Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  ማህደር  ባለ ገድሏ ሸዋረገድ ገድሌ
ማህደር

ባለ ገድሏ ሸዋረገድ ገድሌ

Ethioreview newsEthioreview news—November 4, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በታሪክ ውስጥ የአርበኝነት ተጋድሎ ሰፊ ቦታ አለው፤ ምክንያቱም የሀገር ሉዓላዊነት ጉዳይ ነው። አርበኝነት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ግንባር ቀደም ሆኖ የሚጠቀሰው ደግሞ አፍሪካ ውስጥ ሆና ቅኝ ያልተገዛች ነፃ ሀገር መሆኗ ነው። አንዲት አፍሪካዊት ሀገር የአውሮፓን ቅኝ ገዥ በዱር በገደል ተዋግታ ነፃነቷን ስታስጠብቅ ዓለም አቀፍ ገድል መሆኑ ግልጽ ነው። እነሆ እነዚህን አርበኞቻችንን ታሪክ ሲያስታውሳቸው ይኖራል።

በዛሬው ሳምንቱን በታሪክ ዓምዳችን ብዙም ባልተነገረውና ባልተዘመረው የሴቶች የአርበኝነት ተጋድሎ ውስጥ ነጥረው የወጡትን አርበኛ ሸዋረገድ ገድሌን እናስታውሳለን። ከዚያ በፊት ግን እንደተለመደው ሌሎች የዚህ ሳምንት ታሪካዊ ክስተቶችን እናስታውስ።

ከ120 ዓመታት በፊት በዚህ ሳምንት ጥቅምት 19 ቀን 1897 ዓ.ም ደራሲ፣ የታሪክ ተመራማሪ፣ የግብርና ሳይንስ ሊቅ፣ የምጣኔ ሀብት ባለሙያና ፖለቲከኛ የነበሩት ብላቴን ጌታ ማኅተመሥላሴ ወልደመስቀል ተወለዱ።

ከ94 ዓመታት በፊት በዚህ ሳምንት ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም ፒያሳ (አራዳ ጊዮርጊስ) የሚገኘው የዳግማዊ አጼ ምኒልክ መታሰቢያ ሀውልት (ምኒልክ አደባባይ) ተመረቀ። ይህ የሆነው በንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ የንግሥና በዓል ዋዜማ ነበር። በዚሁ ዓመት ጥቅምት 23 ቀን 1923 ዓ.ም አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ሆነው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆኑ።

More stories

ደበበ እሸቱ (1934-2017 ዓ.ም)

August 24, 2025

ጊዜ መስታወቱ!! ተስፋዬ ገብረአብ ማነው?

January 1, 2024

 የዳውሮ ባለውለታ- ያልተነገሩ ትጋቶች

May 22, 2025

ለዋዜማ ሬዲዮ – የህዳሴውን ግድብ ዜናችሁን ላስተካክልላችሁ

August 29, 2023

ከ108 ዓመታት በፊት በዚህ ሳምንት ጥቅምት 23 ቀን 1909 ዓ.ም ደራሲ፣ መምህር፣ ባለቅኔ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ ፖለቲከኛ፣ ገጣሚ … የክብር ዶክተር ከበደ ሚካኤል ተወለዱ።

ከ60 ዓመታት በፊት በዚህ ሳምንት ጥቅምት 23 ቀን 1957 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) ስርጭቱን ጀመረ። ይህ ብሔራዊ ቴሌቭዥን እነሆ በዚህ ዓመት 60ኛ ዓመት ሆነው።

ከ55 ዓመታት በፊት በዚህ ሳምንት ጥቅምት 24 ቀን 1962 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው አንጋፋው ሒልተን ሆቴል ሥራው ተጠናቆ በቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ተመረቀ። የሆቴሉ ዲዛይን የተሰራው በአንድ የአሜሪካ ሥነ ሕንጻ (አርክቴክት) ድርጅት ሲሆን፤ ሆቴሉ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ ዲፕሎማቶች ቁጥራቸው እየጨመረ መምጣትን ተከትሎ የተገነባሠየቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ፕሮጀክት ነው።

