በሶስተኛ ወገን ግፊትና ትስስር በአማራ ክልል ከሁለት ዓመት በፊት የተጀመረውን የፋኖ እንቅስቃሴ ተከትሎ ከአገር የኮበለሉ የጎጃም ባለሃብቶች ወደ አገር ቤት ለመመለስ እንቅስቅሴ ማድረጋቸው ተሰማ። ውሳኔው ረብሻውንና ቀውሱን በሚፍለጉት ዙሪያ የመርዶ ያህል እንደሆነ ተመልክቷል። “ከዚያስ” የሚል ጥያቄ የሚያነሱ አሉ።
የኢትዮሪቪው ታማኝ የመረጃ ምንጮች እንዳሉት የተጠቀሱት “እውቅ” ባለሃብቶች ወደ አገራቸው ለመመለስ እንቅስቃሴ ከጀመሩ ሰነባብቷል። ጅማሮው ተስፋ የሚሰጥ ሆኗል። በተቃራኒው ዜናው የክልሉንና የአገሪቱን ብጥብጥ ለሚፈልጉና ከጀርባ ሆነው ለሚያቀጣጥሉ አስደንጋጭ እንደሚሆን ተመልክቷል።
በስም ከሚታወቁ የጎጃም ባለሃብቶች መካከል ከፋኖ እንቅስቃሴ ጀርባ መሆናቸውን አደባባይ ወጥተው የመሰከሩ መኖራቸው አይዘነጋም። ከፋኖ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የሚሰሩ ሚዲያዎችንና በሚዲያው ላይ የሚሰሩትን ወርሃዊ ደሞዝ ከመስጠት ጀምሮ መቋቋሚያ ሲሰጡ የነበሩ መኖራቸውንም በተደጋጋሚ መገለጹ አይዘነጋም።
ኢትዮ 360 ሲመሰረት ዳጎስ ያለ መቋቋሚያ ከሰጡ በሁዋላ፣ ገንዘቡ ከዱባይ የተላለፈለት አንድ የሚዲያው አባል ገንዘቡን ወደ ራሱ ኪስ ማዞሩን ተከትሎ ከፍተኛ ረብሻ መነሳቱና ጉዳዩ አደባባይ እስከመውጣት መድረሱም የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።
በዚህን መሰሉና ቀደም ሲል በህልውናው ትግል ወቅት ጀምሮ ዝግጅት የነበራቸው አካላትን ሲደግፉ የነበሩት የጎጃም ባለሃብቶች ከአገር የወጡት በህቡዕ ሲያከንባውኑ የነበረው ድጋፍ በመታወቁ መሆኑም አይዘነጋም።
አሁን ላይ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የአገሪቱን ፖለቲካ በመገምገም ባለሃብቶቹ በምህረት ወደ አገራቸው ገብተው በሰላማዊ መንገድ ለመስራት ከውሳኔ መድረሳቸው ተሰምቷል። ሁሉም ይሁኑ የተወሰኑት ባይገለጽም በዚሁ ውሳኔያቸው መሰረት ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንዲደርስ ዕቅድ መያዙን የዜናው ባለቤቶች ነግረውናል።
ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ በሰላም ከሚኖርበት መንደሩ ሳይቀር ሁከት፣ ዝርፊያ፣ ግድያ፣ እገታ፣ የማዳበሪያ አቅርቦት፣ ሕክምና፣ ትምህርት ቤት፣ ማህበራዊ አገልግሎት፣ የትራንስፖርት አቅርቦት፣ የሸቀጦች ፍሰት ወዘተ ለተናጋበት የአማራ ሕዝብ ዜናው በጎ ነገሮችን ይዞ እንደሚመጣ ዜናውን ያካፈሉን አስታውቀዋል።
