Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  FEATURED  “ሻምቡ፣ ወለንጪቲ ዙሪያ፣ ፊንጫና አንገር ጉቲን ሂዱና ህዝብ አነጋግሩ፣ ቢያንስ ሃምሳ ከመቶ ወደ እውነት ትደርሳላችሁ”
FEATURED

“ሻምቡ፣ ወለንጪቲ ዙሪያ፣ ፊንጫና አንገር ጉቲን ሂዱና ህዝብ አነጋግሩ፣ ቢያንስ ሃምሳ ከመቶ ወደ እውነት ትደርሳላችሁ”

Ethioreview newsEthioreview news—November 27, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

“ሲጀመር ራሱን የፖለቲካ ተቋም አድርጎ ክልልንም ይሁን አገርን ለመምራት የሚዘጋጅ ሃይል ራሱን ስልጣን ላይ ካለው አካል የተሻለ አድርጎ ያቀርባል እንጂ ዜጎችን አያፍንም፣ አይገልም፣ አያግትም፣ አያፈናቅልም፣ መከራ ውስጥ አይከትም” የሚሉት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁና በኢትዮጵያ ፖለቲካ አውድ በሚሆነው ሁሉ ያዘኑ የኦፌኮ አባል ናቸው።

ስለ ድርጅታቸውም ሆነ ስለ ግል ፖለቲካ እምነታቸው ምንም መናገር እንደማይፈልጉ ገልጸው ለአዲስ አበባ ተባባሪያችን “ሻምቡ፣ ወለንጪቲ ዙሪያ፣ ፊንጫና አንገር ጉቲን ሂዱና ህዝብ አነጋግሩ፣ ቢያንስ ሃምሳ ከመቶ ወደ እውነት ትደርሳላችሁ” ሲሉ ለሚዲያዎች አቅጣጫ አሳይተዋል። ይህን ሲሉ ግን መረጃው እንዲመጣጠን እንጂ ማንንም ለመከለል ወይም ለማሳጣት እንዳልሆነ አመልክተዋል።

“ቢያንስ” ሲሉ እኚሁ ሰው ” ቢያንስ የተጠቀሱት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ሰው ናቸውና ሚዲያው ፖለቲከኞቹን ወደ ጎን ትቶ ያነጋግራቸው፤ ህዝብ ይናገር፤ ሚዲያ የህዝብ መናገሪያ እንጂ አቋም የያዙ አጋፋሪዎች ሃያ አራት ሰዓት የሚለፈለፉበት አውድ አይደለም” ሲሉ የወቅሳሉ። ይህን ለማለት ያነሳሳቸው ሚዲያው በተጠቀሱት አካባቢዎች እየተፈጸመ ያለውን ክፉ ድርጊት በስማ በለው፣ በፖለቲካ ትርፍና ዕቅድ፣ በግልና በተጠና የሌሎች ዓላማ በተቃኘ መልኩ የሚቀርበው መረጃ ስለሰለቻቸው ነው። መፍትሄ ለማፈላለግም ስለማይጠቅም ነው።

“በግል ወጥቼ የማውቀውን ብናገር ኦሮሞ ስለሆንኩ ከትችት አልድንም፣ በኦሮሚያ በኩልም ተቃዋሚ ፓርቲ ውስጥ ስላለሁ ከፓርቲዬና ከግል ፍላጎቴ የምናገረው ተደርጎ ይወሰዳል” ያሉት እኚሁ የኦፌኮ አመራር ” ለምሳሌ ፊንጫ፣ ሻምቡና አካባቢው ላይ ማን እንደነበረ፣ ማን ዝርፊያ እንደፈጸመ፣ ስኳር ፍራብሪካውን ሲወሩ እነማን በጋር ፈጸሙት፣ እነማን ነዋሪዎችን እንደገደሉ፣ አሁንም ማን እዛ አካባቢ ጫካ ጫካውን እንዳለ ሚዲያዎች ሂዱና ህዝቡን ጠይቁና ዘግቡ” የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል። በየ ቤተክርስቲያኑ ምን ሲፈጸም እንደነበር፣ አሁንስ ምን እየሆነ ነው? የሚለውን ምዕመኑን በመጠየቅ ሃቁን ማስተላለፍ የወቅቱ ግዴታ እንደሆነ ይናገራሉ።

More stories

መረራ ጉዲና “የዕድሜ ልክ ሃዘንና ቁጭቴ”

September 1, 2024

የባህር በር ህልውናችን!! አብይ አህመድ “መተንፈሻ ወደብ ያስፈልገናል” ሲሉ አወጁ

December 30, 2023

መረን የተለቀቀውና ስርዓት የተጓደለበት የዋጋ ንረት፤ ሰሚ ያጣው የሸማቹ ጩኸት አይሰማም?