ከ117 ዓመታት በፊት በዚህ ሳምንት ጥቅምት 25 ቀን 1900 ዓ.ም ፒያሳ የሚገኘው ታሪካዊው የጣይቱ ሆቴል ግንባታው ተጠናቆ ተመረቀ።

በዝርዝር ወደምናየው የአርበኛ ሸዋረገድ ገድሌ ገድል ስናልፍ፤ ከ75 ዓመታት በፊት በዚህ ሳምንት ጥቅምት 22 ቀን 1942 ዓ.ም የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት በአርበኝነት ተጋድሎ ዘመን የማይሽረው አኩሪ ገድል ከፈፀሙት ኢትዮጵያውያን መካከል አንዷ የነበሩት ታላቋ አርበኛ ክብርት ወይዘሮ ሸዋረገድ ገድሌ አረፉ።

የዓድዋ ሽንፈቷን ለመበቀል ኢጣሊያ በ1928 ዓ.ም ኢትዮጵያን ወረረች። የኢጣሊያ ወራሪ ኃይልም አንዲትም ቀን እንኳን እፎይ ብሎ ሳይቀመጥ ከአምስት ዓመታት እልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ ሌላ የሽንፈት ማቅ ለብሶ ከኢትዮጵያ ምድር ተባረረ። ታዲያ በዚህ አስገራሚና አኩሪ የመስዋዕትነት ጉዞ ውስጥ ደማቅ የጀግንነት ታሪክ ከፃፉና ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ከተጋደሉ እልፍ የኢትዮጵያ ጀግኖች መካከል አንዷ ታላቋ አርበኛ ሸዋረገድ ገድሌ ነበሩ።

አርበኛ ሸዋረገድ ገድሌ የተወለዱት በ1878 ዓ.ም ደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ ነው። የቤተ ክህነት ትምህርት ተምረዋል። ለአቅመ ሔዋን ሲደርሱ ያገቧቸው ባል ብዙም ሳይቆዩ ስለሞቱባቸው ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገብተው ተቀምጠው ቆይተዋል።

በ1888 ዓ.ም በጀግኖቹ ኢትዮጵያውያን ድል የሆነው የኢጣሊያ ጦር ቂሙን ሳይረሳ ሽንፈቱን ሳይዘነጋ ከአርባ ዓመታት በኋላ ዳግመኛ ለብቀላ በተመለሰበት አጋጣሚ በአዲስ አበባ ከተማ በሀገር ተቆርቋሪ ዜጎች መስራችነት «የሀገር ፍቅር ማህበር» ተቋቋመ። በማህበሩ በአባልነት ለመጀመሪያ ጊዜ ከተመዘገቡ ሴቶች መካከልም ጀግናዋ ሸዋረገድ ገድሌ አንዷና ግንባር ቀደም ነበሩ።

ወራሪው የኢጣሊያ ጦር ሀገራችን እንደገባ የመጀመሪያ ተግባሩ ያደረገው ለዘመናት በድል ሲውለበለብ የቆየውን የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በማውረድ የራሱን ባንዲራ መተካትን ነበር።

በወቅቱ ይህን ድርጊት በዓይናቸው የተመለከቱት ሸዋረገድ ግን ወራሪውን ጦር ሳይፈሩና ሳይሳቀቁ «ሀገሬ ተወረረች፤ ተዋረደችም» ሲሉ አምርረውና ጮኸው ማልቀሳቸውን ተያያዙት። ሁኔታቸውን ያዩ የጣሊያን ሹማምንትም የእርሳቸውን ድርጊት እንደ ድፍረት በመቁጠር ለክስ አቀረቧቸው። ሸዋረገድ ግን በተለየ ወኔ ተሞልተው «አዎ አልቅሻለሁ! የሀገሬን መወረርና መዋረድ ያወቅሁት የኛ ሰንደቅ አላማ ወርዶ የእናንተ ሲወለበለብ በማየቴ ነው። ሰው ለእናት ሀገሩ ቢያለቅስ ነውሩ የቱ ላይ ነው?!» ሲሉ እልህ በተሞላበት ሁኔታ መለሱላቸው።

