Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  “መከላከያ ቢፈርስስ?” ኢትዮ ሚዲያ ፎረም ኢትዮጵያን ተቋም አልባ የማድረጉን ዕቅድ ነገረን
NewsOPINION

“መከላከያ ቢፈርስስ?” ኢትዮ ሚዲያ ፎረም ኢትዮጵያን ተቋም አልባ የማድረጉን ዕቅድ ነገረን

Ethioreview newsEthioreview news—August 18, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

“ኢትዮ ፎረም” ገና “ለውጡ” በመጣ ማግስት ከሚያዝያ 2010 ጀምሮ የቀድሞው የኢትዮጵያ የመረጃ እና የደህንነት ተቋም አባላት ከህወሐት ፅህፈት ቤት ጋር በመቀናጀት፤ ከ”ለውጡ” በፊት “ENN” ይባል ከነበረው የቴሌቪዥን ጣቢያ የተመለመሉ ሁለት ወጠጤ “ጋዜጠኞችን” ከፊት አሰልፎ አንዴ ከአዲስ አበባ፣ ሌላ ጊዜ ከመቐለ አሁን ደግሞ ከአውሮፓ ከተሞች “በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረቱ ልብ ወለዶችን” (black propaganda) ያለማቋረጥ እያሰራጨ ይገኛል

እሺታን ማምረት፡ ከ’ክሊክ’ እና ‘ሼር’ ፖለቲካል-ኢኮኖሚ ባሻገር Manufacturing Consent 2.0፡ Beyond The Political Economy of “Click”, “View”, and “Share”

ኖአም ቾምስኪ እና ኤድዋርድ ኸርማን እ.አ.አ. በ1988 ሰለ ሚዲያ/ኮሚዩኒኬሽን የፃፉት አንድ ምርጥ (seminal) መፅሐፍ አለ። “Manufacturing Consent፡ The Political Economy of the Mass Media” የሚል።በአጭሩ “እሺታን ማምረት/መፈብረክ” ልንለው እንችላለን። የመፅሀፉ ዋነኛ ጭብጥም የተቀመረ እና የተጠና መረጃ በመጋት ህዝቦችን “በእሺታ” ለመግዛት/ለማንበርከክ የብዙሐን መገናኛ ዘዴዎች (the mass media) የሚጫወቱትን ወሳኝ ሚና ማተት ነው። እንደ ዋነኛ ምሳሌም (case study) መፅሐፉ የአሜሪካ ሚዲያዎች ላይ ያተኩራል። እነዚህ ሚዲያዎችም (የተቀናጀ ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት) እንዴት ጠንካራ እና ውጤታማ የርዕዮተ አለም መሳሪያ፤ የስርአቱ ቀጣይነት ማስረገጫ ሆነው እንደሚሰሩ ያትታል።

ይህ መፅሐፍ የተፃፈው በማስ ሚዲያ ወርቃማ ዘመን በመሆኑ ይዘቱን ከሶሻል ሚዲያ ዘመን ጋር ማጣጣም ይጠይቃል። ነገር ግን በመፅሀፉ ውስጥ የተዘረዘሩት የፕሮፓጋንዳ ሞዴል ቴክኒኮች፤ በ”click”፣ “view” እና “share” ከሚገኝ financial gain ላይ ለተመሰረተው ይሄኛው ዘመንም ይሰራሉ። ቴክኒኮቹም ባለቤትነት (ownership)፣ ማስታወቂያ ማሰራጨት (adverising)፣ ምንጭ ማጣቀስ (sourcing)፣ የአፀፋ ትችት መሰንዘር (flak) እና ርዕዮተ-አለማዊ ወገንተኝነት (ideological commitment) ናቸው። [ያላነበባችሁት ካላችሁ መፅሀፉን እንድታነብቡ እየጋበዝኩ፤ ከዚህ በላይ ወደዝርዝሩ ከመግባት እቆጠባለሁ። የፅሁፌ መልዕክት የተዋቀረው ግን መፅሐፉ በተዋቀረበት ዋና ጭብጥ “manufacturing consent” ላይ ተመስርቶ፤ ግን ደግሞ ያለንበትን አውድ (context) ባገናዘበ መልኩ መሆኑን አስቀድሜ እገልፃለሁ። ይህንንም Manufacturing Consent 2.0 ብየዋለሁ]።

