Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  POLITICS  አማራ ክልል ! ከኢሰመኮ ዓመታዊ ሪፖርት እንደወረደ
POLITICS

አማራ ክልል ! ከኢሰመኮ ዓመታዊ ሪፖርት እንደወረደ

Ethioreview newsEthioreview news—August 4, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የኢሰመኮ የመንግሥት ኃይሎችና የፋኖ ታጣቂዎች ፈጸመውታል ያለውን በቀን፣ ቦታና በወራት ለይቶ አጥፊውን በመለየት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል። በሪፖርቱ ሕዝብ ላይ የደረሰውን የነፍስ ጭምሮ የንብረት ጉዳት በሪፖርቱ ተካቷል።

  • በአዊ ብሔረሰብ ዞን፣ ወንጀላ ቀበሌ ሰኔ 5 ለሰኔ 6/ 2016 ዓ.ም. አጥቢያ ሌሊት ላይ በመንግሥት ኃይሎች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን ፋኖ አባላት መካከል የተደረገውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ የመንግሥት ኃይሎች በ5 ሰዎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል፡፡

  • በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ አባላት መካከል ሰኔ 17/2016 ዓ.ም. ሰሜን ጎጃም ዞን፤ አዴት ከተማ ላይ በተካሄደ የትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች ተገድለዋል። በመንግሥት ኃይሎች ከ3 ወር በፊት ተይዘው ካምፕ ውስጥ ታስረው የነበሩ 3 ፋኖ አባላት ተገድለዋል። የፋኖ አባላት በቁጥጥር ሥር አውለዋቸው የነበሩትን ቢያንስ 8 የሚሊሻና የአድማ ብተና አባላት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ተገድለዋል፡፡
  • የፋኖ አባላት ጎንዘር ቋራ ወረዳ በአብተጋሆ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ 23 ሲቪል ሰዎችን አፍነው ወደ ቴዎድሮስ ከተማ በመውሰድ የተወሰኑት ሲመለሱ ሌሎችን ገድለዋል፡፡
  • በሰሜን ሸዋ ዞን፣ ጣርማ በር ወረዳ፣ ከደብረ ሲና ከተማ ወጣ ብላ በምትገኝ “ሾላ ሜዳ” በተባለች ቦታ ሰኔ 19/2016 ዓ.ም. የመንግሥት ኃይሎች እና የፋኖ አባላት መካከል በተካሄደ ግጭት በተለያዩ ምክንያቶች በ15 ሰዎች ላይ ግድያ ተፈጽሟል፡፡
  • ሐምሌ 5/2016 ዓ.ም. በሰሜን ወሎ ዞን፣ ጉባ ላፍቶ ወረዳ፣ ውድመን ቀበሌ ላይ የትጥቅ ግጭት መካሄዱን ተከትሎ በአካባቢው ከነበረው የመንግሥት ኃይል በተተኮሰ የጦር መሣሪያ 7 ሰዎች ተገድለዋል፡፡
  • ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም. ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ ሜጫ ወረዳ በሚንቀሳቀሰው የፋኖ አባላት 17 የአካባቢው ነዋሪዎችን ይዘው በመውሰድ በማግስቱ ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ከእነዚህ ውስጥ 4 ሰዎች ተገድለው አስክሬናቸው ተጥሎ ሲገኙ የቀሩት ሰዎች ደግሞ ገንዘብ በመክፈል ከቀናት በኋላ ተለቀዋል፡፡
  • በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ፣ ዶማ በተባለ አካባቢ የነበረውን ግጭት ተከትሎ ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂ አባል ቆስሎ 2 ወንድሞቹ ሊያነሱት ሲሄዱ 3ቱም ሰዎች በመንግሥት ኃይሎች ተገድለዋል።
  • በሰሜን ጎጃም ዞን፣ ሰሜን ሜጫ ወረዳ፣ ወተት ዓባይ ቀበሌና በአካባቢው በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ አባላት መካከል ከነሐሴ 6 እስከ 7/2016 ዓ.ም. ከተካሄደ ውጊያ ተከትሎ በመንግሥት ኃይሎች 7 ሰዎች ተገድለዋል።
  • ነሐሴ 14/2016 ዓ.ም. በባሕር ዳር ከተማ፣ በተለምዶ ቀበሌ 5 በግ ተራ አካባቢ የመንግሥት ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በ2 ሰዎች ላይ የሞት እና 10 የአካል ጉዳት ደርሷል።
  • ጳጉሜን 2/2016 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ አስተዳደር፣ አዘዞ ጸዳ ክፍለ ከተማ፣ ጸዳ ቀበሌ ጤና ጣቢያ አካባቢ 1 የመንግሥት የጸጥታ አባል ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የመንግሥት ኃይሎች ቢያንስ 11 ሰዎችን መግደላቸው ተረጋግጧል።
  • መስከረም 6/2017 ዓ.ም. በሰሜን ጎንደር ዞን፣ ደባርቅ ከተማ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ አባላት መካከል ከተካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ ዒላማቸውን ባልጠበቁ ተኩሶች እና በተባራሪ ጥይቶች ቢያንስ 29 ሰዎች ተገድለዋል።
  • ከመስከረም 6 እስከ 7/ 2017 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ መካከል በነበረው የትጥቅ ግጭት በሁለቱም ወገን በነበረው የተኩስ ልውውጥ ምክንያት ሕፃናትን እና ሴቶችን ጨምሮ ቢያንስ 10 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል። ተጎድቶ ሆስፒታል ከገቡ ሰዎች 1 ሰው ሕይወቱ አልፏል፡፡
