Skip to content
  Wednesday 10 June 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የትግራይ ህዝብ የሰላም፣የህልውናው እና ደህንነቱ ዘብ እራሱ ህዝቡ ነው -ዶ/ር አብርሃም በላይ

    May 29, 20210

    በሰሜን ወሎ በኩል ሰርጎ የገባው አሸባሪ በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን እርምጃ ተወሰደበት

    September 4, 20210

    Ethiopian Envoy Briefs Sudan Based Media On GERD

    July 4, 20210

    በአዳማ ከተማ የምርጫ ሂደቱን ለማወክ በመሞከርና በምርጫ ጣቢያ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት የተከሰሱ ተቀጡ

    June 21, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1875
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ልጆቻቸው መቀለ ዩኒቨርስቲ የቀሩባቸው ወላጆች የተመድ ፊት እያነቡ ነው “ልጆቻችንን አስለቅቁልን”

    July 23, 20210

    መከላከያ በኦሮሚያና አማራ ክልል የማጽዳት ስራ እንደቀረው አስታወቀ፤ አማራ ክልል መዋቅሩን እያጠራ ነው፤

    September 1, 20230

    “ሁሉንም ያማከለ ዴሞክራሲያዊ ስረዓተ መንግስት ካልተመሰረተ ወቅታዊና ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ ችግሮች ለመፍታት አስቸጋሪ ነው”

    April 17, 20210

    “በተለመደው አሰራር ማስቀጠል የምንችለው ድህነትን ብቻ ነው” ሽመልስ አብዲሳ

    June 3, 20220

    “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች?”

    March 9, 20220
    Prev Next Showing 1 Of 1500
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  FEATURED  
“የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግስት አንድም ብር አበድሮ አያውቅም” ባንኩ ሪፓርተር ያተመውን የተዛባና የተዛነፈ ዜና እንዲርያም አሳሰበ
FEATURED


“የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግስት አንድም ብር አበድሮ አያውቅም” ባንኩ ሪፓርተር ያተመውን የተዛባና የተዛነፈ ዜና እንዲርያም አሳሰበ

Ethioreview newsEthioreview news—April 7, 20250
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

“የተዛባ ዜና” ማቅረቡን በመዘርዘር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሪፖርተር ጋዜጣን ነቅፎ ማስተባበያ እንዲያወጣ አሳሰበ፤ ባንኩ ለመንግስት አንድም ብር እንዳላበደረ በዝርዝር ያብራራበትን መግለጫ በይፋዊ ገጹ ይፋ አድርጓል። ይህ እስከታተመ ድረስ ሪፖርተር በገጹ ማስተባበያ አልሰጠም፤

በሪፓርተር ጋዜጣ የዕሁድ ዕትም ቅጽ 30 ቁጥር 2602 መጋቢት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ታትሞ የተሰራጨው ዜና ከርዕሱ ጀምሮ ለቋሚ ኮሚቴው ከቀረበው ሪፖርትም ሆነ ከእውነታው የተለየና የተዛባ መረጃ እንደሆነ ባንኩ አምልክቷል።

“መንግስት ከኢትዮዽያ ንግድ ባንክ የተበደረው አንድ ትሪሊዮን ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ” በሚል ርዕስ “ተቀናብሮ የቀረበው  የተዛባና የተሳሳተ” የተባለው ዘገባ እንዲታረም ያሳሰበው ባንኩ፣ እርምት ለተየቀበትና “የተዛባ” ያለበትን ምክንያት አብራርቷል።

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮዽያ ንግድ ባንክ በዚህ በጀት ዓመትም ሆነ ከዚያ በፊት አንድም ብር ለመንግስት በቀጥታ አበድሮ አያውቅም። መንግስት ከሀገር ውስጥ የንግድ ባንኮች (በብሔራዊ ባንክ በኩል ለሽያጭ ከሚቀርበው የግምጃ ቤት ሰነድ ግዢ ውጪ) በቀጥታ የመበደር አሰራርም ሆነ ልምድ የለውም።

More stories

የፋኖ ሃይሎች የ[አንድነት ዘመቻ] እና ብ/ጀነራል ምግበይ ሃይለ

March 24, 2025

ፌስቡክ ትግራይ ተጀምሮ አማራና አፋርን ጭምር ባወደመው ጦርነት ሚና ነበረው በሚል ክሱ ኬንያ እንዲታይ ተበየነ

April 3, 2025

“ሻምቡ፣ ወለንጪቲ ዙሪያ፣ ፊንጫና አንገር ጉቲን ሂዱና ህዝብ አነጋግሩ፣ ቢያንስ ሃምሳ ከመቶ ወደ እውነት ትደርሳላችሁ”