March 28, 2025

የኢትዮጵያ ህዝብ “እምቢ” ያለው የሩዋንዳን የዘር ጭፍጨፋ ሚዲያዎች እንዴት አቀጣጠሉት? የዓለም ዓቀፍ ማህበርሰብ ሚናስ?

April 8, 2024

“አንገር ጉቲን ሙሉውን ምን ሲደረግ እንደነበር፣ ማን ይፈጽመው እንደነበር፣ ህዝቡን እንዴት ይዘርፉትና ይቀሙት እንደነበር፣ ከስሚ ስሚ ይልቅ አርሶ አደሩ እንዲናገር፣ ምስክርነቱን እንዲሰጥ ማድረግ ወደ ሚዛናዊ ድምዳሜ ያመጣሎ” ሲሉም ቦታ ጠቅሰው ተናግረዋል። ማንም ይፈጽመው ማን ንጹሃን ላይ የሚፈጸም ወንጀል ተቀባይነት እንደሌለው በማስታወቅ፣ ሃቁን በመረጃ ይፋ ማድረግ ደግሞ ለፍትህ ውሳኔ እንደሚጠቅም አስታውቀዋል።

“እገታ፣ ስርቆት፣ አፈና የፖለቲካ ድረጅት ባህሪ አይደለም። ምንም ተቃዋሚ ብሆን በየትኛውም መስፈርት አገር የሚመራ ፓርቲ ንጹሃንን እያገተ በድርድር ገንዘብ አይቀበልም” ያሉት የኦፌኮ አመራር በተመሳሳይ ስልጣን ለመያዝም የሚነቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶችም ህዝብን እያሰቃዩና እያገቱ በድርድር ገንዘብ ሊቀበሉ እንደማይችሉ በአመክንዮ ያስረዳሉ።

“ሃቁ ይህ ከሆነ” አሉ ፖለቲከኛው ” ሃቁ ይህ ከሆነ ማን ነው ይህን የሚፈጽመው? ብሎ መጠየቅና መመርመር እንጂ የጅምላ ጩኸትና ፍረጃ ጉዳት እንጂ ጥቅም አያስገኝም” ባይ ናቸው።

ከጅምላ የመርዶና የለቅሶ፣ የምሬትና የሰቆቃ ሪፖርት ይልቅ የሚሰማውን ዜና ተከትሎ ለማጥራትና ትክክለኛ የሆነውን መረጃ ለህዝብ ለመስጠት የሚተጉ ሚዲያዎች አለመኖራቸው ትልቅ ችግር እንደሆነ ይናገራሉ። በተጠቀሱት አካባቢዎችም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች ሚዲያዎች ግብተው ለመስራት ስጋት አለባቸው በሚል ለተጠየቁት ” አዎ ስጋት አለ። መከላከያ ሽፋን ሰጥቶ የግል ሚዲያዎች ወደ ተጠቀሱት አካባቢዎች ገብተው ህዝብን አነጋገረው የሰሙትንና ያዩትን እንዲዘግቡ ቢደረግ ታሪኩ ሌላ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም” ሲሉ መንግስት በጉዳዩ ላይ ተባባሪ ሆኖ ይህን አውድ እንዲያመቻች ይጠይቃሉ።

ከዚህ ቀደም ባሰራጨነው ዜና “ኦሮሚያ ውስጥ የሚሆነው ሁሉ በመናበብ የሚሰራ ላለመሆኑ ምን ማስረጃ ማቅረብ ትችላለህ” ሲሉ አንድ ጉምቱ ፖለቲከኛ የተናገሩትን ማስነበባችን ይታወሳል።

