አንዳንድ ጎበዞች ጀዋር ብሄራዊ ጥቅም በማስከበር ረገድ በአባይ ግድብ ዙሪያ ያሳየው የማያወላውል አቋም እና ተሟጋችነት የሚል ዘገባና ትንታኔ በማቅረብ የጀዋርን ተክለ-ሰብዕና ለመገንባት ጥረት ሲያደርጉ እያየን ነው። ያስተዛዝባል
ጌታዬ! ለብሄራዊ ጥቅም መቆምህ የሚታወቀው በአዘቦቱ ቀን የድጋፍ መግለጫና ትንተና በማውጣት ሳይሆን ሃገር ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስከበር ጉድ ጉድ በምትልበት በወሳኝ የፈተና ቀናት በምታሳየው አቋም፣ ድጋፍ፣ ትብብር፣ ስልታዊ እርጋታና ቁጥብነት (Strategic Cooperation, Patience and restraint) ነው። በነዚህ የሃገሪቷ ወሳኝ የፈተና ወራት በተለይ የአባይ ግድብ ድርድር ወቅት መረጃዎች የሚያሳዩት ጀዋር ሃገሪቷን ትርምስ ውስጥ በማስገባት ወይም ግጭት በማቀጣጠል ነው።
ግልፅ የአደባባይ የመረጃ ምንጮችን OSINT tools ተጠቅሜ ያዘጋጀሁትን የኩነት ቅደም ተከተል (Events time line) እስኪ እንያቸው:-
፩ በአሜሪካ አደራዳሪነት ወቅት
ግብፅ በደጅ ጠኝዎቿ አማካኝነት በወቅቱ የአሜሪ አቃቤ-ንዋይ ፅህፈት ቤት ሃላፊ (Sec. of treasury) የነበረውን ሎቢ በማድረግ ጥቅምት 23፣ 2012 ዓም በትራምፕ አደራዳሪነት ድርድር ለማድረግ ቀን ተቆረጠ።
ለዚህ ድርድር ኢትዮጵያ ዝግጅት እያደረገች በነበረበት ወሳኝ ወቅት ጀዋር መሃመድ ጥቅምት 12፣ 2012 ዓም “በመንግስት ሃይሎች ተከበብኩ” የሚል መልእክት በማኅበራዊ ሚዲያ በማሰራጨት በመላው የኦሮሚያ ክልል እና በአዲስ አበባም ጭምር ከፍተኛ ሁከትና ግጭት እንዲፈጠር አድርጓል።
በዚህ ግጭት ሳቢያ በርካታ ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን፣ ብዙ ንብረቶችም ወድመዋል።
በጀዋር ምክንያት ሃገር እንዲህ አርብ ላይ ቆማ የኢትዬጵያ ተደራዳሪዎች ወደ ዋሽንግተን አቀኑ።
፪ የሃጫሉ ግድያና የኪንቻሳ ድርድር
የአሜሪካው ድርድር ለግብፅ ያደላ በመሆኑ በኢትዮጵያ እምቢተኝነት ከከሸፈ በኋላ የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪ ሆኖ ቀረበ። ድርድሩ ከሀምሌ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በሶስቱ ሀገራት (ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን) መካከል እንደሚካሄድ ቀን ተቆረጠ።
ከድርድሩ ሳምንት በፊት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ተገደለ።
ጀዋር መሐመድ ግድያው ከተፈጸመ በኋላ ወዲያውኑ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቹ ላይ የግድያውን መንስኤና ተጠያቂነት በተመለከተ ጥርጣሬዎችን በመፍጠር ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የማህበራዊ ሚድያ ተከታዮቹን እና እመራዋለሁ የሚለውን የተደራጃ ወጣት ቡድን ስሜትን በማነሳሳት ወደ ጎዳና እንዲወጡና ተቃውሞ እንዲያደርጉ አነሳስቷል። ይህንንም ተከትሎ ተቃውሞው በፍጥነት በመላው የኦሮሚያ ክልልና በአዲስ አበባም ተሰራጭቷል። የሕይወት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ደርሷል።
እንዲሁም ጀዋር እና ሌሎች አክቲቪስቶች የሃጫሉን ሞት ከመንግስት ጋር በማገናኘት የፖለቲካ ትርጉም እንዲኖረው አድርገውታል። ይህም በወቅቱ በመንግስት ላይ የህዝብን ቁጣና ተቃውሞ በማነሳሳት ግጭቱ እንዲባባስ አስተዋፅኦ አድርጓል።
በአጠቃላይ፣ የሃጫሉን ሞት ተከትሎ ለተፈጠሩ የግርግርና የግጭት ኩነቶች የጀዋር መሐመድ ሚና ግጭት በማባባስ እንደ አቀጣጣይ (catalyst or amplifier) ሆኖ አገልግሏል።
እንግዲህ ሃገር አርብ ላይ በቆመችበት በዚህ ወቅት ነበር የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች ወደ ኪንቻሳ የሄዱት። ድርድሩ ከሃምሌ 2-13 /2012 በቆየበት ወቅትም ግጭቱ አልበረደም ነበር።
ይህ የድርድን አቋም እንዴት ይጎዳል?
