Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  POLITICS  ስምረት ፓርቲ በአፋር ነጻ መሬት የሰፈሩትን ታጣቂ ኃይሎች እንደሚደግፍ አስታወቀ
POLITICS

ስምረት ፓርቲ በአፋር ነጻ መሬት የሰፈሩትን ታጣቂ ኃይሎች እንደሚደግፍ አስታወቀ

Ethioreview newsEthioreview news—June 1, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ስብስባቸው የመሰረቱት ፓርቲ አፋር የሰፈሩትን ታጣቂዎች ዓላማ እንደሚደግፍ በይፋ አስታወቀ። በቅርቡ በትግራይ ጉባኤ እንደሚያካሂድ አመለከተ። ከሻዕቢያ ጋር የተጀመረውን አዲስ ግንኙነት በመቃወም ወደ አፋር ያቀኑትን ታጣቂዎች መላ እንዲፈልጉላቸው ኢሳያስ አፉወርቂ ማሳሰባቸው ተዘግቦ ነበር።

ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) በአዲስ አበባ ጋዜጣዊ መግለጫ ከመስጠቱ በተጨማሪ ከሪፖርተር ዩቲዩብ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። በዚሁ ቃለ ምልልስ ላይ እነ ዶክተር ደብረ ጽዮን ከሚመሩት ኃይል በመውጣት አፋር ላይ ራሱን ዳግም እያደረጃ ያለውን የታጣቂ ቡድን እንደሚደግፉ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም አቶ ጌታቸው ረዳ ወደ አፋር ሃራ መሬት እያመራ ያለውን ሰፊ ቁጥር ያለው ታጣቂ እንዳይበተን የማሰባሰብ ስራ እንደሚሰራ መናገራቸው ይታወሳል። ወይዘሮ ኬሪያም ከርዕዮት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ማደራጀትና ማሰባሰብ እንደሚያስፈልግ አመልክተው ነበር።

ከኤርትራ ወደ መቀለ የተጓዙ ከፈተኛ የጦር አዛዦች ይህ ኃይል ለታሰበው እንቅስቃሴ ችግር ስለሚፈጥር እንዲደመሰስ ወይም ሌላ መፍትሄ እንዲፈለግለት ከኢሳያስ አፉወርቂ በታዘዙት መሰረት መመሪያ መስጠታቸውን አቶ ጣዕመ አርዶም ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው።

More stories

በማደግ ላይ የሚገኙ አገሮች የፋይናንስ ሥርዓት ሥር ነቀል ለውጥ ጥያቄ

July 2, 2023

“ዘመን ትውልድን ይገነባል ፤ ትውልድም ዘመንን ይገነባል”

September 10, 2023

80ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እና የኢትዮጵያ ተሳትፎ

September 27, 2025

ሩስያ ሳታስበው በትጠቃ ሞታም ጠላቶቿን ትበቀላለች ይላል …

August 10, 2025

እሳቸው እንዳሉት “የአርሚ፣ ክፍለጦር፣ ኮርና ዕዝ አዛዥ ከፍተኛ መኮንኖችን ጨምሮ ‘ሐራ መሬት/ ነጻ መሬት’ ላይ የሰፈሩት የትግራይ ሰራዊት አካላት የእነ ደብረስዮንን ትህነግ አስግቶታል። በግምግማቸው ‘አሁን ላይ እንደፈለገን ተዋጋ፣ በዚህ ሂድና ይህን ፈጽም የምንለው ኃይል የለንም’ በማለት ስጋታቸው አኑረዋል። በግል ይህን እየገመገሙ ከሻዕቢያ ጋር የቢሆን ዕቅድ የሚነድፉት የትህነግ ሰዎች የተሳሳተ ሂሳብ እያሰሉ ነው” በማለት እጃቸው የገባውን መረጃ ጠቅሰው አቶ ተናግረው ነበር። እንግዲህ ይህን ለሻዕቢያ ስጋት የሆነ ኃይል ነው የአዲሱ ስምረት ፓርቲ የሚዲያ እና የኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ረዳኢ ሓለፎም እንደሚደግፉት ያረጋገጡት።

በጋዜጣው መግለጫ ላይ ተገኝቶ የዘገበው አዲስ ስታንዳርድ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ ፍቃድ ያገኘው ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ (ስምረት)፤ እስከ አንድ ወር ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ መስራች ጉባኤውን እንደሚያካሄድ ገለጸ። ፓርቲው ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የአባላት ምልመላ እና ከክልል እስከ ቀበሌ ያሉ አደረጃጀቶችን የመፍጠር ስራዎችን እንደሚያከናውን መገለጫ የሰጡትን ጠቅሶ አስታውቋል። 

ስምረት ፓርቲ ይህን የገለጸው፤ ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 23፤ 2017 በአዲስ አበባው ሸራተን ሆቴል በሰጠው የመጀመሪያው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ጋዜጣዊ መግለጫውን ከፓርቲው መስራቾች አንዱ የሆኑት የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት በነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ ይሰጡታል ተብሎ ቢጠበቅም፤ ባጋጠማቸው “የጤና እክል” ምክንያት በመግለጫው ሳይሳተፉ ቀርተዋል።