እንደ እነዚሁ ሰዎች ገለጻ ከሆነ የባለሃብቶቹ መመለስ ብረት ባነሱትና ብረት ያነሱትን ተቧድነው በሚደግፉ ሚዲያዎች አማካይነት የሚሰራጨውን ብጥብጥ የሚያባብስ አካሄድ ያስተነፍሳል። ምን አልባትም የተወሰኑትን ሊያቆማቸው ይችላል። ከምንም በላይ ግን በአገር ውስጥ ይህ ነው ሊባል የማይችል እፎይት እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
በአማራና ኦሮሚያ ክልል ያለው የትጥቅ ትግል ፖለቲካዊ ግብ የሌለው የንግድ ጉዳይ እንደሆነ፣ በርካቶች “ትግል” የሚባለውን አግባብ ለገንዘብ መሰብሰቢያ መጠቀሚያ የሚጠብቀሙበት መሆኑ በስፋት እየተገለጸና እይታመነበት መምጣቱን በርካታ ሰለባዎች እያስታወቁ ነው። በውጊያ ሰላማዊ ሰዎችን ህይወት ጭምር እየበላ ያለው ውጊያ ሕዝቡን ክፉኛ ያሰላቸው መሆኑም በተለያዩ መድረኮች በተደጋጋሚ እየተገለጸ ይገኛል።
በአንዳን ሕዝባዊ ስብሰባዎች ላይ ሕዝብ ” አሁንስ የት እንሂድ” በማለት መንግስትን ሲማጸን መስማት የተለመደ ሆኗል። እነዚህ ዜጎች በየአቅጣጫው “የሰላም ያለህ” እያሉ በሚያነቡበት ወቅት የጎጃም ባለሃብቶች ወደ አገራቸው ለመመለስ ያሳዩት ተነሳሽነት ሊደገፍና በአስቸኳይ እለባት ሊያገኝ እንደሚገባው ዜናውን የነገርናቸው ገልጸዋል።
አቶ ደመቀ ከኢሳት የተወሰኑ ጋዜጠኖች ጋር ከበፊት ጀምሮ ግንኙነት እንዳላቸው፣ ከኃላፊነታቸው እስከ ለቀቁበት ቀን ድረስ የዝግ ስብሰባዎችን ሚስጢር ባማሾለክ የሚጠረጠሩት አቶ ደመቀ መኮንን ይህን ዜና በምን መልኩ እንደሚመለከቱት ለጊዜው የያወቀ ነገር እንደሌለ የዚናው ሰዎች ገልጸዋል።
እነዚሁ አካላት አቶ ደመቀ አማራ ክልልን በፓርቲው መሪነትና በጸጥታ ዘርፍ ለረዝም ጊዜ የመሩና የክልሉ መዋቅር ሙሉ በሙሉ እጃቸው ላይ እንደነበር የሚገልጹት የዜናው ሰዎች፣ እሳቸው ከጎጃም ባለሃብቶች ጋር ከነበራቸው የጠበቀ ግንኙነት አንጻር አማራ ክልል አሁን ለደረሰበት ቀውስ እንዳይጋለጥ ማድረግ ይችሉ እንደነበር ይገልጻሉ።
እነዚህ ውገኖች ብቻ ሳይሆን በርካታ የክልሉ ነዋሪዎችና የራሱ የክልሉ ባለስልጣናት ይህን እውነት ይጋራሉ። ዜናውን ያጋሩን እንደሚሉት አቶ ደመቀ አሁን ላይ ስለተጀመረው እንቅስቃሴ ምንም የሚያውቁት ነገር፣ ወይም እጃቻቸው የሌለበት መሆኑ ቢጠቅሱም ራሳቸውን ለመከላከል ሲሉ ምን አልባትም ደስተኛ ሊሆኑ እንደማይችሉ ከሃብት ጋር አያይዘው ገልጸዋል። ዝርዝሩን ወደፊት እንደ አስፈላጊነቱ እንደሚያቀርቡ አለመክተዋል። አቶ ደመቀ ብሽልማት አሸኛኘት እንደተደረገላቸው አይዘነጋም።