More stories

በትግራይ አምስት ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ማምረት ጀመሩ፣ አንዱ ኤክስፖርት ጀምሯል

March 9, 2021

ብሔራዊ ባንክ በዱባይ ያሉ ድርጅቶን ተጠንቀቁ አለ

August 6, 2025

ኤርትራዊያን ስደተኞችን ከትግራይ ክልል ለማስወጣት የአደጋ ጊዜ እቅዶች መሰናዳቸውን የመንግስታቱ ድርጅት ገለጸ

August 5, 2021

የኢትዮጵያና የሶማሊያ መሪዎች የፊት ለፊት ንግግር ለማካሄድ ቱርክ አንካራ ገቡ፤ ኤርዶጋን የሁለቱን አገራት ውዝግብ ለመቋጨት አቅደዋል

December 11, 2024

…… ልብወለድ እና መኮርኮሪያ በመጨመር ጆሮ-ጠገብ ለሆኑ ሰነፎች እና መረጃን ለመመርመር ጊዜና አቅም ለሌላቸው ባተሌዎች በሚመች መልኩ በማቅረብ፤ ሀገሪቱ “ከመአት እና ከመርገምት” ውጪ ምንም የሚወራ ነገር የሌለባት እስኪመስል ድረስ የምረጃ፣ የፍረጃ እና የማወናበጃ ስራ እየሰራ ይገኛል። ህወሐት ጥቅምት 2013 ከከፈተው ጦርነት በፊት “የከፋፍለህ-ግዛ”፣ በጦርነቱ ወቅት የስነ-ልቦና ጦርነት (Psyop)፣ ጦርነቱ በፕሪቶሪያው ስምምነት ከቆመ በኋላ ደግሞ አጠቃላይ እና ሴንሴሽናል የፕሮፓጋንዳ ጦርነት (comprehensive sensational infowar) በማድረግ ላይ ይገኛል

ምስል – ኢትዮ ፎረም የሚባለው የትህነግ አፍ እንደሆነ የሚታወቀው የዩቲዩብ ገጽ መከላከያ ቢፈርስስ የሚለውን የሰባቱ ዓመት የተቀነባበረ ሴራ የመጨረሻ ግብ ይፋ ሲያደርግ የኢትዮጵያን መከላከያ ኢትዮጵያዊ ይዘት እንደሌለው ለማሳየት የተጠቀመበት ቅንብር ምስል ነው። ላለፉት ስድስትና ሰባት ዓመት “የአብይ ሰራዊት፣ የብርሃኑ ጦር” እየተባለ በመናበብ የአገር መከላከያ ላይ ሲዛበቱበት የቆዩት ቅጥረኞች ሻዕቢያና ወያኔ “የደርግ” ብለው ያፈረሱትን የአገር መከላከያ ታሪክ ለመድገም ካላቸው ህልም የተነሳ ነው። ይህ እንዲሆን የሚፈቅድ ያለ መስሏቸው !! ህልሙን ግን ልብ ማለት አግባብ ነው። እየተሰራ ያለው ስራና ዘመቻ ሁሉ መዳረሻው ይህ ነው።

በጥናት የተደገፈ statistical data ማቅረብ ባልችልም፤ ብዙዎች ስለሀገራቸው በንቃት የሚከታተሉ ዜጎች መረጃ የሚያገኙት ከማህበራዊ ሚዲያ (Facebook፣ YouTube, X/Twitter, etc) ነው ብዬ አስባለሁ። The era of the mainstream media’s hegomony over news and information, as we knew it, is gone! ይህ ሁኔታ የ”ተራ ዜጎችን” እና “የዜጎች ጋዜጠኝነትን” (“citizen journalism”) ዕድል እና አቅም አዳብሯል። የፈጠራ፣ የግብይት እና የተግባቦት መድረኮችን ፈጥሯል። አሳልጧል። በኤሊቶች እና በብዙሃኑ መሐል ያለውን የመረጃ acess እና ሚዛን ክፍተት (inequality) አጥብቧል። የዚያኑ ያህል ተጠያቂነት የሌለበትን፣ ጥላቻ እና ሽብር ያለ ከልካይ የሚዘራበትን፣ ሀገር እና ህዝብ አደጋ ላይ የሚወድቁበትን state of anarchy ፈጥሯል። ምንጩ ባልታወቀ እና ምንም ወይም በቂ ማስረጃ ባልቀረበበት “መረጃ/ዜና” የግለሰቦች፣ የማህበረሰቦች፣ እና የሀገራት ጥቅም እና ደህንነት ለአደጋ ተጋልጧል። ግለሰቦች እና ህዝቦች የተናጠልም ሆነ የጋራ ስነ-ልቦነዊ መረጋጋት እንዳይኖራቸው “ማህበራዊ ዕረፍት ለመንሳት” (societal destabilization) የተጠና እና የተቀናጀ የምረጃ ዘመቻ ሰላባ እንዲሆኑ ቀላል እና ርካሽ መሳሪያ ሆኗል። በዚህም ምክንያት ሀገራት እና ህዝቦች ቾምስኪ እና ኸርማን ከተቹት ከmainstream mediaው ዘመን በከፋ ሁኔታ የምረጃ predatory ፖለቲካል-ኢኮኖሚ ታርጌት ተደርገዋል/ሆነዋል።

