150 የሸኔ አባላት በተደረገላቸው የሠላም ጥሪ መሰረት በሰላማዊ መንገድ እጅ ሰጡ፡፡
እንደተለመደው “ሕዝብ በድለናል” ሲሉ ይቅርታ ጠይቀዋል። ዛሬ ላይ ኦሮሞ ጥይት ተኩሶ። በረሃ ወርዶ የሚስፈጽመው አንድም ጥያቄ እንደሌለ ደጋግመው የሚናገሩ ውሳኔውን አድንቀው ሌሎችም ተመሳሳይ ውሳኔ እንዲወስኑ ጥሪ አቅርበዋል።
በምዕራብ ጉጅ ዞን 150 የሸኔ አባላት የተደረገላቸውን የሠላም ጥሪ በመቀበል በሰላማዊ መንገድን እጅ መስጠታቸውን ተከትሎ በአቀባበሉ ላይ የተገኙ ለኢትዮሪቪው እንዳሉት፣ ታጣቂዎቹ ያደረሱት በደልና ቀውስ ከፍተኛ ነው።
እጃቸውን ከሰጡት መካከል “ይቅርታ” በማለት ሕዝብን መበደላቸውን ጠቅሰው ይቅርታ ጠይቀዋል። የበደሉትም ሕዝብ መልሰው እንደሚክሱ አስታወቀዋል።
“የደቡብ ዕዝ ኮር ግዳጅ እየተወጣበት በሚገኘው ምዕራብ ጉጅ ዞን 150 የሸኔ አባላት የተደረገላቸውን የሠላም ጥሪ በመቀበል በሰላማዊ መንገድን እጅ ሰጥተዋል” ሲል ዜናውን ይፋ ያደረገው የአገር መከላከያ እጅ ለሰጡት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ህዝብ፣ አስተዳደሩና የሰራዊቱ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የደቡብ ዕዝ ኮር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል አባዲ ልዑል፣ የምዕራብ ጉጂ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አዶላ ሂርጳዬ ፣የዞንና የወረዳ አመራሮች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እጅ ለሰጡ የሸኔ አባላት አቀባበል ባደረጉበት ወቅት የኮሩ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል አባዲ ልዑል፣ እና የምዕራብ ጉጂ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አዶላ ሂርጳዬ መልዕክት አስተላለፈዋል።
ተናጋሪዎቹ በሠላማዊ መንገድ እጅ የሠጡ የኦነግ ሸኔ አባላት ሠላም መርጠው እና የሠላም ጥሪውን ተቀብለው መግባታችው ትክክለኛ አማራጭ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ ለሠላም መሥራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
በሰላማዊ መንገድ የገቡት የሸኔ አባላትም እስካሁን ድረስ በሀገር እና በህዝብ ላይ ለፈፀሙት ያልተገባ ድርጊት መፀፀታቸውን ገልፀው ከእንግዲህ ሠላምን የማሥቀደም ሥራ እንደሚሠሩና ለሠላም እንደሚቆሙ ተናግረዋል፡፡
በዕለቱ የዞንና የወረዳ እንዲሁም የሠራዊቱ አመራሮች አባገዳዎች የአካባቢው ነዋሪዎች መገኘታቸውን ያስታወቀው የኮሩ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው።
በቅርቡ የኦሮሞ ምሁራን ሕብረት በሚል በአሳብ የማይግባቡ ተሰባስበው ኢትዮጵያን ቅኝ ገዢ በማለት ሲስማሙ የእነዚህኑ ታጣቂዎች አመራር መጋበዛቸው አይዘነጋም። ይህንኑ ስብሰባ ተከትሎ መንግስት የወራት ዕድሜ እንደቀረው አስታወቀው ነበር።
ክልሉ በቅርቡ እንዳስታወቀ ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እጅ ሰጥተው ወደ ሰላማዊ ህይወት መመለሳቸው፣ የቀረው በየስርቻው ያለ ዘራፊ ቡድን እንደሆነ ማመልከቱ አይዘነጋም።
እነ ጃዋር ይህን የክልሉን መግለጫ በማጣጣል ” መንግስት የሚያስተዳድረው የኮሪዶር መንገድ ያለበትን አካባቢ ብቻ ነው” በማለት ደጋግመው ማስታወቃቸው ይታወሳል።
እነሱ ይህን ሲሉ የክልሉም ሆነ የፌደራል ባለስልጣናት የውጭ አገር ከፍተኛ ባለስልጣን በመያዝ በክልል በጎዳና ላይ ከሕዝብ ጋር መታየታቸው፣ በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትግራይ በስተቀር በተለያዩ ክልሎች ሲዛወሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በተደጋጋሚ እየተሰራጨ ነው።