November 27, 2024

ምርጫ ቦርድ ትህነግን ሰረዘ፤ ትህነግ የሚባል ፓርቲ ከአሁን በሁዋላ የለም

May 14, 2025

ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ የኢትዮዽያ ንግድ ባንክ በዚህ በተገባደደው ሳምንት ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የስምንት ወራት የስራ አፈጻጸም ማቅረባችንን ተንተርሶ በሪፓርተር ጋዜጣ የዕሁድ ዕትም ቅጽ 30 ቁጥር 2602 መጋቢት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ታትሞ የተሰራጨው ዜና ከርዕሱ ጀምሮ ለቋሚ ኮሚቴው ከቀረበው ሪፖርትም ሆነ ከእውነታው የተለየና የተዛባ መረጃ ሆኖ አግኝተነዋል። ለምሳሌ በጋዜጣው ዕትም ርዕስ ላይ የተገለጸውና “̋መንግስት ከኢትዮዽያ ንግድ ባንክ የተበደረው አንድ ትሪሊየን ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ” የተባለው ዜና ከእውነት የራቀ ከመሆኑም በላይ በሪፖርቱም ፈጽሞ እንደዚህ አይነት ኃሳብ አልቀረበም።

“ባለፉት 15 ዓመታት 92 በመቶ ብድር የተሰጠው ለመንግስት ተቋማት ነው ተብሏል” የሚለው ኃሳብም ስህተት ነው። የቀረበው ሪፖርት በግልጽ  እንደሚያሳየው ከለውጡ በፊት የባንካችን የብድር ትኩረት ለመንግስት ተቋማት እንደነበርና ይህ ብድር አድጎ በመጨረሻም ከአምስት ዓመት በፊት እስከ 92% እንደደረሰ እና ከአምስት ዓመት ወዲህ ግን ያ አሰራር የተቀየረና ቅድሚያ ለግል ተበዳሪዎች እየተሰጠ በመሆኑ ፤ ለምሳሌ ያህል በዚህ ስምንት ወራት ከተሰጠው ጠቅላላ ብር 264.65 ቢሊዮን ብድር ውስጥ ከ88% በላይ ብድር የተሰጠው ለግሉ ዘርፍ በመሆኑ አሁን ያለው የመንግስት ተቋማት የብድር ክምችት ድርሻ ወደ 72% ዝቅ ማለቱን ተመላክቷል።

በመሰረቱ ይህ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ዕዳ መንግስት በቀጥታ ራሱ የተበደረው የመንግስት ዕዳ ሳይሆን የተለያዩ እንደ ባንካችን ያሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የተበደሩት ዕዳ ነው። መንግስት በእነኚህ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ የባለቤትነት ድርሻ ቢኖረውም እነዚህ ተቋማት ከአስፈፃሚው መንግስት የተለዩና የራሳቸው ካፒታል ያላቸው፣ እንደ ማንኛውም ድርጅት ንግድ ፍቃድ አውጥተው የሚነግዱ፣ በድርጅታቸው ስም ገንዘብ የሚበደሩ፣ ሊያተርፉም ሆነ ሊከስሩ የሚችሉ፣ ለትርፍ የተቋቋሙ የልማት ድርጅቶች ሲሆኑ ብድሮቹንም የወሰዱት ለራሳቸው ፕሮጀክቶች በመሆኑ ለእነዚህ ተቋማት የተሰጠውን ብድር የመንግስት ብድር ተደርጎ መወሰዱ ስህተት ነው። በሀገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር መሰረት መንግስት ማንኛውም ዓይነት የአጭርም ሆነ የረጅም ግዜ የገንዘብ ፍላጎቱን በሕግ በተቀመጠው አሰራርና ምንጭ ያሟላል እንጂ ከሀገር ውስጥ የንግድ ባንኮች በቀጥታ ብድር የሚወስድበት አግባብ የለም።


ትክክለኛው እውነታ ይህ ሆኖ እያለ አንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን ዕዳውን መንግስት በቀጥታ የተበደረው ዕዳ እንደሆነ አድርገው በሪፖርተር ጋዜጣም ሆነ ጋዜጣውን ተከትለው በወጡ አንዳንድ የሚዲያ አካላትም መረጃውን በተዛባና በተሳሳተ መልኩ መዘገባቸው ከባንካችን መግለጫ አውድ ውጭ የቀረበ ከመሆኑም በላይ የጋዜጣው ርዕስ በውስጡ ከተጻፉት ኃሳቦች ጋርም ያልተጣጣመ መሆኑ አንባቢያንን ግራ ሊያጋባ እንደሚችል ስለሰጋን እውነታውን ለማሳወቅ ተገደናል።