በኢትዮጵያም የሶሻል ሚዲያን ፀጋና መቅሰፍት ማስተናገድ ከጀመርን ቢያንስ አንድ አስርት አመታት አሳልፈናል። በዚህ ወቅት የኢንተርኔት ስርፀት ከትምህርት እና ሶሻል ሚዲያ መስፋፋት ጋር ተሰናስሎ ተከስቷል። በተጨማሪም ሀገሪቱን ካጋጠሟት ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እና ሽግግሮች ጋር ተገጣጥሟል። ያው የታሪክ አጋጣሚ መሆኑ ነው እንግዲህ። እናም በዚህ አውድ ውስጥ በተፈጠረ ሁኔታ የሀገሪቱ መንግስት ተቀይሯል፣ በዜጎች መሐል ማንነትን መሰረት ያደረገ መፈራራት እና ደም አፋሳሽ ግጭት ተከስቷል። ሀገሪቱ በታሪኳ ካየቻቸው አስከፊ የሆኑ የእርስ በእርስ ጦርነቶች አንዱ ተከስቷል። ውሉ ያልለየ የአማፅያን እና የሽፍቶች እንቅስቃሴ ከጀመረም ከራርሟል። “ዜና በማሰራጨት”፣ “ትንታኔ በማቅረብ” እና “ኮንቴንት” በመስራት ስም ሀገሪቱ እና ህዝቧ ከውስጥም ከውጪም የተቀናጀ ምረጃ፣ ፍረጃ እና ማወናበጃ ሰለባ እየሆኑ ነው። ዛሬ በሶሻል ሚዲያው ላይ የማይሸቀጥ እና “የማይገለጥ” ግለሰባዊ፣ ቡድናዊ እና ሀገራዊ ገመና የለም። የፖለቲካ ጥቅምን ከእይታ፣ ከክሊክ፣ እና ሼር ከሚገኘው ገንዘብ ጋር አዳብሎ ለማጋበስ የማይጣስ ምድራዊ፣ ሞራላዊ እና ሀይማኖታዊ ህግ እና ደምብ የለም።

እናም ጦቢያውያን….ይሄ ሁሉ ለሰባት አመታት የዘለቀው ምረጃ፣ ፍረጃ እና ማወናበጃ ዝም ብሎ የመጣ አይደለም። የተቀናጀ የmanufacturing consent እና psyops አካል ነው። ሀገሪቱን እና ህዝቧን ተቋም አልባ በማድረግ፤ ጠባብ ቡድናዊ ፍላጎትን እና የተቀናቃኝ ሀገራትን የፖሊሲ ግብ ለማሳካት የተወረወረ ፍላፃ ነው