ኦነግም ይባል ኦነግ ሸኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ስማቸው በገሃድ የሚነሳ፣ በግልጽ ተጠያቂ የሚደረጉ፣ ለወንጀሉ ግንባር የሆኑ ድርጅት እነድመሆኑ በሚከሰስበት ጉዳይ ላይ በይፋ ሲሞገት አይታይም። ለኦነግ አመራሮች ቅርብ የሆኑ ሚዲያዎች ቢቢሲና ቪኦኤን ጨምሮ ከተራ የማስተባበል ዜና ባለፈ በሚከሰሱበት ልክ ሲሞግቱዋቸው አይታይም። በዚህም የተነሳ ቀደም ሲል ያነጋገርናቸው ፖለቲከኛ ቢቢሲና ቪኦኤን የድርጅቶች የማስተባበያ ልሳን አድርገው እንደሚቆጥሯቸው መግለጻቸው ይታወሳል።

በየቀበሌው፣ በየሰፈሩ ዱካ እየቀያየሩ ንጽሃንን የሚዘርፉ፣ የሚያገቱ፣ የሚያፍኑና የሚገድሉ አካላት አንዳንዴም ፖለቲካዊ ተልዕኮ አላቸው ብሎ መቀበል እንደማይቻል የሚገልጹ ” ህዝብን ምሬት ውስጥ ለመክተት የተደራጁ ተከፋይ ገዳዮችና አፋኞች ናቸው፣ አለያም የራሳቸውን አደረጃጀት ፈጥረው አፈናና እገታን ስራ ያደረጉ የማፍያ ቁጥቋጦ ናቸው” ይላሉ።


ኢትዮጵያን እያመሳት ያለው የ”ገፊና ጎታች ሤራ” ሲገለጥ

ማንም ይሙት የሚገደለው ሁሉ አማራ፣ ገዳዩ ደግሞ ሸኔ ብቻ እንዲባል ለምን ተፈለገ? የሸኔ የፖለቲካ ፕሮግራምና ዓላማ ምንድነው? ሸኔን በፋይናንስ የሚደጉመው ማነው? ሸኔ ወለጋ ላይ በተለይ ያተኮረው ለምንድነው? ሸኔ ሲገድል የአማራ ተቆርቋሪዎች በምን ግንኙነትና ፍጥነት እየተቀበሉ


ይህ መስል ያጣ፣ ህዝብን እያማረረና ወደ ቁጣ ውስጥ እየከተተ ያለ ጉዳይ ለየትኛውም የህብረተሰብ ክፍል የሚጠቅም ባለመሆኑ ከወዲሁ በርብርብ መፍትሄ ሊበጅለት እንደሚገባ ዜጎች እየጠየቁ ነው። በውይይትና በንግግር የሚፈታውን በዚሁ አግባብ ማስተናገድ፣ በሌላ አግባብ መፍትሄ የሚፈለግለትን ጉዳይም ሃቁን ለህዝብ ይፋ አድርጎ እንዲፈታ ማድረግ ለነገ የማይባል እንደሆነ አሁንም ስጋት የገባቸው እየገለጹ ነው። ከምንም በላይ ግን ሁሉንም ጉዳይ፣ በግለሰብ የተፈጸመን ተግባር ሁሉ መንግስትን ለማቆሸሽ ተግባር መጠቀም መፍትሄ ስለማያመጣ በምስኪኖች ስቃይ ፖለቲካ የሚቆምሩም ራሳቸውን ከጸጸት ሊጠብቁ እንደሚገባ የሚመክሩ አሉ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እንዲሁም ኦፌኮ በተለያዩ ጊዜያት መግለጫ በማውጣት ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ግፍ ይቃወማሉ። የሚከሰሰው ኦነግ ራሱ ድርጊቱን ያወግዛል።

ጃዋር መሐመድ ታህሳስ ቀን 2022 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በወለጋ ዞኖች ውስጥ ባጋጠመው ግጭት ዋነኛ ተሳታፊዎች መንግሥት ‘ሸኔ’ እያለ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የአማራ ታጣቂዎች ናቸው በማለት ተጠያቂ አድርጎ ባወጣው ሪፖርት ላይ ለቢቢሲ አስተያየት ሲሰጥ ”  ተኩስ በማቆም ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር ንግግር መጀመር አለበት፤ በተጨማሪም የፋኖ ሚሊሻዎችን ከኦሮሚያ አስወጥቶ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለስ አለባቸው ፣ አጠቃላይ ብሔራዊ የሰላም ሂደት ብቸኛው መፍትሄ በመሆኑ ይህን ለማሳካት አቅዶ መተግበር ያስፈልጋል” ማለቱ ይታወሳል።

