Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  በወንጀል የተገኘን ሃብትና ሽብርተኝነትን መርዳትን ለሚመረመሩ መርማሪዎች የተሰጠው ስልጣን እያነጋገረ ነው
News

በወንጀል የተገኘን ሃብትና ሽብርተኝነትን መርዳትን ለሚመረመሩ መርማሪዎች የተሰጠው ስልጣን እያነጋገረ ነው

Ethioreview newsEthioreview news—June 17, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ አድርጎ መጠቀም በኢትዮጵያ የተለመደና፣ ተጠርጣሪ ቢያዝ እንኳ ሃብቱን ቤተሰብ የራሱ አድርጎ ከመጠቀም የሚገድብ አሰራርም ሆነ ህግ ባለመኖሩ ህጉ ሲረቅ ጀመሮ ተቃውሞ ነበረበት። በተለይም በርካታ ሕንጻዎችና ተቋማት በላቤት አልባ ሆነው መገኘታቸው፣ በአጭር ጊዜ ሃብት የሰበሰቡና ሕዝብ የሚጠቋቆምባቸው በርካታ በመሆናቸው ተቃውሞው ሚዛን እንደማያነሳ ተገልጾ ህጉ መዘገጃእቱ ይታወሳል። ህጉም ሲዘጋጅ ሽብርተኛነትን በገነዘብ መደገፍን አካቶም ነበር።

በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ በማስመሰል መጠቀምና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን የሚመረምር መርማሪ፤ በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከግድያ በስተቀር የትኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ አዋጅ ተደቀ። አዋጁ ለመርማሪ ከልክ ያለፈ ስልጣን ይሰጣል የሚል መከራከሪያ እንደቀረበበት የተሰማው ይህንኑ ንህግ ተከትሎ ዘሬ በጸደቀ አዋጅ ነው።

ይኸው የመርማሪዎችን የወንጀል ተጠያቂነት ያጠበበውና ጥያቄ የተነሳበት ረቂቅ አዋጅ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በሦስት ተቃውሞ፣ በአንድ ድምፀ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቆታል።

በዚህ ዐዋጅ መሠረት መሰል ወንጀሎችን ለመመርመር የተመደበ ሰው በግዴታው ላይ እያለ «ከግድያ ወንጀል በስተቀር ለሚፈጽመው የወንጀል ድርጊት የወንጀል ክስ አይቀርብበትም» በሚል መደንገጉ ጥያቄ አስነስቷል። ይህ ድንጋጌ በምርመራ ሽፋን የመንግሥት ተቃዋሚዎችን፣ የመብት ተሟጋቾችን፣ ጋዜጠኞችን እና ነጋዴዎችን ለማጥቃት የተረቀቀ እና የዜጎችን መብት የሚጎዳ ነው የሚል ተቃውሞ ገጥሞታል። አዋጁን ያዘጋጁት አካላት ግን የሕጉ መንፈስ ይህ አለመሆኑን ጠቅሰው አላማው ሽብርተኝነትን መከላከል ነው ብለዋል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለማሻሻል የቀረበውን አዋጅ ቁጥር 780/ 2005ን ዛሬ ማክሰኞ፤ ሰኔ 10 2017 ዓ.ም በአብላጫ ድምፅ አሻሽሎ ሲያፀድቅ በማሻሻያው ከተካተቱትና ጥያቄ ካስነሱት ጉዳዮች አንዱ የዚህ ወንጀል መርማሪ ሆኖ ለሚሰየም ሰው «በግዴታው ላይ እያለ ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት እና ከፍቃዱ ውጪ ሆኖ ከድግያ ወንጀል በስተቀር ለሚፈጽመው የወንጀል ድርጊት የወንጀል ክስ አይቀርብበትም» የሚለው ዋናው ነበር።

አዋጁ  በሽፋን ስር የሚደረግ ምርመራ (Under cover investigation) እንዲያስፈጽም የተመደበ ሰው፤ በግዴታ ላይ እያለ ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያትና ከፈቃዱ ውጪ በሆኖ ከግድያ ወንጀል በስተቀር ለሚፈጽመው የወንጀል ድርጊት የወንጀል ክስ አይቀርብበትም ይላል።

በምክር ቤቱ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳብ ኢሳ ቦሩ የዚህን ምክንያት ጠቅሰዋል። «ልዩ የምርመራ ዘዴን የሚያከናውን ሰው የሕዝብ ጥቅም ለማስከበር የሚሠራ እንደመሆኑ፤ ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት የሚቆይበት ጊዜ ወንጀል ቢፈጽም እንኳን ከወንጀል ክስ ነፃ ስለሚሆንበት አግባብ መደንገግ ሥራውን ውጤታማ ስለሚያደርገው ነው»።

ይህ ምክንያት ግን ጥያቄም ተቃውሞም ቀርቦበታል።በተለይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት «ጥቂት የፀጥታ አካላት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አስከትለው ነበር» የሚለው ተጠቅሶ ጭምር ነው ተቃውሞዎች የቀረቡት።

«ከግድያ መለስ ብዙ ወንጀሎች አሉ። አካል ማጉደል አለ፣ ንብረት ማበላሸት አሉ እና ይህ ሰው እንደፈለገ የሚያደርግ በመሆኑ መብቱን መዘርዘር ነው [የሚሻለው»።