ሸዋረገድ ሀገራቸው በጠላት ጦር ዳግመኛ መወረሯ ከታወቀ ወዲህ «ሕይወቴ ሀገሬ ናት» ሲሉ ለመታገል ቆረጡ። ከወራሪው የጠላት ጦር ጋር ሊፋለምና ደሙን ለሀገሩ ሊገብር ለተዘጋጀው ወገን ያላቸውን ሁሉ ሸጠው ትጥቅ እያደራጁና ስንቅ እያዘጋጁ እንዲሁም ከኢትዮጵያውያን ሴቶችም ቁርጥራጭ ጨርቆችን እያሰባስቡ በጦርነቱ ለሚጎዱ ቁስለኞች እንዲላክ ያደርጉና ይሰጡ ጀመር።

የእሳቸው ድርጊት ግን ለኢጣሊያኖቹ ሰላም አልሰጠም። ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ከመስጠት አልፈው ለክስ እንዲቀርቡ ወሰኑባቸው። ወይዘሮ ሸዋረገድ ለአርበኞች ስንቅ በማቀበላቸው፣ መሣሪያ በመግዛታቸው፣ መረጃ በማሰባሰባቸው፣ መድኃኒት በመላካቸውና ሞራል በመስጠታቸው ምክንያት በተከሰሱ ጊዜም ‹‹ለአርበኞች ስንቅ ማቀበሌ እውነት ነው፤ ይህንንም ያደረግኩት ለሀገሬ ክብር ብዬ ነው። ሰው እንኳን ለሀገሩ … የእናንተ ወይዛዝርት ሀገራቸው ያልሆነቺው ኢትዮጵያን ለመውረር የጣታቸውን ቀለበት ሳይቀር መስጠታቸውን ትናገራላችሁ። እኔም ለሀገሬ የሠራሁት ሲያንሰኝ እንጂ አይበዛብኝም!›› በማለት ስለፈፀሙት ድርጊት ሁሉ ኩራት እንደሚሰማቸውና ይህንንም ያደረጉት ለሀገራቸው ክብር ሲሉ እንደሆነ በድፍረት ተናገሩ።

አርበኛ ሸዋረገድ ከሚጠቀሱላቸው ሥራዎቻቸው አንዱ ለቀይ መስቀል ማህበር ያደርጉት የነበረው ድጋፍ ነው። በጦርነቱ ዋዜማ፣ በ1927 ዓ.ም ለተቋቋመው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ንብረታቸውን ሸጠው በማስረከብ ሀገር ወዳድነታቸውን አስከብረዋል። ከተከሰሱባቸውና ‹‹ወንጀል›› ተደርገው ከተቆጠሩባቸው ድርጊቶች መካከል አንዱ ይኸው ለቀይ መስቀል ያደርጉት የነበረው ድጋፍ ነው። እሥር ቤት በገቡ ጊዜም የፋሺስት አስተዳደር ባለሥልጣናት ‹‹ቀይ መስቀልንና ሀገር ፍቅር ማህበርን ትረጃለሽ›› ብለው ክስ አቅርበውባቸው ነበር። የጠላቶቻቸውን ክስ ከቁብ ያልቆጠሩት አርበኛ ሸዋረገድ ግን ‹‹ስለ ነፃነት ከሞቀ ቤታቸው ወጥተው የሌሊት ቁርና የቀን ሐሩር ከሚገርፋቸው የሀገሬ አርበኞች ጎን ተሰልፌ ጠላቴን መውጋቴ ቀርቶ የረሃብና የጥም መድኃኒት እያዘጋጀሁ መላኬ ቁም ነገር ሆኖ ነው የተጠየቅሁበት? እኔ ይህን ባለማድረጌና ለሀገርም ባልቆረቆር፤ እንኳን እነሱ እናንተም እንደምትታዘቡኝ ይሰማኛል›› በማለት እጅግ አስደናቂ የሆነ የሀገር ፍቅር የተሞላበትና ቆራጥነት የተቀላቀለበት መልስ ሰጥተዋል።