እርሳቸውን በመተካት መግለጫውን የሰጡት የአዲሱ ፓርቲ የሚዲያ እና የኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ረዳኢ ሓለፎም፤ ፓርቲው በሚቀጥለው አንድ ወር ውስጥ ሁለት መሰረታዊ ስራዎችን እንደሚያከናውን ተናግረዋል። መቶ አባላትን በመያዝ ጊዜያዊ ፍቃዱን ከምርጫ ቦርድ ያገኘው ስምረት፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ከትግራይ እና ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች አባላትን የመልመል ስራዎች እንደሚሰራ አቶ ረዳኢ ተናግረዋል።

“የፓርቲ ምልመላው በመሰረቱ ከሶስት አካላት ነው ዋናው ትኩረት የሚያደርገው። ሁሉም የህብረተሰብ አካል የሚያሳትፍ ቢሆንም አሁን መሰረታዊ ትኩረት የሚያደርግባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ግን ሶስት [ናቸው]። አንደኛው፤ የእኛ አባል የነበረ እና የለውጥ ኃይል የደገፈው [ነው]። ከአሁን በፊት የህወሓት አባል ሆኖ ግን ደግሞ ከደረቀው ሳይሆን ከለውጥ ኃይሉ ጋር ሆኖ እየታገለ ያለው አባልም፣ ካድሬም እንዳለ የሚቀጥል ይሆናል” ብለዋል አስተባባሪው።

አዲሱ ስምረት ፓርቲ፤ የህወሓት አባል ያልነበሩ ወጣቶችን እና ምሁራን ላይ ትኩረት እንደሚያደርግም አቶ ረዳኢ ገልጸዋል። “በድምር እነዚህ የአዲሱ ትውልድ ክፍል ስለሚሆኑ፤ አዲሱ ትውልድ በስፋት የሚሳተፍበት፣ የነገውን ትግራይን ለመገንባት ልዩ አስተዋጽኦ እና ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርግበት እንዲሆን አስበን የምልመላ ስራችንን እንቀጥላለን” ሲሉም አብራርተዋል።

በ2012 ዓ.ም የወጣው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ፤ የክልል የፖለቲካ ፓርቲ ለመመስረት የአራት ሺህ መስራች አባላት ፊርማ ማሰባሰብን በግዴታነት ያስቀምጣል። ከአዲሱ ክልላዊ ፓርቲ መስራች አባላት ውስጥ “ከስልሳ በመቶ በላይ የሚሆኑት” የክልሉ መደበኛ ነዋሪዎች መሆን እንዳለባቸው በአዋጁ ላይ ሰፍሯል።

“ከትግራይ ውጭ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያለ ትግራዋይም ቢሆን የሚመዘገብበትን ስርዓት እንፈጥራለን። በአዲስ አበባም፣ ከአዲስ አበባ ውጭ ያለውም ትግራዋይ፤ የስምረት ፓርቲ አባል ለመሆን የሚያበቃውን ነገር፣ ፕሮግራሙን ከተቀበለ አባል ይሆናል። ይህን ለማድረግ ደግሞ በትግራይ ውስጥ [ብቻ] ሳይሆን በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እና በከተሞችም እንዲሁ አደረጃጀቶች ይኖሩናል” ሲሉ አቶ ረዳኢ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስረድተዋል። 

አዲሱ ፓርቲ በዳያስፖራ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆችን የሚያቅፉ አደረጃጀቶች በየአካባቢው እንደሚኖሩትም ተናግረዋል። የፓርቲውን አደረጃጀቶች በየደረጃው የማዋቀሩ ስራ በሚቀጥለው አንድ ወር ውስጥ ለማጠናቀቅ መታቀዱንም አመልክተዋል። ይህን ለማድረግ በትግራይ ውስጥ “ከክልል ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ የተለያዩ መድረኮች ይኖሩናል” ብለዋል አስተባባሪው።

“እነዚህ መድረኮች ከተጠናከሩ፣ የአባል ምልመላው ከተጠናቀቀ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ትግራይ ውስጥ ጉባኤ የምናካሄድ ይሆናል። ጉባኤው ክረምት ከማለቁ በፊት የሚጠናቀቅ ይሆናል። ምናልባት ከአንድ ወር እስከ አንድ ወር ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ መስራች ጉባኤ ይካሄዳል” ሲሉም አዲሱ ፓርቲ በመጪዎቹ ጊዜያት የሚያከናውናቸውን ተግባራት ዘርዝረዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለስምረት ፓርቲ የሰጠው ጊዜያዊ ፍቃድ የሚያገለግለው ለሶስት ወራት ብቻ ነው። 

POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ሕገ መንግስት እንዲሻሻል መንግስት አጀንዳ አቀረበ፤ ክልሎች በቋንቋ ሳይሆን በአቀማመጥ እንዲዋቀሩ ተጠይቋል
ወደ ትግራይ ክልል ሲጓዙ አፋር ላይ ለቀናት ክልከላ የተደረገባቸው ተሽከርካሪዎች እንዲለቀቁ ተወሰነ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
POLITICS

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

March 28, 2026
POLITICS

አስቸኳይ የአርበኛነት ጥሪ ለኢትዮጵያን

March 4, 2026
POLITICS

ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡ

January 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2