Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  “ዓለም እያዘነብን እየሳቀብን ነው አንድ እንሁን” ዘመነ፤ መከላከያ እርምጃ የወሰደባቸውን ዘረዘር
News

“ዓለም እያዘነብን እየሳቀብን ነው አንድ እንሁን” ዘመነ፤ መከላከያ እርምጃ የወሰደባቸውን ዘረዘር

Ethioreview newsEthioreview news—August 23, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

አርበኛ ዘመነ ካሴ “ዓለም እያዘነብንም እየሳቀብንም ነው” በማለት “መተው ነገሬን ከተተው” እንደሚባለው በመተው “አንድ እንሁን” የሚል ጥሪ አሰማ። ፋኖ ኢትዮጵያን ሠርቶ ምስራቅ አፍሪካን ያረጋጋል ብሏል፤ ቀደም ባሉት ጊዜያት እሱ መሪ ባለመሆኑ ስለፈርሰው ህብረት ያለው ነገር የለም። በአካባቢው መከላከያ የተጠናከረ ኦፕሬሽን እያካሄደ ነው።

አንድነት ለመፍጠር “አንድ ማንኪያ ቅንነት” ነው የሚያስፈልገው ያለው ዘመነ ይህን ያለው በጎጃም እና በደቡብ ጎንደር የተሰማራው የአገር መከላከያ ስም፣ ቦታና ኃላፊነት ጠቅሶ በፋኖ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ባስታወቀበት ዕለት ነሐሴ 16 ነው።

“የዕለቱ መልዕክት” በሚል የአማራ ፋኖ በጎጃም መሪ ዘመነ ካሴ “በቃ መተው እንልመድ” ሲል የተለያዩትን የፋኖ አመራሮችና አደረጃጀቶች ዘርዝሮ ” … አንድ መሆን አለበት” በማለት በተለይ ዛሬ ጥሪ ያቀረበበትን የተለየ ጉዳይ ባይጠቅስም “… ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪካችን የረባ ለትውልድ የሚጠቅም ፍሬ የለዉም …. የመዘላለፍና የመጠፋፋት ነው” በማለት ወቅሷል።

የአገር መከላከያ በተመሳሳይ ቀን ረፋዱ ላይ በፌስቡክ ገጹ ረፋዱ ላይ በደቡብ ጎንደርና በጎጃም ኦፕሬሽን ማካሄዱን አስታውቆ፣ “…. በዚህ ዘመቻ ከተደመሰሱት አመራሮቻቸው መሀል ረዳት ኢንስፔክተር ስሜነህ መለሰ የፋግታ ፖሊስ አባል የነበረ፣ ኢንጅነር ዋሲሁን አለነ ኤፍሬም አጥናፉ የሚባል ብርጌድ አመራር የነበረ፣  ተሻገር አደመ የዚሁ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረ፣ ምህረቱ አበበ ብርጌድ ምክትል አዛዥ፣ ግዛቸው ደሳለው ፋይናንስ ሠራተኛና የአካባቢው ፅንፈኛ መሥራች ታህሳስ 2017 ቆስሎ ያመለጠ ቀንደኛ ዘራፊ፣ ደሴ ባዜ የአባጋስ ሻለቃ አዛዥ፣ ቃኛቸው ተበጀ የሻለቃው ሎጅስቲክስ ይገኙበታል” ሲል ሰፊ ዝርዝር ያለው መረጃ አጋርቶ ነበር።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

“ይህ ትግል አንድ ይሆናል። አንድ ሆኖ አማራን ከፈጽሞ ጥፋት ይታደጋል። አንድ ሆኖ ኢትዮጵያን አንድ ያደርጋል። ኢትዮጵያን ሠርቶ ምስራቅ አፍሪካን ያረጋጋል። የሰላምና የመረጋጋት ተስፋዎች ሁሉ ከፋኖ መንደር ይቀዳሉ” ሲል ዘመነ የትግሉን ከፍታና ልቀት አስገንዝቧል።

ዘመነ “የአማራ ትግል እስክንድርን ከሀብቴ፣ ዘመነን ከደረጀ ፣ ዝናቡን ከመከታው፣ አስረስን ከፋንታሁን ሙሀባ፣ ደሳለኝን ከሄኖክ፣ ምሬን ከሳሚ፣ ጌታ አስራደን ከስሜነህ ሙላቱ … ሳይለይ ቶሎ አንድ መሆን አለበት። ትግሉ ዛሬ አንድ መሆን አለበት። የርዕዮት፣ የመስመርና የሀሳብ ልዩነቶች በዝግ ውይይት ይታረቃሉ። ይከረከማሉ” ሲል የአንድነት ጥሪ ያሰማው ከዚህ ከተጠቀሰው የአገር መከላከያ ኦፕሬሽን ጋር በተያያዘ ይሁን በሌላ የተገለጸ ነገር የለም።