የመንግስት ጥፋት እና ደካማነት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ባለፉት ሰባት አመታት ሀገራችን እና ህዝቧ ከአብራኳ በወጡ ግለሰቦች/ቡድኖች እና በባዕድ ሀገራት operatives የተጠና እና የቀናጀ የምረጃ፣ የፍረጃ እና የማወናበጃ ሰለባ መሆናቸው የአደባባይ ሀቅ ነው። ከ2010 ወዲህ በአንፃሩ ከፈትፈት ብሎ የነበረውን የማህበራዊ እና የሜንስትሪም ሚዲያ አውድ በመጠቀም የተጀመረው sociopolitical destabilization ወደ ማህበራዊ ሚዲያው በህቡዕ እና በግላጭ ጠቅልሎ በመግባት የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበረ-ፖለቲካዊ ሁኔታ እያናጋው ይገኛል። ከእነዚህ operatives አንዱ ራሱን “ኢትዮ ፎረም” በማለት የሚጠራውና በዩቲዩብ ከአንድ ሚሊየን በላይ ተከታዮች ማፍራት የቻለው የምስጢራዊ ፕሮፓጋንዳ (black propaganda) ማሽን ነው።

“ኢትዮ ፎረም” ገና “ለውጡ” በመጣ ማግስት ከሚያዝያ 2010 ጀምሮ የቀድሞው የኢትዮጵያ የመረጃ እና የደህንነት ተቋም አባላት ከህወሐት ፅህፈት ቤት ጋር በመቀናጀት፤ ከ”ለውጡ” በፊት “ENN” ይባል ከነበረው የቴሌቪዥን ጣቢያ የተመለመሉ ሁለት ወጠጤ “ጋዜጠኞችን” ከፊት አሰልፎ አንዴ ከአዲስ አበባ፣ ሌላ ጊዜ ከመቐለ አሁን ደግሞ ከአውሮፓ ከተሞች “በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረቱ ልብ ወለዶችን” (black propaganda) ያለማቋረጥ እያሰራጨ ይገኛል። ዜና ላይ ሳይቀር ልብወለድ እና መኮርኮሪያ በመጨመር ጆሮ-ጠገብ ለሆኑ ሰነፎች እና መረጃን ለመመርመር ጊዜና አቅም ለሌላቸው ባተሌዎች በሚመች መልኩ በማቅረብ፤ ሀገሪቱ “ከመአት እና ከመርገምት” ውጪ ምንም የሚወራ ነገር የሌለባት እስኪመስል ድረስ የምረጃ፣ የፍረጃ እና የማወናበጃ ስራ እየሰራ ይገኛል። ህወሐት ጥቅምት 2013 ከከፈተው ጦርነት በፊት “የከፋፍለህ-ግዛ”፣ በጦርነቱ ወቅት የስነ-ልቦና ጦርነት (Psyop)፣ ጦርነቱ በፕሪቶሪያው ስምምነት ከቆመ በኋላ ደግሞ አጠቃላይ እና ሴንሴሽናል የፕሮፓጋንዳ ጦርነት (comprehensive sensational infowar) በማድረግ ላይ ይገኛል። በዚህም ለህዝብ ተቆርቋሪ በመምሰል ህዝቡ ራሱ ማህበረ-ፖለቲካዊ መረጋጋት እንዳይኖረው ከሌሎች የየራሳቸው (የሚጣጣምም የሚቃረንም) ግብ ባላቸው ስብስቦች ከሚዘወሩ የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች ጋር እየተመጋገበ እዚህ ደርሷል። ከዚህ እና ከሌሎቹም “ሚዲያዎች” ጀርባ ያሉ አካላት ዋነኛ ግባቸው manufacturing consent ነው [ለአንዳንዶቹ የሚያስገኘው ተጨማሪ financial gain እንዳለም ሳይዘነጋ]። አላማቸው ህዝቡን በአስፈሪ ቀቢፀ-ተስፋ ውስጥ በመቀርቀር መድረሻው ወደማይታወቅ የአመፃ መቀመቅ ውስጥ ለመክተት የሚያስችል “እሺታ ማምረት” ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ (በተለይም active ግጭት ባለባቸው የአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች አካባቢዎች ያለው ዜጋ) መቼም አቻዮ ነው! በአንድ በኩል በእብሪት መሳሪያ መንግስት ላይ የመዘዙ አካላት ያስከተሏቸው ሀገራዊ ውጥንቅጦች፤ በሌላ በኩል የመንግስት ፖሊሲ እና ውሳኔ የወለዳቸው ችግሮች፤ በዚያ ላይ የምረጃ፣ የፍረጃ እና የማወናበጃ ዘመቻዎች ሳይበግረው ህዝቡ ሁሉን ችሎ “የባሰ አታምጣ” ብሎ ለመኖር እየተንገታገተ ነው። በዚህ ተስፋ የቆረጡ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ሀይሎች operatives አሁን ደግሞ የሀገሪቱን የፀጥታ እና የደህንነት ተቋማት (በተለይም መከላከያ ሰራዊቱን) ታርጌት አድርገዋል። አንዴ ሰራዊቱ “መፈንቅለ-መንግስት ለምን አይደርግም” ብለው ይብከነከናሉ። ሌላ ጊዜ “ሰራዊቱ ከክልሎች ካልወጣ” ብለው ይመፃደቃሉ። ከሰሞኑ ደግሞ እንደ ቀድሞው (ቅድመ-1983) ሰራዊት “ተሸንፎ ይፈርሳል/ቢፈርስስ?” ይላሉ።