በጋዜጣው በጉልህ ከተገለጸው በተቃራኒ መንግስት የልማት ድርጅቶች ከባንካችን የተበደሩትንና ለበርካታ ዓመታት ሳይከፍሉ የቆዩትን ከፍተኛ የብድር ገንዘብ በባንካችን ላይ የደቀነውን አደጋ በመገንዘብ የሚከተሉትን እርምጃዎች በመውስድ ባንካችንን ከውድቀት ታድጎታል።

1ኛ. የልማት ድርጅቶቹ ከባንካችን ብድሩን የሚወስዱበት አሰራር አመላለሱን የሚያረጋግጥ ስላልነበረ ይህ አሰራር ሙሉ በሙሉ እንዲቀርና ባንካችን የውሳኔ ነጻነት እንዲኖረው ለመንግስት ተቋማትም ቢሆን አዋጭ የንግድ ኃሳብ ለሚያቀርቡና ባንካችን ስለአመላለሱ እርግጠኛ ለሆነባቸው ብቻ ብድር እንዲሰጥ አቅጣጫ የተቀመጠው ከ5 ዓመት በፊት ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን ቅድሚያ ለግል ተበዳሪዎች እንዲሰጥ እና የመንግስት የልማት ድርጅቶችም  ቀድመው የጀመሩትን ፕሮጀክቶች ሳይጨርሱ ሌላ እንዳይጀምሩ ስለተደረገ ከ5 ዓመት በፊት 92% ደርሶ የነበረው የመንግስት ተቋማት አጠቃላይ የብድር ድርሻ ወደ 72% በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝቅ ማለቱ እና የግሉ ተበዳሪዎች ድርሻ ደግሞ ከ8% ወደ 28% በፍጥነት ማደጉ ከፍተኛ ስኬት ሆኖ የቀረበና አንባቢያን ሊያውቁት የሚገባው ጥሬ ሀቅ ነው።


2ኛ. የልማት ድርጅቶቹ በወቅቱ መመለስ ያልቻሉትን ዕዳ በተመለከተ ደግሞ፡-
ሀ. መጀመሪያ የመንግስት ዕዳ እና ኃብት አስተዳዳሪ ድርጅት በማቋቋም እዳዎቹን እንዲከፍል ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል። በዚህ ጥረትም ከብር 42.4 ቢሊዮን በላይ እንዲከፈል ተደርጓል።
ለ. ችግሩ በዕዳና ሀብት አስተዳደር ድርጅት ጥረትም ሊፈታ እንደማይችል በመረጋገጡ በዚህ የበጀት ዓመት መጀመሪያ ላይ አጠቃላይ የአከፋፈል ችግር የገጠመው የመንግስት የልማት ድርጅቶች የብር 845.3 ቢሊዮን ዕዳ ተሰባስቦ ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር እንዲዞር እና በየዓመቱ በጀት ተይዞለት እና በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲከፈል ለዚህም ተመጣጣኝ የመንግስት ቦንድ ለባንካችን እንዲሰጥ በፓርላማ ጭምር በማጸደቅ ኃላፊነት የሚሰማውና ቆራጥ መንግስት ብቻ የሚፈጽመው ታሪክ በመስራት ባንካችንን ከውድቀት ኢኮኖሚያችንንም ከትልቅ አደጋ ያዳነ እርምጃ በመውሰዱ መንግስታችንን እጅግ በጣም አመስግነናል፤ አሁንም እጅግ በጣም እናመሰግናለን። ከዚሁ ከተዛወረው ዕዳ ላይ ደግሞ በስምምነቱ መሰረት የመጀመሪያ የግማሽ ዓመት ወለድ በጥር ወር መጀመሪያ ላይ በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ብር 38 ቢሊዮን ለባንካችን ተከፍሏል። ስለዚህ መንግስት ባንካችንን ለማዳን ሲል ከልማት ድርጅቶች ተቀብሎ መክፈል ከጀመረው ዕዳ ውጪ የተበደረው ምንም ገንዘብ እንደሌለ ለሕዝባችን ማሳወቅ እንፈልጋለን።

