Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  POLITICS  ሩስያ ሳታስበው በትጠቃ ሞታም ጠላቶቿን ትበቀላለች ይላል …
POLITICS

ሩስያ ሳታስበው በትጠቃ ሞታም ጠላቶቿን ትበቀላለች ይላል …

Ethioreview newsEthioreview news—August 10, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ሩሲያ ፡ አያድርገውና ሳታስበው በአሜሪካን ጥቃት ቢደርስባት ፡ መሪዎቿ በጅምላ ቢገደሉ ፡ ከተሞቿ በኒውክሊየር አረር ነደው እንዳልነበር ቢሆኑ ሞተውም ጠላቶቿን ሞታም ትብቀላለች

ኢትዮሪቪው | አሜሪካ በ1942 የኑክሌር መሳሪያ መያዟን ይፋ አድርጋ ከሶስት አመታት በኋላ የጃፓን ከተሞች ላይ ይህንን ቦምብ ስትጥል አለም በድንጋጤ ውስጥ ነበር ።

በወቅቱ ይህንን መቶሺዎችን ከፍ ሲልም ሚሊዮኖችን ሊያወድም የሚችል ቦንብ ባለቤት አሜሪካ ብቻ ነበረች ። ከአራት አመት በኋላ በ Aug1949 ደግሞ ሩሲያ የአለማችን ሁለተኛዋ የኑክሌር ቦምብ ባለቤት መሆኗን አሳወቀች ።

በዚያ አለምን ለሁለት ከፍሎ በነበረው የቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት በተለይ ሁለቱ ሀገራት ከዛሬ ነገ ወደ ጦርነት ሊገቡ ይችላሉ ተብሎ በሚሰጋበት ጊዜ ሩሲያ ኑክሌር መያዟ በተወሰነ መልኩ መረጋጋትን ፈጥሮላት ነበር ። ሆኖም ግን ብዙም ሳይቆይ በሞስኮ ዘንድ ሌላ ስጋት ተፈጠረ ። ይህ ስጋት አሜሪካ አስቀድማ ሩሲያን በኑክሌር ቦምብ ብትመታስ የሚለው ስጋት ነው ።

More stories

ደቡብ ሱዳን ስድስተኛ ሀገር ሆና የናይል ስምምነት ማዕቀፍን አጸደቀች

July 12, 2024

“ትህነግ ጦሩን እስጠግቷል፤ የጦርነት ስጋት አለብን” የጠለምት ወሰንና ማንነት አስመላሽ

June 7, 2025

“የኢትዮጵያን ህልውና የሚበይኑት የተፈጥሮ ሀብቶች…”

September 2, 2024

“ዘመን ትውልድን ይገነባል ፤ ትውልድም ዘመንን ይገነባል”

September 10, 2023

እንደዛ ከሆነ ሁሉ ነገር ያበቃል ፡ አሜሪካ ቀድማ ሩሲያ ላይ የአቶሚክ ጥቃት ካደረሰች ሩሲያ እስከያዘቻቸው መሳሪያዎች ተረት ሆና ትቀራለች ።

ስለዚህ የሩሲያ የኒውክሊየር ጠበብት ለዚህ መፍትሄ ለመፈለግ ለአስር አመታት ያህል ቀን ከሌት ምርምራቸውን መቀጠል ነበረባቸው ።

በመጨረሻም ሩሲያ በ1985 dead hand ( Perimeter ) የተባለውን እስካሁንም ድረስ የምድራችን ብቸኛ የተባለ መሳሪያ ወይም ሲስተም ፈጠረች ።

ሩሲያ ፡ አያድርገውና ሳታስበው በአሜሪካን ጥቃት ቢደርስባት ፡ መሪዎቿ በጅምላ ቢገደሉ ፡ ከተሞቿ በኒውክሊየር አረር ነደው እንዳልነበር ቢሆኑ ፡ እንኳን ደሟን የሚበቀልላት ፡ ከሞተች በኋላ እንኳን ጠላቷን መግደል የምትችልበትን መሳሪያ በእጇ ያዘች ።

ይህ ያለሰው ማጥቃት የሚችል ፡ ሩሲያ ያስቀመጠቻቸውን የኒውክሊየር ሚሳይሎች ተኩሶ የጎዳትን የሚጎዳላት መሳሪያ ሌላ ጥቅሙ ጠላት በሩሲያ ላይ ሊወስድ የሚያስበውን እርምጃ እንዲመረምር ፡ ሩሲያን በኑክሌር ከማጥቃቱ በፊት ቆም ብሎ እንዲያስብ እና እጁን እንዲሰበስብ የሚያደርግም ነው ።

ሩሲያ ለደህንነቷ የሚያሰጋት ጉዳይ በሌለበት ወቅት የdead hand ቁልፎች OFF ሆነው የሚቆዩ ሲሆን ከሀገራት ጋር ውጥረት ውስጥ ገብታ ደህንነቷ አደጋ ላይ እንደሆነ ከጠረጠረች ይህ በጠበብቶቿ የተገነባውን ሲስተም ዝግጁ እንዲሆን ON ይደረጋል ።

