Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  የተሸጡት አባት አባ መፍቀሬ ሰብዕ-    ወደ ፈጣሪያቸው ሄዱ
NewsOPINION

የተሸጡት አባት አባ መፍቀሬ ሰብዕ-    ወደ ፈጣሪያቸው ሄዱ

Ethioreview newsEthioreview news—October 16, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በአውሮፓ ክርስቲያኖች ዘንድ የታወቀ አንድ የአራተኛው መክዘ ታሪክ አለ፡፡ ድኾችን እጅግ የሚወድ፣ የተቸገሩትን ለመርዳት ምንም ነገር የማያግደው፤ ከእራሱም አብልጦ ለሌሎችን የሚሞት አንድ ሰው ነበረ፡፡ ይህ ሰው በበጎ ምግባሩ የተነሣ ስሙ ተረስቶ ‹እኁ ቅዱስ- ቅዱሱ ወንድም› እየተባለ ነው የሚጠራው፡፡ በታሪክ ድርሳናትም የተመዘገበው በዚሁ ስም ነው፡፡ ሠርቶ የሚያገኘውን ምንም ለሌላቸውና ለምነው እንኳን ለማግኘት ዐቅም ላነሣቸው በመስጠት የታወቀ ነበር፡፡

አንድ ጊዜ የሚሰጠው ነገር አጣ፡፡ ብዙ ችግረኞች ደግሞ መልካም ዜናውን ሰምተው ጥቂት ነገር ለማግኘት ወደ እርሱ ዘንድ መጡ፡፡ ምን ይስጣቸው፡፡ የሚያያቸው አካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ሌላ አማራጭ የላቸውም፡፡ ብዙዎቹ ገንዘቡን ከጨረሰ በኋላ ከሩቅ ሀገር ሳይቀር በመምጣታቸው አዘኑ፡፡ መመለሻ እንኳን የላቸውም ነበር፡፡ በመጨረሻ እኁ ቅዱስ አንድ ውሳኔ ላይ ደረሰ፡፡ ‹‹እኔን ሽጡኝና ተካፈሉ› አላቸው፡፡ እነዚያ ችግረኞችም ምን አማራጭ ስላልነበራቸው እርሱን በባርነት ሸጡትና ገንዘቡን ተካፈሉ፡፡


ይህ ታሪክ በታሪክነቱ ሲወሳ የኖረ ነው፡፡ አንዳንዴ ግን ታሪክ ራሱን ይደግማልና አንድን ታሪክ የሚካፈሉ ሁለት ሰዎች በሺ ዘመናት ልዩነት ውስጥ ሳይቀር ይፈጠራሉ፡፡ እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥም እንደ ‹እኁ ቅዱስ› የተሸጡ ሰው አሉ፡፡ እዚያ ደቡብ – ወሎ ደሴ፡፡

ደሴ የምትታወቀው በፍቅር ከተማነቷ፣ የኢትዮጵያ ባሕላዊ ዜማዎች አምባ በመሆኗ፣ በንጉሥ ሚካኤል ታሪክና በአይጠየፍ አዳራሽ፣ በዘመናዊው የኢትዮጵያ የመንግሥት ታሪክ ውስጥም በያዘችው ቦታ ብቻ አይደለም፡፡ ብዙ ያልተነገረላቸው ፣ በደሴ ተራሮች ላይ የሚያበሩ፣ የሚንቀሳቀሱ፣ የሚተነፍሱና ሕይወት ያላቸው የደሴ ውድ ቅርስም አሉ፡፡

እኒህ ሰው የትውልድ ቦታቸው ወሎ እንዳልሆነ በቅርበት የሚያውቋቸው ይናገራሉ፡፡ ምናልባት ወደ ሰሜን ሸዋ አካባቢ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ እስካሁን ግን የተወለዱበትን ቦታና ዘመን በርግጠኝነት የሚያውቅ የለም፡፡ እርሳቸውም ሃይማኖታቸውንና ምግባራቸውን እንጂ ሰው ትውልዳቸውንና ጎሳቸውን እንዲጠይቃቸውም እንዲያውቅላቸውም አይፈልጉም፡፡ ከጥንት ጀምሮ የሚያውቋቸው የደሴ ከተማ ሽማግሌዎች ግን እርሳቸውን ያወቁበትን ጊዜና በዚያ ጊዜ የስንት ዓመት ሰው ሊሆኑ እንደሚችሉ በመገመት እድሜያቸውን በሰባና ሰማንያ መካከል ይገምቱታል፡፡ ወደ ጎንደር ለትምህርት ሲሄዱ ደሴ ደረሱ አሉ፡፡ እዚያ የፈረሱ አብያተ ክርስቲያናትና የተጎዱ ሰዎችን አዩ፡፡ እዚህ በተግባር የሚሠራ ሥራ እያለ እዚያ የቃል ትምህርት ለመማር ምን ወሰደኝ ብለው እዚያው ደሴ ቀሩ አሉ፡፡