3ኛ. መንግስት ከልማት ድርጅቶች ከተረከበው ከፍተኛ ዕዳ በተጨማሪ ባንካችንን ለማጠናከር የብር 54.7 ቢሊዮን የካፒታል ጭማሪ በማድረግ ከላይ ከተገለጸው የድርጅቶች ዕዳ ጋር ተደምሮ ብር 900 ቢሊዮን የመንግስት ቦንድ እንዲሰጠን በማድረጉም ባንካችንን ሊገጥሙት የሚችሉትን የፋይናንሻል ስጋቶችን መቋቋም ብቻ ሳይሆን ጠንካራ እና ተወዳዳሪ ባንክ እንዲሆን ረድቶታል።

4ኛ. መንግስት ባንካችንን የበለጠ ለማጠናከር ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር ላለፉት አምስት ዓመታት ጥልቅ ሪፎርም እንድናደርግ ከፍተኛ ድጋፍ እና አመራር የሰጠን ሲሆን የባንካችን ካፒታል የበለጠ እንዲጠናከርና የውጪ ምንዛሬ ፍላጎታችንን ለማሟላት ያለመ 650 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የካፒታል ማሳደጊያ ድጋፍ እንድናገኝ በማድረጉ ባንካችንን የበለጠ የሚያገዝፈው እና የማይበገር ጠንካራ ተወዳዳሪ የሚያደርገው የመንግስታችን ልዩ ድጋፍ በመሆኑ ባንካችን አሁንም አብዝቶ ያመሰግናል።

እንግዲህ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ በስብሰባው ላይ የቀረቡትና ሕዝባችን ሊያውቃቸው የሚገቡ ብዙ መልካም ዜናዎች እያሉ ያለመታደል ሆኖ አሉታዊ ዜና የመናፈቅ ችግር ጎልቶ በታየበት አኳኋን ሪፖርተርም ሆነ ሌሎች ጥቂት ሚዲያዎች የባንካችንን እጅግ በጣም አንጸባራቂ የስምንት ወራት አፈጻጸም ላይ ጥላሸት ለመቀባት መሞከራቸው አሳዛኝ ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል።
 
ይልቁንም ሕዝባችን ቢያውቀው የሚጠቅመው ባንካችን በስምንቱ ወራት አፈጻጸም በሁሉም ቁልፍ መለኪያዎች እጅግ በጣም የላቀና ከምንግዜውም እጅግ በጣም ከፍ ያለ ውጤት ማስመዝገቡን ነበር። ለምሳሌ ያህል፦

