መብቶች ንቅናቄ ላይ ንቁ ተሳታፊ ነበሩና በብላክ ፓንተር ፓርቲ ውስጥም ተሳትፎ የነበራቸው ምሁር ነበሩ፡፡ በሞራል እና ፖለቲካዊ ፍልስፍናዎች እንዲሁም ስነ-ምግባር ላይ ያተኮሩ የድርሰት ውጤቶችን በበርካታ መንገዶች ለህትመት አብቅቷል፡፡ ከፍልስፍና ባሻገር ስለ ኢትዮጵያ አጫጭርም ሆነ ረጃጅም አርቲክሎችን በተለያየ ወቅት አስነብቦናል፡፡

ፕሮፌሰሩ በሙሉ ጊዜያቸው ተምረዋል፡ አስተምረዋል፡ ተፈላስፈዋል፡፡ አንድሪያስ እሸቴ በአስተማሪነት ካገለገለባቸው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በአሜሪካን ሀገር በሚገኘው ብራውን ዩኒቨርሲቲ፡ ዩሲኤልኤ፤በርክሊን፣ ፔንሲልቬንያ ዩኒቨርሲቲ ከሀገር ውጪ ያስተማረባቸው ቦታዎች ሲሆኑ በርካታ ተማሪዎችም ማፍራት ችሏል፡፡

የተለያዩ ቦታዎች ማስተማር ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የትምህርት ዓይነቶችንም በማስተማር ይታወቅ ነበር፡፡ ከፍልስፍና እስከ ስነ-ምግባር፣ከሀይማኖት እስከ ስነ-ውበት፣ ከወንድማማችነት እስከ ነፃነት በርካታ ፍልስፍናዎችን ማጋራት ችሏል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን ካተረፉ ዝነኞች ውስጥ በአሜሪካ ከዋነኞቹ የፖለቲካ ፈላስፋ መሀል ጆሴፍ ኮን እንዲሁም የሂውማን ራይትስ ዎች ፕሬዘዳነት ኬኔት ሮፍ ከፕሮፌሰሩ ተማሪዎች ውስጥ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡   
ፕሮፌሰሩ ገና በወጣትነታቸው በኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ወቅት ታዋቂ ምሁር ከነበሩት ውስጥ አንዱ ነበር፡፡ በብዕር ተጋድሎአቸው፣ በጥቁሮች መብት ጋር ባለው አቋም፣ በአንባቢነቱ  በምሁርነቱ ዙርያ የሚያሻማ ሀሳብ ባይኖርም በኋላ በመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ(መኢሶን) ፓርቲ ውስጥ በመታቀፍ አባል ሆኖ ለሀገሩ ያበረከተው ፖለቲካዊ አስተዋፅኦ አብሮ ይነሳል፡፡

ፕሮፌሰሩም ቢሆን ከታላላቆቹ ፈላስፎች ውስጥ  የፕሌቶ፣የማርክስ እና ሄግልስ አድናቂ ሲሆኑ ከሀገር ውስጥ ምሁራን እነ ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ እና መንግስቱ ለማ ስራዎችን ማንበባቸውን እና መውደዳቸውን ሳይሸሽጉ ለስነ-ፅሁፍም ከፍተኛ ፍቅርና ክብር እንዳላቸው ይናገራሉ፡፡

ከማስተማር እና የዩኒቨርሲቲ ህይወት ባሻገር በተለያዩ ዘመናት በጦርነት ሰበብ በርካታ የሀገር ቅርሶች፣ የቤተክርስትያን እና የሀገር መዛግብት፣መስቀል እንዲሁም የብራና መፅሐፍቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ለመመለስ ታስቦ በተቋቋመው ተወሰዱ እና የተዘረፉ የኢትዮጵያ ቅርሶችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስመለስ በነበረው ኮሚቴ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ከፍተኛ ሙግት በመግጠም እና በማሳመን የተወሰኑትን ሀብቶች በጊዜው ማስመለስ ከቻሉ የኮሚቴ አባላት ውስጥ አንዱ አንድሪያስ እሸቴ ናቸው፡፡