“ሰርገው የገቡ እጆች በጥንቃቄና በጥበብ ይቆረጣሉ። የአንድ መከረኛ ህዝብ ልጆች ነን። ይብቃንና ማንንም ሳንጥል ማንንም ሳናንጠለጥል አንድ እንሁን። ዓለም እያዘነብንም እየሳቀብንም ነው። ድርጅታችን የአማራ ፋኖ በጎጃም ለዚህ የተቀደሰ እርምጃ እንደሁልጊዜው ሁሉ ዝግጁ ነው። በቃ መተው እንልመድ። መተው ነገሬን ከተተው ነውና ብሂሉ” ያለው ዘመነ ካሴ፣ ደጋፊዎች ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስቧል።

አክሎም “መሰዳደቡን መዘላለፉን እንተወዉ። ዘመናዊ የፓለቲካ ታሪካችን የረባ ለትውልድ የሚጠቅም ፍሬ የለዉም እንጅ የመዘላለፍና የመጠፋፋት ነው። ከተማርንበት እሱ በቂ ነው” ብሏል።

በመልዕክቱ ማጠቃለያ “አሁን ወደ ሥራ” እንግባ ያለው ዘመነ ካሴ፣ አፋብኃ በቅጡ ጤናማ ሆኖ ይሰራል። አፋህድ እና አፋብኃ አንድ ይሆናሉ።አለቀ” ሲል የጥሪውን ግብ አስቀምጧል። ይህ ይሳካ ዘንዳ የሚያስፈልገው አንድ ማንኪያ ቅንነት ብቻ እንደሆነም አመልክቷል።

የፋኖ አደረጃጀትን ወደ አንድ ኅብረት ለማምጣት በተደጋጋሚ ጥረቶች የተካሄዱ መሆናቸው ይታወሳል። በተለይ አራቱንም የፋኖ አደረጃጀቶች (እስክንድርንም ጨምሮ) ወደ አንድ ዕዝ ለማምጣት በተደረገው ስብሰባ የዘመነ ሰዎች አመራሩን ወደ ጎጃም ለመውሰድ ባደረጉት ሙከራና በጠነሰሱት ሤራ፤ ይህም ይፋ በመውጣቱ ሳይሳካ ቀርቷል።

የአሜሪካው አምባሳደር ማሲንጋ ላቀረቡት ጥሪ እስክንድር በእንግሊዝኛ ምላሽ በመስጠቱና በቀጣይም ለድርድር የተዘጋጀ የተጠናከረ ቡድን ሆኖ መውጣቱ ያሳሰበው ዘመነ የሻዕቢያ ትዕዛዝም ተጨምሮበት እነ ምሬ ወዳጆንና ሌሎች ደጋፊዎቹ ሰብስቦ ኅብረት ለመፍጠር መሞከሩ ይታወሳል። ሆኖም ዘመነ የኅብረቱ መሪ እኔ ካልሆንሁ በሚል ባስነሳው ጭቅጭቅ የታሰበው ኅብረት ከአንድ ቀን የፎቶ ሥነስርዓት ማለፍ አቅቶት ተበታትኗል።   

በርካታ የፋኖ ኅብረት አደረጃጀቶችን እኔ ካልመራሁት በሚል እብሪትና ራስ ወዳድነት አፍርሷል በማለት ዘመነን የሚከስሱ ወገኖች ያሁኑን ጥሪውን ጠላቱን ለመጉዳት ብሎ የተሻገረበትን ድልድይ እያፈረሰ እንደመጣ ግለሰብ አድርገው ይቆጥሩታል። ድልድይ አፍራሹ የጠላቱን መጎዳት ብቻ ነበር ያሰበው በኋላ ግን ራሱም መመለስ አቅቆታል፤ ዘመነም እንዲሁ ነው። ፋኖን እኔ ካልመራሁት በሚል ስሁት እሳቤ “በምድር ላይ እኔና እስክንድር ብቻ ብንሆን አንጣላም” ካለው ወዳጁ እና ከሌሎችም ተቃቅሮ አሁን የአንድነትና የኅብረት ጥያቄ ቢያቀርብ ምላሹ “ድልድዩ ፈርሷል” የሚል ይሆናል በማለት በምሬት ይናገራሉ።

