Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News2  የደቡብ ሱዳን ወደ ቀውስ ማምራትና የተመድ ማስጠንቀቂያ
News2POLITICS

የደቡብ ሱዳን ወደ ቀውስ ማምራትና የተመድ ማስጠንቀቂያ

Ethioreview newsEthioreview news—August 24, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት በአምስት ዓመታት ውስጥ ሰባተኛ የፋይናንስ ሚኒስትር ሾመዋል። ልጃቸው አዱት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት ፕሬዝዳንታዊ አማካሪ ሆናለች። ኪር ተቀናቃኛቸው ሪየክ ማቻርን አስረው ሹም ሹር ሲያካሒዱ በግጭት እና ፖለቲካዊ ቀውስ የሀገሪቱ ሰላም እየተሸረሸረ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት አስጠንቅቋል።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት በዚህ ሣምንት የፋይናንስ ሚኒስትራቸውን አባረው በአምስት ዓመታት ውስጥ ሰባተኛ ባለሥልጣን ሾመዋል። ባለፈው አንድ ዓመት የደቡብ ሱዳን የፋይናንስ ሚኒስትር የነበሩት ማሪያል ዶንግሪን አተር ከሥልጣናቸው ለምን እንደተባረሩ ኪር ያሉት ነገር የለም። ይሁንና መንግሥት በሚቆጣጠረው ብሔራዊ ራዲዮ ይፋ በተደረገ ውሳኔያቸው ባለፈው ሐሙስ አቲያን ዲንግ አቲያን አዲሱ የደቡብ ሱዳን የፋይናንስ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውን አሳውቀዋል።

ከፋይናንስ ሚኒስትሩ በተጨማሪ የደቡብ ሱዳን የኢንቨስትመንት ሚኒስትር የነበሩት ዲሖ ማቶክ ተሽረው ጆሴፍ ማጃክ ተሾመዋል። ሳልቫ ኪር የመጀመሪያ ሴት ልጃቸው አዱት ሳልቫ ኪር የልዩ ፕሮግራሞች የፕሬዝደንቱ ልዩ ልዑክ አድርገው ሾመዋል። የቀድሞው ልዩ ልዑክ ቤንጃሚን ቦል ሜል በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የኢኮኖሚ ጉዳዮችን እንዲመሩ ተሾመዋል።

አዱት የአባታቸው ሳልቫ ኪር የቅርብ አማካሪ ሆነው ከመሾማቸው በፊት በደቡብ ሱዳን መንግሥት ውስጥ ሠርተው አያውቁም። የግብረ-ሰናይ እና የሰብአዊ ርዳታ ሥራዎችን የሚያስተባብር በሥማቸው የተሰየመ ድርጅት ሲመሩ ቆይተዋል። ሳልቫ ኪር ለቤተሰቦቻቸው ሥልጣን ሲሰጡ አዱት የመጀመሪያዋ አይደሉም። ወንድ ልጃቸው ቲክ ሳልቫ ኪር ሚያርዲት የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንታዊ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ፤ የባለቤታቸው ወንድም ሜጀር ጄኔራል ግሪጎሪ ዴንግ ቀደም ሲል የአፐር ናይል አገረ ገዥ ኋላ ደግሞ የስለላ መሥሪያ ቤቱ ምክትል ኃላፊ አድርገው ሾመው ያውቃሉ።

More stories

የደቡብ ሱዳን ወደ ቀውስ ማምራትና የተመድ ማስጠንቀቂያ

August 24, 2025

የኦሮሞ ዞን ምክር ቤት ጥብቅ ገደብ ጣለ

May 17, 2022

ኢትዮጵያ ላይ በማንኛውም መልኩ የሚቃጡ ትንኮሳዎችን የሚመክት ሠራዊት ተገንብቷል- ፊ.ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

June 12, 2025

ከ40 ቀናት ክትትል በሁዋላ 27.75 ኪሎ ግራም ወርቅ በቁጥጥር ስር ዋላ፤ የውጭ አገር ዜጎች አሉበት

August 2, 2025

ደቡብ ሱዳን ነጻ ከወጣችበት ከጎርጎሮሳዊው 2011 ጀምሮ ፕሬዝዳንትነቱን የተቆናጠጡት ሳልቫ ኪር ለልጃቸው የሰጡት ሥልጣን እና ያካሔዱት ሹም ሽር በሀገሪቱ ፖለቲካዊ ሥርወ-መንግሥት ወይም የውርስ አመራር የመፍጠር አካሔድ እንደሆነ ተቺዎቻቸው ይነቅፋሉ።

