የኮቪድ ወረርሽኘን ከዓመታት በፊት የተነበየው ራሱን ተንባይ (ሳይኪክ) ብሎ የሚጠራው ግለሰብ በ2025 አለም ከባባድ ቀውሶችን እንደምታስተናግድ ተንብዮዋል፡፡
ነዋሪነቱን በለንደን ያደረገው ኒኮላስ አውጁላ የተባለው የ38 ዓመቱ “የሂፕኖቴራፒ” ባለሙያ አመቱ በአለም ላይ ርህራሄ የጎደለበት ይሆናል ብሏል።
“የሶስተኛው የዓለም ጦርነት ከፍተኛ ስጋትን ጨምሮ በሃይማኖት እና በብሔርተኝነት ስም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ አሰቃቂ ድርጊቶችን እና ጥቃቶችን እንመለከታለን” ሲል ትንቢቱን አስቀምጧል።
2024 ከመግባቱ በፊት የትራምፕን አሸነፊነት ቀድሞ መተንበይ የቻለው ግለሰብ፤ ራዕዮቹን መቆጣጠር እንደማይችል እና ተመልክቸዋለሁ ባለው ራዕይ መሰረት በ2025 አመት አጋማሽ የሶስተኛ የአለም ጦርነት ሊከሰት ይችላል ነው ያለው፡፡
ደይሊ ሜይል ባወጣው ዘገባ የቅሪተ አካል ነዳጆች አጠቃቃም ማደግ የባህር ከፍታ መጨመር፣ ከባድ ዝናብ እና ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅን ጨምሮ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ በተለያዩ የአለም ክፍሎች የተፈጥሮ አደጋ በብዛት ሊከሰት እንደሚችል ማስጠንቀቁን አስነብቧል፡፡
በተጨማሪም ሰደድ እሳትን ጨምሮ በቅርቡ በአሜሪካ በሰሜን ካሮላይና የተከሰተው አውሎ ንፋስ ፣ የደን ቃጠሎ እና ሌሎችም የተፈጥሮ አደጋዎች በአመቱ ለሰው ልጆች እና ለእንስሳት ህይወትን ከባድ እንደሚያደርግ ጠቅሷል፡፡
ወጣቱ ከ17 አመቱ ጀምሮ ስለ ወደፊቱ የመጀመሪያ ራዕይ ከተመለከተ በኋላ ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት ትምህርትን አቁሞ ወደፊቱን ሲተነብይ እንደቆየ ተነግሮለታል፡፡
via – alaine