በገሃድ የጎጃም አካባቢ ፋኖ አማራ ክልል ዘልቆ መግባቱ በየትኛውም የተቃዋሚ ሚዲያዎችም ሆነ ፓርቲዎች በገሃድ ሲወገዝ አይሰማም። እስክንድር ነጋ የብሄር ፖለቲካ አቀንቃኝ እንደሆነ ሲጠየቅ ለበርካታ ዓመታት ሲያስተባብል ቢቆይም፣ አሁን በገሃድ የአማራ ህዝባዊ ሃይል ግንባር የአገር ውስጥ አመራር መሆኑ ሲጠቅስ የውጭ አገር የግንባሩ መሪ ሻለቃ ዳዊት እንደሆኑ ማስታወቁ ይታወሳል።

የቀድሞ የእርዳታ ማስተባበሪ ኮሚሽነር የነበሩትና ከርሃብተኞች ገንዘብ ዘርፈው አገር እንደከዱ ቢቢሲና ኤፒ በሰነድ አስደግፈው በወቅቱ ዜና የሰሩባቸው ሻለቃ ዳዊት፣ “ድፍን ወለጋ የአማራ ነው” ሲሉ አስቀድመው መናገራቸው የሚታወስ ነው።

ሰፊ ቁጥር ያለው አማርኛ ተናጋሪ በሁሉም አገሪቱ ተሰራጭቶ ለፍቶና ላቡን አንጠፍጥፎ ሃብት በማፍራት እንደሚኖር የሚገልጹ፣ የአንዳንድ ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስት ነን ባዬችና ለአማራ እንደሚቆረቆሩ የሚናገሩ የሚራምዱት አቋም ሰላማዊውን ህዝብ እንዳይጎዳው ይሰጋሉ። በጥቅልም ዓላማው ኦሮሞና አማራን ማጫረስ እንደሚመስላቸው ይናገራሉ። በጋህድ በተቃውሞ ስም በጅምላ ህዝብን መፈረጅ፣ ማስቀይም፣ ስሜት ውስጥ መክተት መመረጡ የአገሪቱን ፖለቲካ ጡዘት እየጨመረው እንደሆነ በርካቶች ይናገራሉ።

መንግስትን በሰለጠነና በተጠና ፖለቲካዊ ትግል መገዳደልና ማበሻቀጥ እየተቻለ፣ በዘር፣ በሃይማኖትና በጎሳ ላይ ተቸክሎ ልዩነትን ማጋም ጉዳቱ ለጸጸት እንኳን የማይመች እንደሆነ የሚገልጹ ” ህዝብ ትከሻው ብርቱ፣ አብሮነቱ ጠንካራ፣ እምነቱ ጽኑ መሆኑ ረዳ እንጂ እንደሚታሰብው ቢሆን ኖሮ ይህን ጊዜ በጠፋን” ሲሉ ችግሩን ሁሉ ተቋቁሞ በስሜት ለማይነዳው ህዝብ ምስጋናቸውን ያቀርባሉ።

featured
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ደበበ ሰይፉ – የኪነት ፀሐይ
ኢትዮጵያ እና የአይ ኤም ኤፍ ባለሙያዎች በተራዘመ የብድር አቅርቦት ሁለተኛ ግምገማ ላይ ተስማሙ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
FEATURED

የጸረ – ቤተሰቡ የአንዳርጋቸው ጽጌ የፖለቲካ ውርዴ ውርስ፣ ባንዳነትና ክህደት

November 7, 2025
FEATURED

የአስገድዶ መድፈርና የግፍ ወንጀል – ከትግራይ የወጣው አዲስ ሪፖርት ገለልተኛነት?

October 23, 2025
ECONOMY

“የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማየት ሁላችንንም ያብቃን፤ እኔ እንደማይ አምናለሁ፤ ያመነ ከእኔ ጋር ይጓዝ” አብይ

October 8, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2