  • መስከረም 8/2017 ዓ.ም. በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ስናን ወረዳ በፋኖ አባላት ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት አካባቢ 2 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንን ከመኖሪያ ቤታቸው በመውሰድ የገደሏቸው ሲሆን በሌሎች 4 መምህራን ላይ ድብደባ ፈጽመዋል። በመምህራኑ ላይ የተፈጸመው ግድያ እና ድብደባ በ2017 ዓ.ም. ትምህርት ለማስጀመር ካደረጉት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ነው።
  • መስከረም 23/ 2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ በደቡብ ጎንደር ዞን፣ ጉና በጌምድር ወረዳ፣ ክምር ድንጋይ ከተማ በመንግሥት ኃይሎች የተተኮሰ የጦር መሣሪያ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ግቢ ላይ በማረፉ 2 የቤተሰቡ አባላት ሲገደሉ ሌሎች 2 ሕፃናት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
  • መስከረም 26/ 2017 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን፣ በቋራ ወረዳ የፋኖ አባላት 8 ሰዎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል፡፡
  • ኅዳር 11/ 2017 ዓ.ም. በማእከላዊ ጎንደር ዞን፣ ጎንደር ዙሪያ ወረዳ፣ ለምባ አርባይቱ ቀበሌ፣ አርባ ተንሳይ ጎጥ በመንግሥት ኃይሎች ላይ የደፈጣ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ የመንግሥት ኃይሎች 3 ሰዎችን ገድለዋል፡፡
  • ታኅሣሥ 3/2017 ዓ.ም. በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ ገነተ-ማርያም ቀበሌ አርክን በተባለ ቦታ 5 ሰዎች በመንግሥት ኃይሎች ተገድለዋል፡፡
  • በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቡ ወረዳ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች መጋቢት 2/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ 3 ሰዎችን (የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ፣ የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ እና ሾፌር) ለሥራ ጉዳይ ከወረዳው ዋና ከተማ ቢስቲማ ወደ ቦኬክስ ሲሄዱ ልዩ ቦታው ጠቢሳ ከሚባል ቦታ ላይ ተኩስ ከፍተው ገድለዋቸዋል።
  • መጋቢት 8/ 2017 ዓ.ም. በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች የይካሆ ቀበሌ ነዋሪዎችን ” ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ፋኖን ትዋጋላችሁ ” በሚል የጦር መሣሪያ ለመውሰድ ሲሞክሩ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ታጣቂዎች መጋቢት 11/2017 ዓ.ም. በድጋሚ ወደ ይካሆ ቀበሌ በመግባት በፈጸሙት ጥቃት 6 ሰዎችን ገድለዋል።
  • መጋቢት 11/ 2017 ዓ.ም. በሰሜን ጎጃም ዞን፣ ሰሜን ሜጫ ወረዳ መራዊ ከተማ የፋኖ አባላት ከቀኑ 6:00 እስከ 7:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ከተማው ዘልቀው በመግባት 4 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንን ጨምሮ 6 ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል።
  • መጋቢት 28/2017 ዓ.ም. ከቀነ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ በአማራ ክልል፣ ደቡብ ጎንደርዞን፣ ፎገራ ወረዳ፣ ዓለም በር ከተማ የፋኖ ታጣቂዎች ዘልቀው በመግባት 2 የአባይ ባንክ የጥበቃ ሠራተኞችን ገድለዋል። አባይ ባንክ ላይ ዘረፋ ፈጽመዋል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በፀደይ ባንክ ላይ የዘረፋ ሙከራ አድርገዋል።
  • ግንቦት 2/2017 ዓ.ም. ከንጋቱ 11፡30 ሰዓት ጀምሮ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ጭልጋ ወረዳ፣ ኳበር ሎምጌ ቀበሌ የፋኖ ታጣቂዎች 2 ሰዎች ገድለዋል፤ 4 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት አድርሰዋል፤ የቤት እንስሳ ዘርፈው ወስደዋል፣ 7 የመኖሪያ ቤቶችን  እንዲሁም 34 የሚሆኑ የመንደሩ አባወራዎችን አፈናቅለዋል።

POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
በግብፅ የቀብር ስፍራዎች 3ሺህ ዓመት ያስቆጠረ ማር ተገኘ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 7.6 ቢሊዮን ዶላ አተርፈ፤ ሻዕቢያ የዘረፈውን ገንዘብ አልመለሰም
Related posts
  • Related posts
  • More from author
POLITICS

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

March 28, 2026
POLITICS

አስቸኳይ የአርበኛነት ጥሪ ለኢትዮጵያን

March 4, 2026
POLITICS

ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡ

January 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2