የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበጀት ዓመት 7 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ገለጹ። ተቋሙ ይህን ትርፍ ያስመዘገበው ሻዕቢያ የዘርፈውን ሳያካትት ነው። በአገር ውስጥ በረራ አገልግሎት ሲባል ማህኘት የሚገባውን ከሃያ ሚሊዮን ዶላር በላይ ማጣቱም ተመክቷል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን ያሉት የአየር መንገዱን እኤአ የ2024/25 ወይም የ2017 የበጀት ዓመት አፈፃፀምን በተመለከተ መግለጫ ሲሰጡ ነው። በመግለጫቸውም፤ በጀት ዓመቱ በአየር ትራንስፖርት ዘርፉ ተፅዕኖ ያሳደረ እንደነበር አስታውሰዋል።
በተለይም በአለም የተለያዩ ሀገራት የተከሰቱ ጦርነቶች፤ የዓለም ኢኮኖሚ ባለፈው በጀት ዓመት ከነበረበት እድገት መቀዛቀዝ እንዲሁም ሌሎች ክስተቶች የአየር ትራንስፖርት ዘርፉን የፈተኑ እንደነበሩ አስታውሰዋል።
በበጀት ዓመቱ በዓለም ላይ አምስት ቢሊዮን መንገደኞችን በአየር ትራንስፖርት ማስተናገድ እንደተቻለ ጠቁመው፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድም 19 ሚሊዮን በላይ መንገደኞች ማጓጓዙን አብራርተዋል። ከዚህ ውስጥ 15 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዓለም አቀፍ እንዲሁም 3 ነጥብ 9 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ መንገደኞች መሆናቸውን ተናግርዋል።
ከዚህም ባለፈ 785ሺህ 323 ቶን ጭነት በማጓጓዝ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የአራት በመቶ እድገት ተመዝግቧል ብለዋል። በዚህም በበጀት ዓመቱ የተመዘገበው 7 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር 8 በመቶ እድገት ተገኝቷል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፈጣን እድገት የሚል ስትራቴጂ በመከተል ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡንም ገልጸዋል። ለአብነትም በበጀት ዓመቱ ስድስት አዳዲስ ዓለም አቀፍ የበረራ መዳረሻዎችን ማስፋት መቻሉን ጠቅሰዋል።
” 28 ሚሊየን ዶላር በሃገር ውስጥ በረራ ከስረናል ” – የኢትዮጵያ አየር መንገድ
በተመሳሳይ ዋና ስራ አስፈጻሚው ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት ለቀረበላቸው የቲኬት ዋጋ መጨመርና ተያያዥ ጉዳዮች ምላሽ ሲሰጡ የተለያዩ ጉዳዮችን ዳሰዋል። በኤርትራ ሻዕቢያ ከዘረፈው ገንዘብም ምላሽ ሰጠተዋል።
” የዓለም አቀፍ በረራዎች ትኬት ኮምፒውተር ውስጥ በዶላር ነው የተጻፈው ሰው ትኬት ሲገዛ በዕለታዊ የዶላር ምንዛሬ ተመን ነው ይህንን ምንም ልናደርግ አንችልም” በለዋል።
የሃገር ውስጥ በረራ ግን በብር ነው የተጻፈው ባለፈው ዓመት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ወቅት አልጨመርንም የዶላር ምንዛሬ ዋጋው ሁለት እጥፍ ነው ያደገው በሃገር ውስጥ በረራ ክፍያ ላይ ግን ጥቃቅን ማሻሻያ ብቻ ነው ያደረግነው።ብ፤እዋል። በዚህ አግባብ እንደማይቀጥል ከተቋሙ የአሰራር ደንብና ግዢ አንጻር ማብራሪያ በመስጠት አስታውቀዋል።
“የኢትዮጵያ አየር መንገድ 28 ሚሊየን ዶላር በሃገር ውስጥ በረራ ከስሯል ምክንያቱም አውሮፕላኖች የሚገዙት በዶላር ነው ፣ የተከራየነውን አውሮፕላን የምንከፍለው በዶላር ነው፣ የመለዋወጫ እቃ የምንገዛው በዶላር ነው፣ የነዳጅ ዋጋ አድጓል” ሲሉ አየር መንገዱ እንዳይጎዳ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት አመልካተዋል።
የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ አየር መንገዱ በኤርትራ ባንክ ያለውንና የተዘረፈውን ገንዘብ ማንቀሳቀስ እንዳይችል እንደታገደ መግለጻቸው ይታወሳል።
” ወደ ኤርትራ በረራ አቁመናል በኤርትራ አየር ክልል ግን እየበረርን ነው የሃገሪቱ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጋር በዚህ ጉዳይ ምንም ችግር የለበትም ” ነው ያሉት።
አክለውም ” ፈቅደውልናል ከኢትዮጵያ ስንወጣም ወደ ኢትዮጵያ ስንገባም የኤርትራን የአየር ክልል አንዳንዴ ጊዜ የሱዳንን አየር ክልል እየተጠቀምን እየሰራን ነው ” ብለዋል።
የተያዘውን ገንዘብ በሚመለከት ግን ” ገንዘባችን አሁንም እንደተያዘ ነው በፍርድ ቤት ለማስለቀቅ ሙከራ አድርገን ነበር ነገር ግን በተለያየ ምክንያት ገንዘባችንን ሊያስለቅቅልን አልቻለም የፖለቲካ ውሳኔ ይፈልጋል ” ሲሉ ነው ያስረዱት።
በበጀት ዓመቱ 13 አዳዲስ አውሮፕላኖች ተገዝተው ስራ ላይ ውለዋል፤ 4 ቱ ቦይንግ 3 ቱ ኤርባስ ናቸው ”
የአየር ትራንስፖርት ኢንዱስትሪው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳደሩ ብዙ ክስተቶች የተመዘገቡበት ዓመት ነበር በተለይ መካከለኛው ምስራቅ የነበረው አለመረጋጋት፣ የሱዳን ጦርነት ፣የራሽያ እና ዩክሬን ጦርነት ፣ ዲሞክራቲክ ሪፕብሊክ ኮንጎ ጦርነት በመኖሩ በረራዎቻችን ተስተጓጉለው እንደ ነበር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።
የአሜሪካ መንግስት የተለያዩ ህጎችን በማውጣቱ ምክንያት የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ እክል ፈጥሮ ቢቆይም፣ ተጽዕኖዎችን በመቋቋም የአየር ትራንስፖርት ኢንዱስትሪው በአጠቃላይ 5 ቢሊየን ደንበኞችን ማጓጓዝ መቻሉን አቶ መስፍን ጠቅሰዋል። ከዚህ ስሌት አንጻር የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጥቅሉ ሲታይ የተሻለ አፈጻጸም የነበረበት ነው ማለት እንደሚቻል አቶ መስፍን ገልጸዋል።
አክለውም በበጀት ዓመቱ አስራ ሶስት አዳዲስ አውሮፕላኖችን ማስገባታቸውን፣ ከገቡት ውስጥ አራቱ ቦይንግ ሶስቱ ኤርባስ መሆናቸውን ዋና ስራ አስፈጻሚው አመልክተዋል። ። 15.2 ሚሊየን የውጭ ደንበኞች ፣3.9 ሚሊየን የሃገር ውስጥ ደንበኞች በድምሩ 19 ሚሊየን ደንበኛች፣ እንዲሁም 785,323 ቶን ካርጎ ጭነት ማጓጓዝ መቻሉን አስረድተዋል።