እና አይበለውና ሩሲያ እንደገመተችው በኑክሌር ጥቃት ሲደርስባት በአስር ደቂቃዎች ውስጥ የዚህ መሳሪያ ጆሮም አፍንጫውም ስራ ይጀምሩና ፡ ኑክሌር ሲተኮስ የሚታዩ ምልክቶችን መመርመር ይጀምራል ። አውዳሚ የሆነው የኑክሌር መሳሪያ እጅግ አደገኛ በመሆኑ የሆነ ሀገር ላይ ቢጣል ከፍተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ይፈጥራል ።

ሌላው ከፍተኛ የሆነ የብርሀን ጨረር ነው ። ይህ ጅምላ ጨራሽ ቦንምብ ወደ መሬት በሚወድቅበት ሰአት ለሰከንድ ፀሀይ ከምትፈጥረው ብርሀን የሚስተካከል ታላቅ የጨረር ብልጭታ ይከሰታል ። ይህ ለሰከንድ የሚፈጠረው ብልጭታ ሌላው ለDead hand ምልክት የሚሰጠው ነገር ነው ። የኑክሌር ቦንብ ሌላው መታወቂያ ከፍተኛ የሆነ የአየር ግፊትና ሀይለኛ የሆነ ጨረር መለቀቅ ነው ።

በተጨማሪም ፡ ኑክሌር ሲፈነዳ ብቻ የሚከሰቱ እንደ ሀይለኛ የፍንዳታ ድምፅ ፡ ሰው አልባ ሆኖ ፍፁም ፀጥታ የሰፈነበት ድባብ እና የመሳሰሉትን የምፅአት ምልክቶች እንደተከሰቱ ካወቀ በኋላ ሩሲያ ለዚህ ቀን ብላ ያዘጋጀችው dead hand የመጨረሻ ማረጋገጫ የሆኑትን ነገሮች ይፈልጋል ።

በሩሲያ ቤተመንግስት ላሉ ሰወች እና ወደ ዋናው ማዘዣ ጣቢያ ያሉ ሃላፊዎችን ለማግኘት ይሞክራል ፡ ግን የተተኮሰው ማንንም የማያስተርፈው ኑክሌር ነውና ማንንም ማግኘት አይችልም ።

በዚህ ጊዜ የሩሲያ ደም-መላሽ ፡ ነገሮችን እንዳልነበር ከሚያደርገው እርምጃ ውስጥ ቀዳሚ የሆነውን ሚሳይል በመተኮስ ይጀምራል ። ይህ ሚሳይል በውስጡ ምንም ቦምብ የለም ። ይህ ሚሳይል የያዘው አንድ የሲግናል መልእክት ብቻ ነው LAUNCH የሚል አንድ ቃል ።

ይህ በሩሲያ ሰማይ ላይ ርቆ የተተኮሰ ሚሳይል ሩሲያ ያሏትን በሺህ የሚቆጠሩ ሚሳይሎች እንዲተኮሱ ትእዛዝ የሚሰጥ ነው ። ልክ በዚህ ጊዜ በየቦታው የኑክሌር ቦንብ ይዘው ከምድር ስር የተቀበሩት ትላልቅ አገር አቋራጭ ሚሳይሎች የሚገኙበት ባንከር የብረት በሮች ይከፈታሉ ።

በሩሲያ ውስጥ እና በተለያዩ ባህሮችና ውቅያኖሶች ውስጥ ያሉ የሩሲያ ሰርጓጅ መርከቦች ፡ እንዲሁም በተለያየ ቦታ ፡ ያሉ ኑክሌር የጫኑ ሚሳይሎች ከdead hand ሲስተም LAUNCH የሚለው ትእዛዝ እንደደረሳቸው ትእዛዙን መፈፀም ይጀምራሉ ።

በሩሲያ ላይ ጥቃት በተሰነዘረ በአስር ደቂቃ ውስጥም ፡ ቀደም ሲል ኢላማ በተደረገባቸው ሀገራት ያሉትን ከተሞች ፡ ወታደራዊ ሰፈሮች ፡ እና መመታት አለባቸው ተብሎ የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ልክ ሩሲያ ላይ የተጣለው አይነት የኑክሌር አረር የያዙ ቦንቦችን ማዝነብ ይጀምራሉ ።.በጠላት ኑክሌር ቦምብ የወደመችው ሩሲያ ሞታም ጠላቶቿን በDead hand በኩል በዚህ መልኩ ትበቀላለች ።

በምድር ላይ በዚህ መልኩ ሀያል ስትሆን ብቻ ነው ጠላት እንኳን ሊያከብርህ የሚችለው ፡ ልክ እንደ ሩሲያ ። ባለፈው ሰሞን የቀድሞ የሩሲያ ፕሬዝደንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ለትራምፕ ያስታወሱት ይህንን ነው ። ሩሲያ የዚህ ሲስተም ባለቤት መሆኗን መዘንጋት አይገባም ነበር ያሉት ።

Via Wasihun Tesfaye


POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
600 ሚሊዮን ብር እንደወጣበት የተነገረለት የንግድ ባንክ ሎጎ ጉዳይ!..
የኦሮሚያ አዲሱ ዘመቻዋ “ማጥራት”- ሽመልስ አብዲሳ በአሸናፊነት ይወጣሉ?
Related posts
  • Related posts
  • More from author
POLITICS

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

March 28, 2026
POLITICS

አስቸኳይ የአርበኛነት ጥሪ ለኢትዮጵያን

March 4, 2026
POLITICS

ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡ

January 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2