Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  FEATURED  የፋኖ ሃይሎች የ[አንድነት ዘመቻ] እና ብ/ጀነራል ምግበይ ሃይለ
FEATUREDOPINION

የፋኖ ሃይሎች የ[አንድነት ዘመቻ] እና ብ/ጀነራል ምግበይ ሃይለ

Ethioreview newsEthioreview news—March 24, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የሃገር መከላከያ ሰራዊት በቅርቡ ባወጣው መግለጫ ምክንያት የፋኖ ሃይሎች ዘመቻዎች እና ብ/ጀነራል ምግበይ ሃይለ ግንኝነት እንዳላቸው በመጥቀሱ ምክንያት አጀንዳው ከፍተኛ ትኩረት አግንቷል ። ይህ የመከላከያ ሰራዊት መግለጫ ምን ያህል እውነትነት አለው የሚለውን ጉዳይ ወደ ጎን በመተው ፋኖ ከትግራይ ሃይሎች በተለይም የእነ ደብረፂዮን ህወሓት ጋር በመጣመር ፌደራል መንግስት ለመጣል ቢስማሙ ወይም ለመስማማት ዕቅድ ካላቸው ፖለቲካዊ እንድምታው ምን ማለት እንደሆነ ግና መታወቅ ያለበት ይመስለኛል።

1ኛ) የፋኖ ሃይሎች ከእነ ደብረፅዮን ህወሓት ጋር መጣመሩ ወይም ለመጣመር ዕቅድ አለው ማለት በዋነኛነት የፋኖ ሃይሎች ለትጥቅ ትግል የዳረጋቸው ምክንያት የህልውና ሳይሆን የስልጣን መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል የሚያስብል ይሆናል ። ይህ ለማለት የቻልኩት ምክንያቱም የአማራ ህዝብ ችግሮች ህገ መንግስታዊ እና መዋቅራዊ ናቸው የሚል በአማራ ክልል ፖለቲካዊ ሃይሎች የተደረሰ ስምምነት መኖሩን ስለማቅ ነው ። በሌላ አማርኛ የአማራ ህዝብ ችግሮች የሚመነጩት አሁን ካለው የፌደራል ህገ መንግስት መሆኑን ብዙዎቹ  የአማራ ፖለቲከኞች የሚስማሙበት እና በትግል ሂደታቸው የትግል አጀንዳቸው መሆኑን የሚታወቅ ሃቅ ነው። ከዚ ነጥብ አንፃር የአማራ ህዝብ ለእልቂት የዳረገው ህገ መንግስቱ እና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በመትከል፡ ለዚህም ደጋፊ የሚሆን ትርክት በመንዛት፡  በማስፈፀም እና ዘብ በመቆም የእነ ደብረፂዮን ህወሓት( core Tplf) ዋነኛ ፖለቲካዊ ሃይል በመሆኑ የፋኖ ሃይሎች ከዚህ ሃይል ጋር የሚያደጉት መጣመር ትግላቸው የህልውና ሳይሆን የስልጣን ለዛውም ከአማራ ህዝብ ግፍ ፈፃሚ ሃይል ጋር የሚደረግ መርህ አልባ ጥምረት እንደሆነ ያሳያል የሚል እምነት አለኝ።

2ኛ) የፋኖ ሃይሎች ከእነ ደብረፂዮን ህወሓት ጋር ጥምረት መፋጠር እንደ አዲስ የትግል ሃይሎች በሂደት የቅቡልነት ችግር ይፈጥርባቸዋል የሚል እምነት አለኝ። የእነ ደብረፂዮን ህወሓት በረዥም ግዜ የስልጣን ቆይታ ምክንያት ሰፊ የሚባል ሰብአዊ መብት ጥሰቶች፡ የሙስ ወንጀሎች እና የጦር ወንጀሎች በመፈፀማቸው ምክንያት ተጠያቂ መሆን ያለባቸው ቡድኖች ናቸው። በመሆኑም በዚህ ልክ እና መጠን በወንጀል የሚፈግ አካል ጋር የትግል ጥምረት የሚፈፀም አካል የፍትህ፡ የዴሞክራሲ እና የህግ ልዕልና አካል ይሆናል ተብሎ አይታሰብም። በመሆኑም ከወዲሁ የስልጣን ሃይል እና ስልጣኑን ተፃረው የቆሙት አካላት በፀረ ዴሞክራሲያዊ መንገድ በማስተናገድ ከፍተኛ ሰብአዊ መብት ጥሰት ፡ ሙስና የሚፈፅም፡  ፍትህ የሚያጓድል እና ለህግ ልዕልና ቀናኢ ያልሆነ የመሆን ዕድሉ ሰፊ ነው። በመሆኑም የፋኖ ሃይሎች አዲስ እንቅስቃሴ ቢሆንም ቅቡልነቱ አሉታ ከሆነው የእነ ደብረፂዮን ሃይል የትግል ጥምረት ካደረገ ቅቡልነቱ በዛ ልክ የወረደ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ።