የአድዋ ጦርነት መቶኛ ዓመት መታሰቢያ በሚከበርበት ወቅትም አስተባባሪ የነበሩ ሲሆን አድዋ አባቶቻችን ከሰሩዋቸው ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ሳይሆን መላ ጥቁርን የሚያኮራ ታሪክ እንደሆነ ፈላስፋው በፅኑ የሚያምኑበት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በ1995 ህገ-መንግስት በሚሻሻልበትና በሚረቅበት ወቅት የህገ-መንግስት እና አስተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪ አባል በመሆን አገልግለዋል፡፡ በቦርዱም ውስጥ ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ እንደነበራቸው ይነገርላቸዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት የሰብአዊ መብቶች መታሰቢያ ፕሮጀክት ጊዜያዊ ቦርድ ሊቀ-መንበር እና አባል በመሆን ፓን አፍሪካንነትን በፅኑ ከሚያቀነቅኑ ምሁር ውስጥ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡ እንዲሁም የጣና ፎረም ከፍተኛ ደረጃ መድረክ ሊቀ-መንበር በመሆን እና የፌዴሬሽን መድረክ ቦርድ አባል በመሆን አገልግለዋል፡፡

ከጽሑፎቹ መካከል ስለ “ወንድማማችነት” የጻፈው ድርሰቱ በኢትዮጵያ በተግባራዊ ሥራው ውስጥ ትልቅ ሚና የተጫወተ ይመስላል። ከሦስቱ አስተሳሰቦች፣ “ነፃነት፣ እኩልነት እና ወንድማማችነት”፣ የምዕራቡ ዓለም የፖለቲካ ፈላስፋዎች “ነፃነት እና እኩልነት” ላይ ያተኮሩ እና “ወንድማማችነትን” ችላ ብለዋል በኢትዮጵያ የብሄር ፌደራሊዝም አውድ ውስጥ “ወንድማማችነት” የሚለውን ሃሳብ የጋራ ቋንቋ እና ባህል ላላቸው ብሄረሰቦች መተግበር አስተማማኝ ይመስላል።

“ብሔርተኝነትን” በ “የጎሣ ማንነት” በመተካት የወንድማማችነት ምሳሌ በመሆን ብሔርተኝነትን የሚመለከት ተመሳሳይ መከራከሪያ ማቅረብ ይቻላል።
ፕሮፌሰሩ ከስራ ህይወታቸው ባሻገር የቅርብ ወዳጆቻቸው ሲገልጧቸው አንድሪያስ አንባቢና ሙሉ ፈላስፋ ነው፡፡ የምትተማመኑበት ጓደኛ፣አዋቂ እና ተጫዋች ነው፡፡ ስስ የሆነ ነፍስ አለው የተጎዳ ሰው ካየ በዕንባ ሀዘኑን ይገልፃል፡፡ ደግና ለሴቶች መብት አብዝቶ የሚጨነቅ ሰው ነው ብለው ይገልፁታል ወዳጆቹ፡፡ በኢትዮጵያ ቁልፍ የታሪክ ሁነቶች ውስጥ ታዛቢ ብቻ ሳይሆኑ ቁልፍ ተሳታፊም ነበሩ፡፡

ፕሮፌሰር የግል ህይወቱ በጥልቅ ንባብና ልምድ የዳበረ፣ ያመነበትን የሚኖር ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ ነው በማለት የስራ ባልደረቦቹ ይገልፁታል፡፡ አንድሪያስ ከወለደው ልጁ አሉላ አንድሪያስ በተጨማሪ የአባት ፍቅር እየሰጠ ያሳደጋቸው የቀድሞ ባለቤቱ የእሙዬ አስፋው ሁለት ልጆችን ታጠቅ እና አደይን ጨምሮ የሶስት ልጆች አባት ነበር፡፡

(Via ተወዳጅ ሚዲያ)

archive
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የፐርፐዝ ብላክ አክሲዮን ማኅበር ሥራ አስፈጻሚዎች ታሰሩ
“መንግስት እንደ አክቲቪስት ከሆነ አደጋ ነው” አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
Events

የመደመር መንግሥት አዕማዶች – የመጽሐፍ ዳሰሳ

October 8, 2025
ማህደር

የሦስት ሊቃውንት የአሻራ ቅብብሎሽ

October 5, 2025
ማህደር

“ኦሮሞ ‘ፈጣሪ ጥቁር ነው’ ይላል” የዋቄፈና እምነት

October 4, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2