እኒህ ሰው የሚታወቁት በሥራና በፍቅር ነው፡፡ በደሴ ከተማ የሚገኙትን አብያተ ክርስቲያናት በማሳነጽ፣ ታሪክ ሲዘክረው የሚኖር አሻራ አኑረዋል፡፡ እንዲያውም እርሳቸው ካልገቡበት የሚሳካ አይሆንም ብለው ደሴዎች እስኪገምቱ ድረስም ደርሰዋል፡፡ እርሳቸው ካዘዙ ምደርም ትታዘዛለች እንኳን ሰው ይባላል፡፡ የርሳቸው በጎ ሥራ ግን በዚህ የሚያቆም አይደለም፡፡ የተቸገረና የተጨነቀ ሰው ካገኙ ግንባር ቀደም ደራሽ ናቸው፡፡ ለርሳቸው ዘርና ሃይማኖት ሰውን ለመርዳት መመዘኛዎች አይደሉም፡፡ ሰውነት ብቻ ይበቃቸዋል፡፡ ይህ ርዳታቸው ከመከራ ያወጣቸው፣ ከችግር የታደጋቸውና ሕይወታቸውን ያቀናላቸው ሰዎች ስለ እኒህ አባት ሲያወሩ ከማያቋርጥ ዕንባ ጋር ነው፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም ከንግግር ይልቅ እርሳቸውን እያሰቡ ዝም ብለው በማልቀስ ይገልጧቸዋል፡፡

መቼም ለአንዳንዱ አብዝቶ አይደል የሚሰጠው፡፡ እርሳቸው የአካባቢ ጥበቃ አርበኛም ናቸው፡፡ በዚህ የእርግና እድሜያቸው እንኳን መኮትኮቻና መቆፈሪያ፣ አካፋና ባሬላ ይዘው በደሴ ተራሮች ላይ ዛፍ ሲተክሉ ይውላሉ፡፡ ደሴን በአራቱ መዓዝን ስታዩዋት አረንጓዴ ብትሆንባችሁ አትገረሙ፤ እርሳቸው ከአርባ ዓመት በላይ ለፍተውላት ነው፡፡ ለእርሳቸው ዛፍ የሚቆርጥ ቀርቶ ቅጠል የሚበጥስም የማርያም ጠላት ነው፡፡ አይከፈላቸውም፤ አልተመደቡም፤ ደብዳቤ የሰጣቸው የለም፤ እርሳቸው ግን የሀገሬ መራቆት የኔ መራቆት ነው ብለው ደን ሲተክሉና ሲከባከቡ ይኖራሉ፡፡

የእኒህን አባት ስም የሚያውቀው የለም፡፡ ስማቸው ተረስቷል፡፡ ስማቸው የተረሳው ሕዝብ ሌላ የፍቅር ስም ስላወጣላቸው ነው፡፡ ሕዝብ የንቀት ስም፣ የውርደት ስም፣ የሃፍረት ስም ይሰጣል – ለጠላው፡፡ ሕዝብ የፍቅር ስም፣ የክብር ስም፣ የቁልምጫ ስም ይሰጣል – ላፈቀረው፡፡ ለእርሳቸውም ወላጆቻቸው ያወጡላቸውን ስም የሚያስረሳ ስም ሰጥቷቸዋል፡፡ መፍቀሬ ሰብ (ሰውን የሚወድድ፣ ሰውም የሚወደው) የሚል ስም፡፡ አባ መፍቀሬ ሰብ ይባላሉ፡፡

ድፍን ደሴ ይታዘዛቸዋል፡፡ ንጽሕናቸውንና ሰው ወዳጅ መሆናቸውን ይመሰክርላቸዋል፡፡ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም እኩል ልጃቸው ነው፡፡ የግሼንን መንገድ ሲያሠሩ በደሴ ከተማ የታወቁት የሙስሊም ባለሀብት ‹ሃምሳ ሺ ብር ሰጡኝ› ብለው ነግረውኛል፡፡ ቤታቸው ብትገቡ ትደነቃላችሁ፡፡ ወንበርና አልጋ ነው ያላቸው፡፡ አልጋው ላይ መጻሕፍት በክብር ተደርድረዋል፡፡ ‹‹አልጋ ለንጉሥ ነው፤ ነገሥታቱ ደግሞ መጻሕፍቱ ናቸው፡፡ አልጋው ላይ የሚኖሩት እነርሱ ናቸው›› ይላሉ፡፡ ሰው ለሀገሩና ለወገኑ መልካም ሲሠራ ካዩ የለበሱትንም ካባ ቢሆን አውልቀው ይሸልማሉ፡፡ ስለ እርሳቸው ሲነገር አይወዱም እንጂ ስለ መልካም ሰዎች ተናግረው አይጠግቡም፡፡

አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፡፡

የደሴ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተጀመረና ለመጨረስ ገንዘብ አጠረ፡፡ ወዲህ ቢባል ወዲያ ገንዘብ ከየት ይምጣ፡፡ የደብሩ አስተዳዳሪ አውጥተው አውርደው አንድ ሃሳብ አመጡ፡፡ አባ መፍቀሬ ሰብ እንደ እኁ ቅዱስ መሸጥ አለባቸው፡፡ ሄዱና አማከሯቸው፡፡ ‹‹አባ እርስዎን ሸጠን የገብርኤልን ቤተ ክርስቲያን ልንጨርስ ነው›› አሏቸው፡፡ ‹‹እኔ ምን አወጣላችኋለሁ›› አሉ ገርሟቸው፡፡ ‹‹በደንብ ያወጣሉ፡፡ ብቻ ለመሸጥ ይስማሙልን›› አሏቸው፡፡ ‹‹ካወጣሁ እንኳን እንድ ጊዜ ዐሥር ጊዜ ልሸጥ›› አሉ አባ መፍቀሬ ሰብ፡፡

በእርሳቸው ስም የርሳቸው ፎቶና ስም ያለበት ቶምቦላ ተዘጋጀ፡፡ ድፍን ደሴ – ሙስሊም ከክርስቲያኑ ተሻምቶ ገዛው፡፡ መፍቀሬ ሰብእ አይደሉ፡፡ ያልተሰበሰበውን ጨምሮ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ተሸጡ – አባ መፍቀሬ ሰብ፡፡ ሌሎቹ የሀገር ሀብት፣ ቅርስና ታሪክ በሚሸጡበት ዘመን አባ መፍቀሬ ራሳቸውን ለሀገርና ለወገን፣ ለእምነታቸውና ለዓላማቸው ሸጡ፡፡ ሌሎች በቤተ እምነቶች ውስጥ ተደብቀው ለጥቅማቸው ሲሉ የምእመናንን ገንዘብ በሚበሉበት ዘመን፤ ለምእመናን ሲሉ አባ መፍቀሬ ሰብ ተሸጡ፡፡ ሌሎች በጎቻቸውን ለራሳቸው ሲሸጡ፤ አባ መፍቀሬ ግን ለበጎች ሲሉ ራሳቸውን ሸጡ፡፡ እልም ባለ በረሃ ውስጥ የምትገኝ ቀዝቃዛ ምንጭ ተስፋ የቆረጠውን ሁሉ እንድታረካ፤ ታማኝነትና ሕዝብን መውደድ፣ በዓላማ መኖርና ለዓላማ መሠዋት እየጠፋ ባለበት ዘመን፣ እርሳቸውን ማየት እንደዚያ ነው፡፡
(ዳንኤል ክብረት – ዓመታት በፊት በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የቀረበ)

ስለ ቅዱሳን የተማርነውን በዓይናችን ያየንባቸው አባት። ሙስሊም ክርስቲያኑ የሚወዳቸው የሚያከብራቸው አባት። ተራሮችን በዛፍ የታረዙትን በልብስ የሸፈኑ አባት። ቤታቸውን በትምህርት ካሴት ልባቸውን በሰው ፍቅር የሞሉ አባት። ወላጆቻቸው ያወጡላቸው ስም ተረስቶ ሕዝብ ባወጣላቸው የፍቅር ስም የሚጠሩ አባት። ወደ ፈጣሪያቸው ሄዱ። በረከታቸው ይድረሰን።

አባ መፍቀሬ ሰብዕ ኪዳነወልድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ


በተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አድባራት በሐይማኖታዊ አስተምህሮ፣ አንድነትን በማስተማር እንዲሁም በብዝኀ ሕይወት ጥበቃ ስራ ያገለገሉት አባ መፍቀሬ ሰብዕ ኪዳነወልድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

በ1921 ዓ.ም የተወለዱት አባ መፍቀሬ ሰብዕ በግሸን ደብረ ከርቤ ለበርካታ ዓመታት ሲያገለግሉ ቆይተው በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

More stories

“ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረው

April 29, 2024

የጁንታው መደምሰስ አመላካቾች!!

August 31, 2021

“ውሳኔውን በመርህ ደረጃ የተቃወመ አላየሁም” ቹቹ አለባቸው

April 8, 2023

ላይቤሪያ፣ ብሩንዲ፣ ሩዋንዳ ፣ሶማሊያ፣ በችግራቸው ወቅት ስለደረስክላቸው ውለታህን አልረሱም ከአማፂያን አብረው ደምህን አላፈሰሱም

July 3, 2021

አባ መፍቀሬ፤ በተለያዩ ሐይማኖት ተከታዮች እና የሕብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ተወዳጅ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል፡፡

OPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
በሙስና የተከሰሱት የብ.መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች በስር ፍርድ ቤት የተጣለባቸው የቅጣት ውሳኔ ተሽሮ አዲስ ፍርድ ተፈረደባቸው
ጉቦ በመቀበል የሙስና ወንጀል በተጠረጠሩት የገቢዎች ቢሮ የኦዲት ባለሙያዎች ላይ ክስ የመመስረቻ ጊዜ ተፈቀደ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2