ሥጋት የፈጠረው ግን ኪር ሹም ሽር የሚያደርጉት የደቡብ ሱዳን ኢኮኖሚ ብርቱ ቀውስ ውስጥ በወደቀበት እና ዳግም የርስ በርስ ጦርነት እንዳያገረሽ ባስፈራበት ወቅት መሆኑ ነው። በጎርጎሮሳዊው ከ2013 እስከ 2018 በተካሔደው የርስ በርስ ጦርነት አሽቆልቁሎ የነበረው ደቡብ ሱዳን በዓለም ገበያ የምትሸጠው ነዳጅ ዘይት አሁን ደግሞ በሱዳን ቀውስ ምክንያት ዳግም ተስተጓጉሏል።

በጎርጎሮሳዊው 2025 የደቡብ ሱዳን ኢኮኖሚ በ4.3% እንደሚኮማተር የተነበየው ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) የዋጋ ግሽበት በተመሣሣይ ዓመት 65.7% ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቋል። የደቡብ ሱዳን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ለገባበት ቅርቃር መፍትሔ አልሆነም።

የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት በዚህ ሣምንት በደቡብ ሱዳን ተደራራቢ ቀውሶች እና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ላይ ሲወያይ ማብራሪያ የሰጡት በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ክፍል የፖለቲካ እና የሰላም ግንባታ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሀፊ ማርታ አማ አክያ ፖቤ “የሰላም ሥምምነት በተፈራረሙት ኃይሎች መካከል የነበረው መተማመን” እና “በሰላም ሒደቱ የተገኙ ውጤቶች መሸርሸራቸውን ቀጥለዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

የደቡብ ሱዳን “የፖለቲካ ቀውስ እና በግዛቶቿ የተቀሰቀሱ ግጭቶች እየተባባሱ” መሔዳቸውን የሰላም ሥምምነቱ አፈጻጸም በአንጻሩ መቀዛቀዙን የጠቀሱት ጋናዊቷ ዲፕሎማት የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ኅብረት፣ የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ “ግጭት እንዲቆም፣ ውጥረቱ እንዲረግብ እና ሁሉም ኃይሎች ወደ ውይይት እንዲመለሱ ጥሪ” ቢያቀርቡም ተጨባጭ መልስ እንዳልተገኘ ገልጸዋል።

ማርታ አማ አክያ ፖቤ “እንዲያውም የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች፣ የተናጠል እርምጃዎች አሁንም በመቀጠላቸው የብሔራዊ አንድነት መንግሥቱ ሥምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ያለው አቅም መዳከሙን ቀጥሏል” ሲሉ ተደምጠዋል።

ተቀናቃኞቹ ሳልቫ ኪር ሚያርዲት እና ሪየክ ማቻር የተፈራረሙት የሰላም ሥምምነት ቅርቃር ውስጥ የገባው ባለፈው መጋቢት የደቡብ ሱዳን መንግሥት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱን በቁጥጥር ሥር ካዋለ በኋላ ነበር። ማቻር ሲታሰሩ ፓርቲያቸው የደቡብ ሱዳን ነጻ አውጪ ንቅናቄ -በተቃውሞ (SPLM-IO) የርስ በርስ ጦርነት ያቆመው እና ተፋላሚዎቹ ሥልጣን የተካፈሉበት ሥምምነት መፍረሱን አውጇል።

በተባበሩት መንግሥታት መረጃ መሠረት ወደ 400,000 ገደማ ሰዎች የተገደሉበትን የርስ በርስ ጦርነት በሁለት ጎራ በፊት አውራሪነት የመሩት ኪር እና ማቻር ዳግም የገቡበት ፍጥጫ የጎሳ ግጭት በተለይ በዲንቃ እና በኑዌር ጎሳዎች መካከል ሊቀሰቅስ እንደሚችል ሥጋት ፈጥሯል።

የጦር መሣሪያ በትከሻው የተሸከመ የደቡብ ሱዳን ወታደር የጦር መሣሪያ በትከሻው የተሸከመ የደቡብ ሱዳን ወታደር
ተቀናቃኞቹ ሳልቫ ኪር ሚያርዲት እና ሪየክ ማቻር የገቡበት ፍጥጫ ደቡብ ሱዳንንን በመቶ ሺሕዎች ወደተገደሉበት የርስ በርስ የጦርነት አዘቅት መልሶ እንዳይከታት ሥጋት አይሏል።ምስል፦ picture-alliance/AP Photo/J. Lynch
የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ቀውስ ከቀጠለ በሀገሪቱ የተለያዩ ግዛቶች “የተወሰነው ማኅበረሰባዊ ግጭት የሥምምነቱን ፈራሚዎች እና ሌሎች ጎረቤት ሀገራት ወደሚያሳትፍ በጎሳ ክፍፍል ላይ ወደ ተመሠረተ ጦርነት ሊሸጋገር” እንደሚችል ማርታ አማ አክያ ፖቤ አስጠንቅቀዋል። የደቡብ ሱዳን የሰላም ሥምምነት የክትትል እና ግምገማ የጋራ ኮሚሽን ጊዜያዊ ሊቀ-መንበር ጆርጅ አግሬይ ኦዊኖው ተመሣሣይ ሥጋት አላቸው።

“አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ እና የሀገሪቱ አካሔድ በአፋጣኝ መፍትሔ ካልተበጀለት ባለፉት ዓመታት የታዩ መሻሻሎችን የሚቀለብስ እና የሰላም ሥምምነቱን በማክሸፍ ደቡብ ሱዳንን ወደ ጦርነት የሚመልስ ነው” ሲሉ ያስጠነቀቁት ጆርጅ አግሬይ ኦዊኖ የሚመሩት ኮሚሽን ከአፍሪካ ኅብረት እና ከተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ልዑክ ጋር በመሆን “ገንቢ ውይይት እንዲደረግ፣ ውጥረት እንዲረግብ የእስረኞች ጉዳይ መፍትሔ እንዲበጅለት እና የሰላም ሥምምነቱ ተግባራዊ እንዲሆን በተደጋጋሚ ጥሪ አቅርበዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

የክትትል እና ግምገማ የጋራ ኮሚሽኑ ከመጋቢት ወዲህ የሰላም ሥምምነቱ አተገባበር ቆሟል የሚል እምነት አለው። በሀገሪቱ መንግሥት እና ጦር ውስጥ የነበሩ የደቡብ ሱዳን ነጻ አውጪ ንቅናቄ -በተቃውሞ (SPLM-IO) ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አመራሮች መታሰር፣ መባረር እና መሸሽ ሥምምነቱን እንደሚጥስ የክትትል እና ግምገማ የጋራ ኮሚሽኑ የጽህፈት ቤት ኃላፊ አምባሳደር ብርሀኑ ከበደ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለሚተዳደረው ራዲዮ ሚራያ ተናግረዋል።

“ወደ ደቡብ ሱዳን የሚመጣ እያንዳንዱ ተልዕኮ፣ እያንዳንዱ ዓለም አቀፍ እና ቀጠናዊ ስብሰባ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንቱ ያለ አንዳች ቅድመ-ሁኔታ ከእስር እንዲፈቱ በሙሉ ድምጽ ጥሪ ሲያቀርብ ቆይቷል” ያሉት አምባሳደር ብርሀኑ “የዚህ አገር አመራር ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱን ለመፍታት እና የሰላም ሥምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ይስማማል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል።

“ሥምምነቱ የፓርቲዎቹ ነው” ያሉት ዲፕሎማቱ “ሀገሪቱ በሰላም ወደተመረጠ መንግሥት እንድትሸጋገር የሥምምነቱን ድንጋጌዎች፤ የሥምምነቱን ቃል እና መንፈስ ማክበር ይሻላል” ሲሉ መክረዋል።

በጎርጎሮሳዊው መስከረም 2018 የተፈረመው የሰላም ሥምምነት በ44 ወራት ውስጥ ተግባራዊ ሆኖ ሲጠናቀቅ ደቡብ ሱዳን የተመረጠ መንግሥት ይኖራታል ተብሎ ዕቅድ ነበር። ዕድሜያቸው 70ዎቹን የተሻገረው ኪር እና ማቻር ግን ሥምምነታቸውን ባለማክበራቸው የታቀደው አልተሳካም።

በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ክፍል የፖለቲካ እና የሰላም ግንባታ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሀፊ “ሁሉም ወገኖች ለግጭት ማቆም ሥምምነቱ ሙሉ ቁርጠኛ ሆነው የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታት፣ በከፍተኛ አመራሮቻቸው መካከል ቀጥተኛ ውይይት በማድረግ አካታች የሰላም ተግባራዊ በማድረግ ለተፈጠረው ፖለቲካዊ ልዩነት መፍትሔ እንዲያበጁ” ጥሪ አቅርበዋል።

ማርታ አማ አክያ ፖቤ እንዳሉት“በተለይም ለሽግግር የጸጥታ ጉዳዮች መፍትሔ ለማበጀት፣ ለሽግግር ፍትህ፣ ለሕገ-መንግሥት ዝግጅት እና ለምርጫ ቁርጠኛ መሆን አለባቸው።”

Via – DW amharic


homePOLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት
ደበበ እሸቱ (1934-2017 ዓ.ም)
Related posts
  • Related posts
  • More from author
POLITICS

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

March 28, 2026
News2

ብሔራዊ ጥቅምን አሳልፎ ለመስጠት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ባለድርሻ ሊሆኑ አይገባም – በለጠ ሞላ

March 8, 2026
News2

ለክቡር የኢፌዴሪ ማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝና ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው የቀረበ ጥሪ

March 8, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2