ሃገራት ብሄራዊ ጥቅማቸውን ለማስከበር ወደ ድርድር ጠረምጴዛ ሲመጡ በተቃራኒያቸው ላይ የላቀ የድርድር አቋም (Position of Strength) እንዲኖራቸው ያላቸውን ብሄራዊ የተፅዕኖ አቅም(National instrument of Power) በመጠቀም በግልፅና በሕቡዕ የተለያዩ የተፅዕኖ ተግባራትን (Influence Operations) ይፈፅማሉ። ይህም በድርድር ወቅት ተፈላጊውን ውጤት የማግኘት ዕድል ይጨምራል፣ የማስፈራራትና የማሳመን አቅም ይሰጣል፣ እንዲሁም ተለዋዋጭነትንና ምርጫን ያሰፋል።
በአጭሩ፣ በአለም አቀፍ ግንኙነት የላቀ የድርድር አቋም የሚፈለገውን ግብ ለማሳካት ወሳኝ መሣሪያ ነው፤ በተቃራኒው ደግሞ ደካማ ሆነህ ከተገኘህ የሚመጣውን ውጤት ሁሉ ለመቀበል ትገደዳለህ። ለዚህ አብነት ይሆናችሁ ዘንድ ዩክሬንና ራሽያ ወደ ድርድር ጠረጴዛ ሲመጡ የላቀ የድርድር አቋም እንዲኖራቸው የሚፈፅሟቸውን ወታደራዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና የስነ ልቦና ጦርነትን በተመለከተ ከዚህ በፊት የፃፍኩትም መመልከት ትችላላችሁ።
አሁን ደግሞ ከላይ ያየናቸው ቅድመ ድርድር ጀዋር መራሽ ግጭቶች የኢትዮጵያን የድርድር አቋም እንዴት እንደ ግድ በአንፃሩ ግብፆችን እንዴት እንደጠቀመ እናያለን።
እነዚህ የውስጥ ግጭቶች በኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች ላይ የድርድር አቅማቸውን እንደሚያዳክሙ እሙን ነው። ምክንያቱም የውስጥ ግጭት ሲከሰት የመንግስትና የህዝብ ትኩረት ከውጪ ጉዳዮች ይልቅ ወደ ውስጣዊ ችግሮች ያዘነብላል። ይህ ደግሞ በድርድር ላይ ያለውን አቅምና ዝግጅት እንዲቀንስ ያደርጋል። የስነ ልቦናው ጭናው ከፍተኛ እንደነበር መረዳት አይሳድግትም።
በተጨማሪም በተፈጠረው የፖለቲካዊ አለመረጋጋት ድርድሩን በሚመለከት ወጥ የሆነ አቋም እንዳይያዝ አድርጎ ነበር። አንዳንዶች የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዎቻቸውን በመጠቃም “ግድቡ ተሽጧል” በማለት የፓለቲካ ትርፍ ለማግኘት በዘመቻ መልክ ይሰሩበት ነበር። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያውያን በአንድ ድምጽ ለመናገር እንድንቸገር በማድረግ የድርድር አቋሟችን እንዲዳከም ምክንያት ሆኑዋል። በውስጥ ግጭትና አለመረጋጋት የምትታወቅ ሀገር በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ያላት ተዓማኒነት እንዲቀንስ ያደርጋል። ለሀገራችን አቋም የሚሰጡትን ትኩረትና ድጋፍ ሊቀንስ ይችላል።