እናም ጦቢያውያን….ይሄ ሁሉ ለሰባት አመታት የዘለቀው ምረጃ፣ ፍረጃ እና ማወናበጃ ዝም ብሎ የመጣ አይደለም። የተቀናጀ የmanufacturing consent እና psyops አካል ነው። ሀገሪቱን እና ህዝቧን ተቋም አልባ በማድረግ፤ ጠባብ ቡድናዊ ፍላጎትን እና የተቀናቃኝ ሀገራትን የፖሊሲ ግብ ለማሳካት የተወረወረ ፍላፃ ነው። በግሌ ከጠመንጃ የፀዳ የተቃውሞ ፖለቲካ ቢኖረን ኖሮ ስልጣን ላይ ያለውን መንግስት የምተችበት አንድ ሺህ አንድ ምክንያቶች አሉኝ። በአብዛኛው እየሆነ ያለው ግን በስልጣን ላይ ያለውን ቡድን ወይም መንግስት ከመተቸት፣ ከመቃወም እና ከመዋጋት ያለፈ እና የፀነፈ በሀገር ብሄራዊ ጥቅም እና ደህንነት ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው።

በዚህ አውድ ውስጥ የሀገሪቱን የደህንነት ተቋማት፤ በተለይም የመከላከያ ሰራዊቱን በተመለከተ የሚደረግን ወታደራዊም ሆነ ፖለቲካዊ ዘመቻ ራሱን የሚያከብር ዜጋ ሁሉ ሊቃወመው እና ሊመክተው ይገባል። ከ34 አመታት በፊት ደርግን በመታገል ስም ሀገራችን አንጡራ ሀብቷን ያፈሰሰችበትን መከላከያ ሰራዊት፣ የብዙዎች ነፍስ የተገበረበትን የባህር በር፣ በብዙ ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ትግል የተከበረውን የግዛት አንድነት እንድናጣ እንደተደረገ ሁሉ፤ ዛሬም ያ እንዲደገም መፍቀድ የለብንም። መንግስትን በመታገል ስም landlocked ተደርገናል። ትልቋን ሀገር በሚጢጢ ጎረቤት ላይ ጥገኛ እንድትሆን ተሲሮብናል። በተመሳሳይ ዘመቻ ሌሎች ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ጥቅሞቻችንን (የአባይን ወንዝ የመጠቀም መብታችንን ጨምሮ) እንድንነጠቅ መፍቀድ የለብንም!

ሲያስፈልግ መንግስትን ጉድለቱን ነቅሰን በማስረጃ እና በመረጃ እንተቻለን። የሀገራችንን ብሄራዊ ጥቅም እና ደህንነት ግን ለማንም አሳልፈን አንሰጥም! በብሄራዊ ጥቅም እና ደህንነት ጉዳይ ገለልተኝነትም (neutrality)፤ ኢ-ወገንተኝነትም (impartiality) የለም! እኔና መሰሎቼ የሀገራችንን ብሄራዊ ጥቅም እና ደህንነት በተመለከተ የማናፍር፤ “አይናችንን በጨው የታጠብን” ወገንተኞች ነን!

Let’s fight against #ManufacturingConsent By Oluma fb ነጻ አስተያየት


NEWSOPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ እንስሳት እየሞቱ ነው፤ ሕዝብ እየተሰደደ ነው”
የአሲይቲ ፓርክ ኃላፊዎች እስር የመንግስት ሹመኖች መጠቃቃት? “መንግስት ባስቸኳይ አጥርቶ እርምጃ ይውሰድ” – ልዩ ሪፖርት
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2