3ኛ) የፋኖ ሃይሎች ከእነ ደረብፅዮን ቡድን ጋር መጣመሩ ሊያስከትለው የሚችል ሌላው ፖለቲካዊ አደጋ ከትግራይ አዲስ ትውልድ ጋር ሊገጥመው የሚችል ስልታዊ ተቃርኖ ነው። አሁን አሁን በትግራይ ክልል እየታየ እንዳለው ፖለቲካዊ ዕድገት አዲሱ የትግራይ ትውልድ ፀረ ህወሓት በአጠቃላይ የደብረፅዮን ቡድን በልዩ ሁኔታ ከፍተኛ ተቋውሞ ከማሰማት አልፎ የትጥቅ ትግል የማድረግ ምልክትቶች እየታዩ ነው። በዚህ ሂደት የአዲሱን ትውልድ ፀረ እነ ደብረፂዮን ህወሓት የሚደረግ ትግል የክልሉ ዋነኛ ሃይል ለመሆን እና እየሆነ ሲመጣ  በሚያደርገው ትግል የፋኖ ሃይሎች ከእነ ደብረፂዮን ቡድን በሚቀርብለት ጥያቄ ሊያደርገው የሚችል ማናቸውም ድጋፍ ከትግራይ አዲሱ ትውልድ ጋር ግጭት መግባት ሊኖር ይችላላ። ይሄ ደግሞ የፋኖ ሃይሎች ከእነ ደብረፂዮን ቡድን ከሚያገኙት ጥቅም በላይ ከትግራይ አዲሱ ትውልድ የሚገጥማቸው ተፃብኦ በብዙ እጥፍ ይጎዳቸዋል የሚል እምነት አለኝ።

More stories

“አህያም ካናፋ በኛ ቤት ዘፈን ነው” የኢሳያስ ስላቅ “ኤርትራ በፍፁም ኢትዮጵያ ያለመረጋጋት ውስጥ ገብታ የማየት ፍላጎት የላትም”

December 1, 2024

የግብጽ ኢትዮጵያን የማዳከም ስትራቴጂ እስከምን?

September 22, 2024

ቬትናም ድህነትን ያራገፈች የስኬት ምድር!

April 19, 2025

እነሆ የድሉ ባለቤቶች

January 30, 2022

4ኛ) የፋኖ ሃይሎች ከእነ ደብረፂዮን ቡድን ጋር መጣመር ከፈጠሩ ሌላው ሊያስከትለው የሚችል አደገኛ ውጤት ከትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተደዳር ሊኖር የሚችል ከፌደራል መንግስት ወታደራዊ ጥምረት መፍጥር ነው። እንደሚታወቀው የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ምንም እንኳን ዝቅ ያለ ወታደራዊ ድጋፍ ቢኖረውም ከፍተኛ የሚባል የህዝብ በተለይም የወጥቶች ድጋፍ ያለው አካል ነው። ግዚያዊ አስተዳደሩ በማናቸው የጦርነት ፕሮጀክቶች የመሳተፍ ፍላጎት እንደሌለው ሲገልፅ ይሰማል። ለዚህም ይመስለኛል የፌደራል መንግስት የዛሬ ሁለት አመት በአማራ ክልል ጦርነት ሲያውጅ የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ከሌሎች ክልል መንግስታት በተለየ ሁኔታ ለፌደራል መንግስት የድጋፍ መግለጫ ያላወጣው። ሆኖም ይህ የግዚያዊ አስተዳደሩ የገለልተኝነት አቋም ሊቀየርበት የሚችል በጣም ጠባብ ዕድል የለም ማለት አይደለም። የፋኖ ሃይሎች እና የነ ደብረፂዮን ህወሓት መጣመራቸው እውን ሆኖ ውጤት እያመጣ ከታየ የግዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮቹም ስልጣናቸው ከእነ ደብረፂዮን ቡድን ከመነጠቅ ለማዳን ያችን ጠባብ ዕድል በመጠቀም ከፌደራል መንግስት ጋር በመጣመር ፀረ ፋኖ -ደብረፂዮን ቡድን የጥምረት እንቅስቃሴ ሊያደርጉ ይችላሉ።

በአጠቃላይ የፋኖ ሃይሎች ከእነ ደብረፂዮን ቡድን ጋር መጣመራቸው ማስረጃ ይሁን መረጃ የሌለ ቢሆንም ፍላጎት ግን የለም ማለት አይቻልም።  ይህ ጥምረት ከላይ በዘረዘርኳቸው ምክንያቶች ውጤት አልባ የተሳሳተ ጥምረት ( wrong match) ነው የሚል እምነት አለኝ።

Abera Nigus ( opinion)

featuredOPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“እስራኤል ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተዋሳኝ ለመሆን ለያዘችው ጥረት ያልተገደበ ድጋፍ ታደርጋለች!” 
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Related posts
  • Related posts
  • More from author
OPINION

እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ…

April 8, 2026
OPINION

ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት!

April 8, 2026
OPINION

ሙስጠፌ ተረኛው ባለስልጣን – የሃሰት ትርክ ዘመቻ በደቦ

March 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2