መከላከያ ያስነበበው ዘገባ እንደሚከተለው ይነበባል፤

“በጎጃም እና በደቡብ ጎንደር የተሰማራው ሠራዊት 81 የጽንፈኛውን ቡድን አባላት ደመሰሰ” ሲል የአገር መከላከያ ያሰራጨው ዜና ከስር ሙሉ በሙሉ ቀርቧል። ፋኖ በየትኛውም አደረጃጀቱ ዜናውን አላስተባበለም።

ምስራቅ ዕዝ እና በስሩ ያሉት ኮሮች ባደረጉት ልዩ ስምሪት የጽንፈኛው ቡድንን አከርካሪ የሰበሩ ውጤቶች አስመዝግበዋል። ጽንፈኛው የሚዲያ ግርግር ለመፍጠር በሁሉም የጎጃም እና የደቡብ ጎንደር ዞኖች ሽብር ለመፍጠር ቢያስብም ሀሳቡ መና ቀርቶ 81 አመራሩን እና ተዋጊዎቹን አጥቷል።

ምስራቅ ዕዝ በደቡብ ጎንደር በእብናት ፣ በሊቦ ከምከም ፣ በፋርጣ፣ በእስቴ፣ በደራ ወረዳዎች ቀበሌዎች ባደረገው ስምሪት ጽንፈኛውን የገባበት ገብቶ ደምስሶታል። በሰሜን ጎጃም ባሉ ደቡብ ሜጫ፣ደቡብ አቸፈር፣ ሰሜን ሜጫ ወረዳዎች ቀበሌዎች ውስጥ ተሰግስጎ የነበረውን ዘራፊ ቡድን የማጽዳት ግዳጅ ተወጥቷል።

በአዊ ብሑረሰብ ዞን በዳንግላ፣ በፋግታ ለኮማ፣ ድማማ አንገረብ እና በሌሎች ወረዳዎች ውስጥ ባሉ ቀበሌዎች ባደረገው ዘመቻ ጽንፈኛውን የገባበት ገብቶ ነው የቀጠቀጠው። በምዕራብ ጎጃም ቋሪት፣ አበስቃን፣ ጉልሽ፣ ጎሽ ሜዳ፣ አየለች ገበያ፣ ሰከላ ወረዳ ቀበሌዎች ላይ እንዲሁም በምስራቅ ጎጃም አነደድ ወረዳ ጉዳለማ ከተማ ኮሮች ህግ የማስከበር ግዳጃቸውን በብቃት ተወጥተዋል።

በነዚህ ስኬታማ አፕሬሽኖችን ከተደመሰሱት በተጨማሪ 44 የጥፋት መልዕክተኞች ቁስለኛ ሆነዋል።  አስራ አንድ ሲማረኩ ፣ አስራ ሁለት እጃቸውን ሰጥተዋል ። ሌሎች አስራ ሁለቱ ጥቃቱን መቋቋም ተስኗቸው ሲሸሹ በአባይ ወንዝ እና በጎርፍ ተበልተው ህይወታቸው አልፏል። በውሀ ከተውሰዱት መሀል አዲሱ መንበር የኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ፅ/ቤት ሃላፊ የነበረ ፣ ጉምዜ እና በዛብህ የሚባሉ የጽንፈኛው አመራሮች ይገኙበታል።

አንድ አር ፒ ጂ/ላውንቸር ከነቅንቡላው፣ አንድ ፒ ኬ ኤም/መትረየስ፣ 85 የድሽቃ ጥይት፣ 27 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ፣ 60 የመትረየስ ጥይት፣ 103 የኤ ኬ ኤም ጥይትን ጨምሮ ሌሎች ጽንፈኛው ለጥፋት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሸከርካሪዎች እና 22 ሞተር ሳይክሎች እንዲሁም ሌሎች ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በተለይም በሠራዊታችን ቁጥጥር ስር የዋለውና የጽንፈኛው መሪ ያስመረቀው “ዘሪሁን 13 የአዲሱ ትውልድ ሮኬት ሚሳዔል” በሚል ቁርጥራጭ ብረት ቀጣጥለው የሰሩት የውሸት መሳሪያ ህዝቡን ምን ያህል እንደናቁትና በውሸት ፕሮፓጋንዳ እንደሚያታልሉት ያጋለጠ ነበር። ጽንፈኛው ዘመናዊ ሮኬት ሰርቻለሁ በሚል ከህብረተሰቡ በርካታ ገንዘብ በመዋጮ ስም ዘርፎበታል።