1.  በቁጠባ  (Deposit)
  በ8 ወራት ብቻ ብር 367 ቢሊዮን ማሰባሰብ መቻሉ፤ የዚህም ውጤት ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ሲነጻጸር 344% በላይ ዕድገት መሆኑ፣
  የባንካችን አጠቃላይ ተቀማጭ ብር 1.54 ትሪሊዮን በላይ መድረሱ፤ በዚህም የባንካችን የገበያ ድርሻ የመቀነስ ጉዞውን ቀይሮ በ2.2% በማደግ ወደ  49.3% ከፍ ማለቱ፣
2.  ብድር
  በ8 ወራት ብቻ ብር 149.2 ቢሊዮን መሰብሰቡ፤ ይህም ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲወዳደር የ66.8% ዕድገት ማስመዝገቡ ፣
  በዚሁ ጊዜ ውስጥ አዲስ የተለቀቀ ብድር ብር 264.7 ቢሊዮን መሆኑ፤ ይኸውም ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ82.4% ዕድገት ያስመዘገበ መሆኑ፤ ከተለቀቀው አዲስ ብድር ውስጥ ከ88.2% በላይ ለግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ የተሰጠ መሆኑ፣
  የባንካችን አጠቃላይ ብድር ከፍተኛ ዕድገት ያስመዘገበ በመሆኑ የባንካችን የብድር የገበያ ድርሻ የመቀነስ አቅጣጫውን ቀይሮ እ.ኤ.አ. ጁን 2024 ከነበረው 42.8% ከፍተኛ ዕድገት  በማሳየት 51.7% ከፍ ማለቱ፣
  የባንካችን የተበላሹ ብድሮች ምጣኔ አምና በተመሳሳይ ጊዜ ከነበረው የ2.7% ወደ 2.3% ዝቅ ማለቱ፤
3.  በውጪ ምንዛሪ
–  ባንካችን በ8 ወራት አፈጻጸሙ 2.45 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማሰባሰቡ፤ ይህም ግኝት ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ16.7% እድገት የነበረው መሆኑ፣
–  በተለይም ከግል ኃዋላ እና ከሸቀጥ ወጪ ንግድ የተገኘው የውጪ ምንዛሪ እንደቅደም ተከተሉ የ52.2% እና የ58% ከፍተኛ እድገት ማስመዝገብ መቻላቸው፣
–  ባንካችን በ8 ወራት ውስጥ አጠቃላይ ለገቢ ንግዱ የከፈለው የውጪ ምንዛሪ መጠን 5.14 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር መድረሱ እና ከዚህም ውስጥ ለግሉ ሴክተር የተከፈለው 1.22 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ከአምና ተመሳሳይ ወቅቶች ጋር ሲነፃፀር የ58% ከፍተኛ እድገት ማስመዝገቡ መልካም ስኬት ነው፡፡
4.  ካፒታል
የባንካችን አጠቃላይ ካፒታል ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ሲወዳደር የ105% ዕድገት በማሳየት ብር 132 ቢሊዮን መድረሱ፤
5.  አጠቃላይ ሀብት
የባንካችን አጠቃላይ ሀብት በስምንት ወራት በብር 641.7 ቢሊዮን በማደግ ብር 2.07 ትሪሊዮን መድረሱ፤ በዚህ የ44.8% ከፍተኛ ዕድገት ማስመዝገብ በመቻሉ በሀብት የነበረን የገበያ ድርሻ እ.ኤ.አ. በጁን 2024 ከነበረው 43.7% ከፍተኛ ዕድገት በማስመዝገብ 50.4% መድረስ መቻሉ፤
6.  አጠቃላይ ገቢና ወጪ
  በ8 ወራት ባንካችን በሁሉም ዘርፍ ከፍተኛ የገቢ ዕድገት ያስመዘገበ ሲሆን አጠቃላይ ገቢውም ብር 109 ቢሊዮን መድረሱ፤ ይኸውም ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር  ሲወዳደር  የ26 % ዕድገት ማስመዝገቡ ፣
  ባንካችን ጥብቅ የወጪ ቅነሳ ፕሮግራም ሲከተል የነበረና ከፍተኛ የተበላሹ ብድሮች ቅነሳ በማድረጉ ምንም እንኳን በማክሮ ኢኮኖሚው ደረጃ ብዙ ወጪ  ጨማሪ ምክንያቶች ቢኖሩም ባንካችን ከመደበኛ የስራ እንቅስቃሴው ያስመዘገበው የወጪ ዕድገት የ2.6 በመቶ ብቻ በመሆኑ አጠቃላይ የመደበኛ ኦፕሬሽን ወጪ ብር 76.7 ቢሊዮን ብቻ መሆኑ፤
7.  መደበኛ ያልተጣራ ትርፍ
  ባንካችን በ8 ወራት ብር 32.6 ቢሊዮን ያልተጣራ ትርፍ ከመደበኛ ኦፕሬሽን ማግኘት መቻሉ እና ይኸም አፈጻጸም ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ170.5% ዕድገት ያሳየ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት ዓመቱን በሙሉ ተመዝግቦ ከሚያውቀው ትልቁ ትርፍም ከፍተኛ ብልጫ ያሳየ መሆኑ፣
8.  የዲጂታል ግብይት
  ባንካችን በ8 ወራት በዲጂታል ቻናሎቹ ብቻ ከብር 7.7 ትሪሊዮን በላይ ማንቀሳቀሱ፤ አጠቃላይ የግብይት ብዛትም የ1.27 ቢሊዮን የበለጠ መሆኑ የተንቀሳቀሰው ገንዘብ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ92% ዕድገት ያሳየ ሲሆን የግብይት ብዛት ዕድገትም ከ84% በላይ ዕድገት የነበረው መሆኑ፤
  ከባንካችን አጠቃላይ የደንበኞች ግብይት በስምንቱ ወራት አማካይ ግብይት 79% በዲጂታል የተስተናገዱ ሲሆን 21%ቱ ብቻ ወደ ቅርንጫፎቻችን ጎራ ብለው የተስተናገዱ መሆኑ ለደንበኞቻችን ምቾት እና ለባንካችን በወጪ ቁጠባም ያገዘና እጅግ በጣም ከፍተኛ ስኬት ማስመዝገቡ የሚጠቀሱ ከፍተኛ ቁልፍ ስኬቶች ናቸው፡፡