በአንፃሩ እነዚህ ግጭቶች ለግብፅ የላቀ የድርድር አቋም
እንዲኖራቸው ትልቅ እድል ፈጥረዋል።
ግብፅ በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረውን አለመረጋት በመጠቀም የሞራልና የስነ-ልቦናዊ የበላይነት አግኝታለች። “ኢትዮጵያ በውስጥ ችግር የተመሰቃቀለች ሀገር ናትና ስለ ግድቡ በብቃት መደራደር አትችልም” የሚል ትርክት ለመፍጠር ሞክራለች።
እንዲሁም ግብፅ ሁልጊዜም የአባይ ግድብ ድርድር ከአፍሪካ ህብረት ይልቅ በአሜሪካና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) እንዲመራ ትፈልጋለች። በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠሩት ግጭቶች የሀገሪቱን የውስጥ ድክመት እንደ ማሳያ በመጥቀስ፣ ድርድሩን ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ ለማውጣት ተጨማሪ ምክንያት ሆኗታል።
በተጨማሪም ግብፅ ይህን የውስጥ ችግርና አለመረጋጋት በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ በአብነት በማንሳት ኢትዮጵያን ደካማ አድርጋ በማቅረብ ለራሷ ድጋፍ እንድታሰባስብ ረድቷታል።
በአጠቃላይ፣ ከጀዋርና ከሌሎች የፓለቲካ ሃይሎች መነሻነት ሲፈጠሩ የነበሩት የሃገር ውስጥ ግጭቶች የኢትዮጵያ የውስጥ ግጭት የሀገሪቱን የድርድር አቅም አዳክሞ ለግብፅ መንግስት ደግሞ የላቀ የፖለቲካዊና የስነ-ልቦናዊ የድርድር አቋም እንዲኖራት አስችሏል።
ክብርና ሞገስ ሃገር አርብ ላይ በቆመችበት በፅናት የሃገራችንን ብሄራዊ ጥቅም ላስከበሩ ጀግኖች ተደራዳሪዎቻችን!
ክብርና ሞገስ ከጥንስስ እስከ ፍፃሜ በቆራጥ አመራራነት ለተሳተፉ ለሃገሬ መሪዎች በሙሉ!
ክብርና ሞገስ ግድቡ ዳር እንዲደርስ ላብ፣ ደምና ገንዘባቸውን ላዋሉ ዜጎች!
Hailemariam Yirga C/o Abegaz, [30.08.2025 11:47]
ክብርና ሞገስ በወትሮ ዝግጁነት የግድቡን ደህንነትና ፀጥታ ሲያስከብሩ ለነበሩት፣ ላሉትንና ወደፊትም ለሚመጡት ለሃገር መከላከያ፣ ፓሊስ፣ መረጃና ደህንነት አባላት!
ማሳሰቢያ ይህ የግል እይታየ ነው። ከዚህ በፊትም እንደማደርገው ኢትዬጵያ ውስጥ የሚፈፀሙ ጉዳዮችን ከመደበኛው እይታና አመለካከት ባለፈ ከደህንነት አንፃር(Intelligence insight) እንድንገነዘብ ለማድረግ አስቤ ያጋራኋችሁ ነው። አውቀን እንድንታረም ከማሳሳብ በዘለለ ይህን የፃፍኩት ከጀዋር ፀብና ጥላቻ ስላለኝ እንዲሁም የብልፅግና ደጋፊ ሆኘ አይደለም። ከሃገር ፍቅር ስሜት በነጨ የፃፍኩት እንድትገነዘቡት ይሁን።