«መንግሥት ውስጥ ሆነው የተለየ ድምፅ ያላቸው እና መንግሥትን የመተቸት አዝማሚያ ያላቸውን ጋዜጠኞች፣ የሰብዓዊ መብት አራማጆችን ነው ለመክሰሻ የዋሉት [የቀደሙ ሕጎች]። ይህም የማሻሻያ አዋጅ በተመሳሳይ መንገድ እነዚህን አካላት እና በተጨማር ደግሞ የንግዱን ማኅበረሰብ በተለይ ከመንግሥት ጋር ተጠግተው የማይነግዱ ወይም ለመንግሥት ፋይናንስ የማያደርጉ ግለሰቦችን ለማጥቃት ሊውል ይችላል»።

አዋጁ ሰው [መርማሪዎች] እንደፈለገ እንዲሆን የሚያደርግ፣ ያልተገባ ሥልጣንን በመስጠት የዜጎችን መብት የሚጋፋ ይሆናል ተብሎም ማሻሻያው ከመጽደቁ በፊት ማስተካከያ ተጠይቆበት ነበር። ማሻሻያ የተደረገበት ይህ ሕግ ዓለምአቀፍ አሠራርን መነሻ ያደረገ እና አስፈላጊነቱ የሚያጠያይቅ እንዳልሆና ተገልጾም በምክር ቤቱ ድጋፍ አግኝቷል። «ሥጋት አድርጎ ሊወስድ የሚችል ወገን ሊኖር ይችላል [ሕጉን]። ግን ለምን ይሰጋል ነው ያ ወገን»።

በምክር ቤቱ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳብ ኢሳ ቦሩ ለተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ይህ ማሻሻያ ሕግ «ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ደህንነት ተቋም የሰጠውን ምክረ ሀሳብ መነሻ በማድረግ» መዘጋጀቱንም ጠቅሰዋል። «እኛ ፖለቲከኞችን ሆን ብሎ ለማጥቃት በምንም ተዐምር ያለመ እንዳልሆነ መያዝ አለበት»

ይህንን ወንጀል ለመከላከል «አስቸኳይ ሁኔታ ባጋጠመ ጊዜ ‘መርማሪ’ ተብሎ የተጠቀሰው አካል የዐቃቤ ሕግ የበላይ ኃላፊ ሲፈቅድ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የወንጀል ፍሬን ተከታትሎ ለመለየት በባንክ ሒሳቦች እና በሌሎች ተመሳሳይ ሒሳቦች ላይ ክትትል ለማድረግ፣ የኮምፒውተር መረቦችን እና ሰርቨሮችን ለመለየት፣ መገናኛዎችን በክትትል ሥር ለማዋል ወይም ለመጥለፍ ፣ የደብዳቤ ልውውጦችን መጥለፍ እና ለመያዝ» እንዲችል ሥልጣን ይሰጣል። ይህንንም በ48 ሰዓታት ውስጥ ለፍርድ ቤት ማሳወቅ ይኖርበታል ተብሏል።

በዚህ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ሰው የንብረቱ መወረስ እንደተጠበቀ ሆኖ ከ15 እስከ 25 ዓመት ጽኑ እስራት እና እስከ አንድ ሚሊዮን ብር መቀጮ እንዳለውም ቅጣትን በሚመለከተው የድንጋጌው ክፍል ላይ ተጠቅሷል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ኢሳ ቦሩ ለኢቲቪ በሰጡት ማብራሪያ የተሻሻለው አዋጅ በወንጀል የተገኘ ሃብትን ሕጋዊ የማስመሰልና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያለመ ነው።

ሽርተኝነት ዓለም አቀፍ ችግር መሆኑን ያነሱት አቶ ኢሳ፤ ችግሩ በአንድ ሀገር ኢኮኖሚ እና በሀገር ደህንነት ላይ የሚያስትለውን ተፅዕኖ ለመከላከል ጠንካራ የሕግ ሥርዓት ወሳኝ በመሆኑ ሕጉን ማሻሻል አስፈልጓል ነው ብለዋል።

ዛሬ የፀደቀው አዋጅ የቀድሞው አዋጅ ቁጥር 780/2012ን ያሻሻለ መሆኑን የጠቀሱት ምክትል ሰብሳቢው፤ የአዋጁ መሻሻል ለኢኮኖሚውና ለሀገር ደህንነት ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።

በሀገሪቱ በወንጀል የተገኘ ሃብትን ጠንካራ የሕግ ስርዓት ዘርግቶ በደንብ መቆጣጠር ካልተቻለ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑንም ጠቁመዋል።

አዋጁ ወንጀልን ለመቆጣጠር ከማገዝ በቀር በዜጎች ላይ የሚፈጥረው ምንም ዓይነት ስጋትም ሆነ ጉዳት እንደማይኖር፤ ማንኛውም ሰው በወንጀል ውስጥ ባለው ተሳትፎ ብቻ ተጠያቂ እንደሚሆን አረጋግጠዋል።

ዛሬ የፀደቀው በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ የማስመሰልና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አዋጅ ቁጥር 1387/2017 በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የሚተገበር ይሆናል።

DW and ETV

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ከፊል የፋኖ አደረጃጀት የሰላም ድርድር እየተሳካ ነው፤ ለክረምት ዝግጅት ወደ ሱዳን ያመሩ አሉ
Is Iran on the Brink of Collapse? Shocking Report on the Israel-Iran Conflict.
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2