በሌሎች በተቀሩትም ዘርፎች ተመሳሳይ ስኬት የተመዘገበበት በመሆኑ እጅግ በጣም ደስ ይለናል፤ ሁላችሁም የተከበራችሁ  የባንካችን ደንበኞችም ሆናችሁ ሀገር ወዳዶች በሙሉ በባንካችን መልካም አፈጻጸም ደስ እንደምትሰኙ እና ከባንካችን ጋር አብሮነታችሁን እንደምታጠናክሩ እናምናለን።

በመጨረሻም ባንካችን ለመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴው በግልጽ ካቀረበው እውነታ ባፈነገጠና በተዛባ መልኩ የሪፖርተር ጋዜጣ በዜና አርዕስቱ “መንግስት ከኢትዮዽያ ንግድ ባንክ የተበደረው አንድ ትሪሊዮን ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ” በሚል እንዲሁም በሌሎች ጥቂት ሚዲያዎችም የመንግስት ዕዳ ብር 1.3 ትሪሊዮን እንደተሻገረና አሁናዊ የመንግስት የብድር ዕዳ ዕድገትን የሚያሳይ በሚመስል መልኩ ተቀናብሮ የቀረበው ዘገባ ሀሰተኛ ከመሆኑም ባሻገር ከላይ በዝርዝር በተመላከቱት እውነተኛ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ በባንካችን በኩል የቀረበውን ትክክለኛ ሪፖርት የማያንጸባርቅ እና እነዚህን ለመንግስት የልማት ድርጅቶች የተሰጡትን ብድር ለባንካችን ለመክፈል መንግስት እያደረገ ያለውን ቁርጠኝነት ታሳቢ ያላደረገ በመሆኑ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ሚዲያዎች የተላለፈው የተዛባና የተሳሳተ ዘገባ እንዲታረም እናሳስባለን።

featured
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

በኦሮሚያና በሌሎች ክልሎች ግድያ ይፈጸም እንደነበር አቶ ጌታቸው ረዳ ይፋ አደረጉ፤ ሊገድሉኝ ነበር ያሉዋቸውን በስም ገለጹ፣ ዛሬ በይፋ ተሰናበቱ
“ጅቡቲ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ብታብር…” ሙሼ ሰሙ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
FEATURED

የጸረ – ቤተሰቡ የአንዳርጋቸው ጽጌ የፖለቲካ ውርዴ ውርስ፣ ባንዳነትና ክህደት

November 7, 20250
FEATURED

የአስገድዶ መድፈርና የግፍ ወንጀል – ከትግራይ የወጣው አዲስ ሪፖርት ገለልተኛነት?

October 23, 20250
ECONOMY

“የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማየት ሁላችንንም ያብቃን፤ እኔ እንደማይ አምናለሁ፤ ያመነ ከእኔ ጋር ይጓዝ” አብይ

October 8, 20250
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
TOP NEWS

ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups

June 7, 20260
TOP NEWS

Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV

June 7, 20260
AFRICA

Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science”

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ»

June 7, 20260
News

ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ”

June 6, 20260
Load more
Recent Posts
  • ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups June 7, 2026
  • Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV June 7, 2026
  • Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science” June 7, 2026
  • ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ June 7, 2026
  • ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ» June 7, 2026
  • ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ” June 6, 2026
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! – ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ June 5, 2026
  • Agricultural Sovereignty, Economic Transformation, and the Defiance of Extremism Ahead of the 7th National Election June 5, 2026
  • የዘለንስኪ ጥሪ፦ “ጦርነቱን ለማቆም ከፑቲን ጋር ፊት ለፊት ለመወያየት ዝግጁ ነኝ” June 5, 2026
  • የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫውን አደነቀ June 5, 2026
  • The Inverted Frontlines: How Secret Alliances and the Western Tigray Fault Line Threaten to Reignite Ethiopia June 4, 2026
  • Analysis: Ja-War, Aljazeera, Bloodshed and Terror in Ethiopia June 4, 2026
  • ጃዋር ለአርሲው ግድያ ቀዳሚ ተሟጋች ሆነ፤ “እንቀነጥሳችኋለን” ያለበትን ሜንጫ የት ጣለው? June 3, 2026
  • International Partner Welcomes Ethiopia’s 7th General Election, Calls for Inclusive Voting in Remaining Constituencies June 3, 2026
  • ዓለም አቀፍ አጋሮች የኢትዮጵያን 7ኛ አጠቃላይ ምርጫ በበጎ ተቀበሉ፤ June 3, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news