የአንዲ ልጅ ፣
” ኢንጂነር እንደው ሰሞኑን በፋኖዎች መካከል እየተካሄደ ያለው እርስ በርስ መጨራረስ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሆኗል። ጆሮም ጭው ከማድረግ አልፎ የተጠናቀቀውን ትግል ወደ ኃላ እየጎተቱው ነው? እርሶ እንዴት ያዩታል?”
ኢንጂነር ፣
” ምን መሰለህ የአንዲ ልጅ? በግራንድ ስትራቴጂ ውስጥ adaptability, speed, surprise 🫢 የሚባል ነገር አለ። አሁን ያጋጠመው እሱ ነው። ለእኔ ኢንጂነሩ ያመላከተኝ ነገር የህልውና ትግሉ ይበልጥ እየጎመራ እና consolidate እያደረገ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ መሄዱን ነው። በመሆኑም በዝርዝር ባስቀመጥነው በግራንድ ስትራቴጂ እቅዳችን መሰረት በፍጥነት እየሄድን ነው።አመራሩንም by design ያልተማከለ ያደረግንበት መሰረታዊ ምክንያት ለዛ ነው። በርግጥ የቁርጥ ቀን አርበኛቻችን አንተን እና ‘አንዲን’ ጨምሮ የሰራነው አደረጃጀት by design መሆኑ ያልገባችሁ እንዳላችሁ እንገነዘባለን”
የአንዲ ልጅ፣
“እንደው ኢንጂነር ይሄ እርሶ ግራንድ ስትራቴጂ የሚሉትን ምትሓታዊ እቅድ አግኝቼ ባነበብኩት እና እንደ እርሶ የትግሉን አቅጣጫ እና እንቅስቃሴ በተረዳሁት። እስከዛው ግን በእኔ በኩል ለታሪክ እንዲቀመጥልኝ የሚሰማኝን መተንፈስ እፈልጋለሁ። ትግሉ ተስፋ አስቆራጭ ወደ ሆነ እርስ በርስ መገዳደል አምርቷል። እባክሆትን እኔም <<ቋቅ>> ብሎኛል ብዬ በተናጠል ከማወጄ በፊት ይህንን ታላቁ እቅድ አግኝቼ ባነበው?”
ኢንጂነር፣
“አንድ ማወቅ ያለብህ ነገር አለ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ላይ የተካሄዱ የህልውና ትግሎች በadaptablity, speed , surprise 🫢 ምዕራፋቸው እንዲህ አይነት ነገር አጋጥሟቸው ነበር። አንተም እንደምታውቀው ታሪካዊ እና ስትራቴጂ አጋራችን የሆነው ሻዕቢያ በእንዲህ አይነት ሂደት ውስጥ አልፏል። የእኛው ጉዶች የሆኑት TPLFችም በተመሳሳይ መልኩ አጋጥሟቸው ነበር። ሁለቱም ከሌላው ነጻ አውጭ በተለየ የድሉን ዋንጫ ማንሳት የቻሉት ይህንን ፕሮሰስ በማለፋቸው ምክንያት ነው። አንተም ማሰብ ያለብህ እንደዛ ነው።ለፕሮፐጋንዳ ስራህ የጆርጅ ኦርዌልን 1984 Newspeak መለማመድ አለብህ”
የአንዲ ልጅ ፣
“Newspeak ነው ያሉኝ?”
ኢንጂነር፣
“መጠርጠሩስ! Newspeak! አዲስ ቋንቋ። አዳስ አነጋገር። አዲስ የመረዳት እና የማስረዳት ችሎታ!”
የአንዲ ልጅ፣
” በጣም አመሰግናለሁ ኢንጂነር ልብ የሚያሞቅ ነገር ነገሩኝ። እንደው ግን ከአንድ አመት በፊት ስጠይቆት በ3 ወር ውስጥ ትግሉ ይጠናቀቃል ብለውኝ ነበር?”
ኢንጂነር፣
” ምን መሰለህ የአንዲ ልጅ? የህልውና ትግል የሚመራበት ግራንድ ስትራቴጂ ሶስት ወር ሲል ሶስት ዓመትም ሰላሳ አመትም የሚል ትርጓሜ አለው። እንደዛ ነው መገንዘብ ያለባችሁ Newspeak!…አዲስ ቋንቋ፣ አዲስ አነጋገር፣ አዲስ የመረዳት ችሎታ”
የአንዲ ልጅ ፣
” በጣም አመሰግናለሁ። በድጋሚ ልቤ ሞቀ። ምስጋና የህልውና ትግሉን ለምትመሩት ግራንድ ስትራቴጂስቶች። እናንተን ባናገኝ ምድር ተሰንጥቃ ትውጠን ነበር። ድል ለዘመቻ አንድነት! ድል ለአዲሱ ትውልድ! ድል ለአዲሱ የህልውና ግራንድ አስተሳሰብ! ዘላለማዊ ክብር Newspeak ለፈጠረው ጆርጅ ኦርዌል እና ለአዲሱ አስተሳሰብ አፍላቂዎች! ድል አንገቱ እንድ ለሆነው ህዝባችን!”
(ተፃፈ እንቅልፍ እምቢ ሲል ከለሊቱ 3፡30 am) Ermiyas Legese