አርበኛ ሸዋረገድ ከቁሳቁስ ርዳታው ጎን ለጎን ለአርበኞቹ የመረጃ ምንጭም ነበሩ። በከተማው የሚገኙ የጠላት መረጃዎችን በማሰባሰብና ወደ አርበኞች በምሥጢር በመላክ አርበኞች እንዲጠቀሙባቸው አድርገዋል። ይህ ተግባራቸውም ከወቅቱ ‹‹የውስጥ አርበኞች›› መካከል አንዷና ዋነኛዋ ሆነው እንዲቆጠሩ አስችሏቸዋል። ሸዋረገድ ለኢጣሊያ ሰዎች ወዳጅ በመምሰል ለኢትዮጵያውያን አርበኞች መረጃ ይሰጡ ስለነበር የኢጣሊያ ፋሺስቶች ሸዋረገድ እውነተኛ ወዳጃቸው መስለዋቸው ‹‹አርበኞችን ከረዳሽ እኛን አትወጂንም ማለት ነው?›› ብለው ሲጠይቋቸው ‹‹አዎ አልወዳችሁም! ማነው የሀገሩን ደመኛ የሚወደው?›› በማለት ቁርጥ ያለ ምላሽ ሰጥተዋቸዋል።

አርበኛዋ ሸዋረገድ በሚፈፅሟቸው በርካታ ፀረ ፋሺስት እንቅስቃሴዎች ምክንያት ጥርስ የነከሱባቸው የፋሺስት ኢጣሊያ አስተዳደር ባለሥልጣናት ሕይወታቸውን በእስር እንዲገፉና ቆይቶም ሞት እንዲፈረድባቸው ወስነው ነበር። ሆኖም አዚናራ ወደምትባልና በሰሜናዊ ምዕራብ ኢጣሊያ ወደምትገኝ ደሴት ታስረው እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ፍርዱ ወደ እስራት ብቻ በመቀየሩ ምክንያት የእስር ዘመናቸውን በደሴቲቱ እንዲገፉ ተወሰነባቸው።

ጀግናዋ አርበኛ ሸዋረገድ ግን የቦታ ለውጥና ርቀት አልበገራቸውም። በጠላት ሀገር ሆነውም ጽናታቸው አልተሰበረም፤ ወኔያቸውም አልተሰለበም። እንዲያውም ወኔያቸውን አጠናክረው ትግላቸውን ቀጠሉ። በእስር ቤቱ የሚቀርብላቸውን ምግብ በአሳሪዎቻቸው ፊት በመድፋትና ጦማቸውን ውለው በማደርም ተቃውሞ ማድረግ ጀመሩ። ከአንድ ዓመት የእስራት ቆይታ በኋላ ከእስራት እንዲለቀቁ በመወሰኑም ወደ አዲስ አበባ የመግባት እድል አገኙ። በወቅቱ ወደ አዲስ አበባ ሲገቡም ሕዝቡ …

‹‹ የዘበኛ ሱሪ ካኪና ገምባሌ፣

እንኳን ደህና መጣሽ ሸዋረገድ ገድሌ ››

ብሎ በመግጠም ተቀበላቸው። በተለይ በጅቡቲ የነበረ አንድ ኢትዮጵያዊ የሰጣቸውን ‹‹የይሁዳ አንበሳ›› የሚል ጽሑፍና ዓርማ ያለበትን ወረቀት ከንጉሰ ነገሥቱ የተላከ የሚመስል መልዕክት እየፃፉ አርበኞች ተጋድሎ ወደሚደርጉባቸው ልዩ ልዩ ስፍራዎች በመላክ አርበኞቹ እንዲበረታቱ አድርገውበታል።