በዚህ ዘመቻ ከተደመሰሱት አመራሮቻቸው መሀል ረዳት ኢንስፔክተር ስሜነህ መለሰ የፋግታ ፖሊስ አባል የነበረ ፣  ኢንጅነር ዋሲሁን አለነ ኤፍሬም አጥናፉ የሚባል ብርጌድ አመራር የነበረ፣  ተሻገር አደመ የዚሁ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረ ፣ ምህረቱ አበበ ብርጌድ ምክትል አዛዥ ፣ ግዛቸው ደሳለው ፋይናንስ ሰራተኛና የአካባቢው ፅንፈኛ መስራች ታህሳስ 2017 ቆስሎ ያመለጠ ቀንደኛ ዘራፊ ፣ ደሴ ባዜ  የአባጋስ ሻለቃ አዛዥ ፣ ቃኛቸው ተበጀ የሻለቃው ሎጅስቲክስ ይገኙበታል።

በዚህ ስምሪት የተደመሰሱት የጽንፈኛው አመራሮች በቡድኑ ውስጥ ትልቅ ቦታ ነበራቸው። በተለይም ሃምሳ አለቃ ደሴ አባይነህ የዘራፊው ዋና ስምሪት ሰጪ እና ሎጀስቲክስ፣ መሪጌታ ብርሃኑ ጌታነህ  የቀጣናው አወያይ እና ፖሊቲካ አስልጣኝ ወደ መንግስት ፅንፈኛው የሰላም ጥሪ እንዳይቀበል ቃለ መህላ የሚየስገባና እየሰበከ ሲያዋጋ የነበረ፣ አንተነህ መሠረት ከዚህ በፊት መንገድ ትራንስፖርት ሙያተኛ የነበረ  ከመጀመሪያው ጀምሮ ፅንፈኛን ያደራጀ የመንግስት መሣሪያ ከሚሊሺያ ያስወረደ አሁን የሻለቃ ምክትል አዛዥ የነበረ በጀግኖቹ የኢትዮጵያ ልጆች ቀለባቸው አፈር ሆኗል።

የሠራዊታችንን ምት መቋቋም ያቃታቸው የጽንፈኛው አመራሮች በዋሉበት የማያድሩ ፣ ህይወታቸውን ለማትረፍ በየጥሻው እና ጉራንጉሩ መደበቂያ ሲፈልጉ የሚውሉ ፣ የሠራዊታችንን መምጣት ምልክት ሲያዩ በመጨነቅ ከመሞት ለመሰንበት በመደበቅ ህይወታቸውን የሚያራዝሙ ሆነዋል።

ምስራቅ ዕዝ በቅርቡ በጀመረው በዚህ አዲስ ስልት ፣ ሠራዊታችን አስቸጋሪ መልክዓ ምድሮችን በቀንም ሆነ በድቅድቅ ጨለማ በጽናት በማለፍ፤ ዝናብ፣ ጭቃ፣ የወንዝ ሙላት፣ ብርድ እና ሌሎች የተፈጥሮ መሰናክሎችን በመቋቋም ባደረጋቸው እልህ አስጨራሽ ስምሪቶች ህዝብን እፎይ ያስባሉ ውጤቶችን አስገኝቷል።

በዚህ ወር ከነሐሴ 9 ቀን ጀምሮ ባሉት ቀናቶች በተካሔደው ልዩ ኦፕሬሽን የአማራ ክልል የሰላም እና ፀጥታ ሀይሎች፣ የመስተዳድር አካላት እና ኅብረተሰቡ መረጃ እና ሌሎች ድጋፍ በመስጠት ለሰላማቸው እንዲጸና ያላቸውን አጋርነት በተግባር አሳይተዋል።

ሠራዊታችን እነዚህን የህዝብ ሰላም አደፍራሾች በጸረ-ሽምቅ ከያሉበት እያሰሰ ፣ እየከበበ እና እየመነጠረ አጽድቶ ህግ ያስከብራል። ዘመቻው ሰላም አደፍራሾች እስኪጠፉ የሚቀጥል ሲሆን ሰራዊታችን ክልሉን ከጽንፈኞች የማጽዳት ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ


NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
አረምና መልከ ብዙ ዝርፊያ በኢትዮጵያ
አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2