አዲስ ዓለም አካባቢ ይገኝ የነበረው የፋሺስት አጣሊያ ምሽግ ኅዳር 5 ቀን 1933 ዓ.ም ሲሰበር ጠቃሚ መረጃዎችን ለአርበኞች በማሰባሰብና በርካታ እቅዶችን በመንደፍ ታላቁን ድርሻ የተወጡት ታላቋ አርበኛ ሸዋረገድ ነበሩ። ምሽጉ ከተሰበረም በኋላ ደጀን መሆኑን ትተው ወደ ውጊያ ለመግባት በመወሰናቸው ከሻለቃ በቀለ ወያ ጦር ጋር ተሰልፈው ጠላትን ተፋልመዋል። በመቀጠልም ወደ ወሊሶ በመሄድ ከደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ጦር ጋር ሆነው ተዋግተዋል። በጦርነቱ የአራት ሰዓታት ውጊያ ላይ ጠላት በጣለው ድንገተኛ አደጋ ከታላቅ ተጋድሎ በኋላ የተማረኩት አርበኛ ሸዋረገድ፣ በድጋሚ በፋሺስት ኢጣሊያ ወታደሮች እጅ በመውደቃቸው የፊጥኝ ታስረው ወደ እስር ቤት ተወረወሩ። የሸዋረገድን ጀግንነት የተመለከተው ሕዝብም …

‹‹ የምታስፎክር ሰንጋ ገለሌ፣

በጦር መካከል ሳይሆኑ አያሌ፣

በጥይት ገዳይ ነጭ ብር ገድሌ፣

የሴት ወንድ ናት ሸዋረገድ ገድሌ ››

ብሎ ጀግንነታቸውን በማድነቅ አወድሷቸዋል። የጀግኖች አርበኞች ትግል ተጠናክሮ የጠላት ጦር በመጣበት እግሩ በታላቅ ውርደትና በአሳፋሪ ሽንፈት በ1933 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ሲባረር ታላቋ አርበኛ ሸዋረገድ ገድሌም ነፃ ሆነው ተፈቱ። ከዚህ በኋላ ሕይወትን በነፃነት ማጣጣም ለእኚህ ታላቅ ሴት ትልቅ ትርጉም ነበረው። ቀድሞ የጀመሩትን አርበኞችን የመርዳት የበጎ አድራጎት ሥራቸውን አጠናክረው ቀጠሉበት። በንግዱ ዘርፍ ተሰማርተውም በርካታ ሰዎችን እንደጠቀሙም ይነገርላቸዋል።

ታላቋ አርበኛ ክብርት ወይዘሮ ሸዋረገድ ገድሌ ታዋቂ ያደረጋቸው የአርበኝነት ሥራቸው ሆነ እንጂ ከመጀመሪያዎቹ የባንክ ተጠቃሚዎች፣ የአክስዮን ገዥዎች፣ የፋብሪካ ተካፋዮች መካከል አንዷ ነበሩ። በእነዚህ የንግድ ሥራዎቻቸውም በርካታ ሰዎችን በተለይ ደግሞ ሴቶችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደቻሉ ታሪካቸው ያስረዳል። በሃይማኖታቸውም ጠንካራ እንደነበሩ ታሪካቸው የሚናገረው አርበኛዋ፣ የጉለሌ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንንም ያስተከሉት እርሳቸው ናቸው።

ታላቋ አርበኛ ክብርት ወይዘሮ ሸዋረገድ ገድሌ ለወቅቱ አርበኞች በመሳሪያ፣ በስንቅና በመረጃ ያደርጉላቸው ከነበረው ድጋፍ በተጨማሪ ከአንዳንዶቹ ጋር በጦር ሜዳ አብረው ተሰልፈው ተዋግተዋል። ለአብነት ያህልም ከጀግኖቹ አርበኞች ደጃዝማች በቀለ ወያ እና ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ጋር ተሰልፈው ከጠላት ጦር ጋር ተፋልመዋል። ለታዋቂው አርበኛ ሌተናል ጀኔራል ጃገማ ኬሎም ልዩ አክብሮት ነበራቸው። ከዚህ ጋር በተያያዘም ሊጠቀስ የሚገባው አንድ አጋጣሚ አለ።

ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ከእንግሊዝ ተመልሰው ዙፋናቸው ላይ ቢቀመጡም ጎንደርና ጅማ ከጠላት ጦር አልተለቀቁም ነበር። ‹‹መጀመሪያ የቅርቡን እናስለቅቅ›› ተብሎ ወደ ጅማ ሲሄዱ የፋሺስት ጦር የጊቤን ድልድይ ቆርጦ መከላከል ጀመረ። በዚህ ጊዜ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ጃገማን ያውቋቸው ነበርና ለንጉሠ ነገሥቱ ‹‹ለጃገማ ትዕዛዝ ቢሰጡልኝ በአምቦ መንገድ ሄዶ በኋላ በኩል ይቆርጥልኛል›› በማለታቸው ጃገማ ከደጃዝማችች ገረሱ ጋር እንዲዘምቱ በደብዳቤ ታዘዙ።

አርበኛ ሸዋረገድ ገድሌ ለንጉሠ ነገሥቱ ‹‹ጃንሆይ ይህ ልጅ ገና ሕፃንና የሚያምር ልጅ ነው፤ እንዴት ከሞት ወደ ሞት ይልኩታል? ያሰናብቱት! ጦሩን ቢያዩለትም መልካም ነው›› ብለው ስለተናገሩ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ‹‹እውነት ነው፤ ተሣሥተናል፤ እናያለን፤ ጦርህን መጥተን እናያለን ተዘጋጅተህ ጠብቅ፤ ፉከራም ታሰማለህ›› ብለው አዘዙ። ንጉሠ ነገሥቱም የጀግናውን ጦር ጎብኝተው ከጃገማ ጋር ምሳ በሉ። ከዚያም ጃገማ አዲስ አበባ መጥተው ከንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ሽልማት (25ሺ ብር፣ የወርቅ ሰዓት እና ሙሉ ገበርዲን ሱፍ) ተቀበሉ። ከዚያም ጃገማ ወደ ደጃዝማች ገረሱ ዘንድ ዘምተውና የለመዱትን ጀብድ ፈፅመው በቦታው የነበረውን የፋሺስት ጦር ዋና አዛዥና ሌሎች መኮንኖችን ማርከው ጦርነቱንም በድል ፈጸሙ።

በመጨረሻም ግሼን ማርያም ሄደው ሥጋ ወደሙን ተቀብለው፤ ከዚያም ወደ ላሊበላ ተጉዘውና ተሳልመው፤ የመጨረሻቸው መሆኑን እየተናገሩ ጥቅምት 22 ቀን 1942 ዓም አረፉ። የአርበኛ ሸዋረገድ ገድሌ የመሞታቸው ዜና እንደተሰማ ሕዝቡ እንዲህ ብሎ አንጎራጉሮላቸው ነበር።

‹‹ እናንት ወጥ ቤቶች በርበሬ ቀንጥሱ፣

እናንት ሥጋ ቤቶች ሰንጋውን ምረጡ፣

ሸዋረገድ ገድሌ ለገና ሲመጡ።

ቤተሰቧ ሰፊ ገናና ጥምቀት፣

ሸዋረገድ ገድሌ እንደምን ትሙት። ››

ታላቋ አርበኛ ሸዋረገድ ገድሌ የአብራካቸው ክፋይ የሆነ ልጅ አላፈሩም። የልጅ መካን ቢሆኑም የአኩሪ ታሪክ እናት በመሆናቸው ስማቸው በጀግንነት ሕያው ሆኖ እነሆ ሲዘከር ይኖራል።

ዋለልኝ አየለ

አዲስ ዘመን ጥቅምት 24 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
Towards a fairer world
የሰነድ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
Events

የመደመር መንግሥት አዕማዶች – የመጽሐፍ ዳሰሳ

October 8, 2025
ማህደር

የሦስት ሊቃውንት የአሻራ ቅብብሎሽ

October 5, 2025
ማህደር

“ኦሮሞ ‘ፈጣሪ ጥቁር ነው’ ይላል” የዋቄፈና እምነት

October 4, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2