በኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው አዲስ ረቂቅ መመሪያ መሰረት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች የስራ እድል የሚያመቻች ማዕከል እንዲያቋቁሙ መመሪያ ሊወጣ መሆኑ ተሰምቷል።
ይህ “የስራ ቅጥርና ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ማዕከል” ተማሪዎችን፣ ሰራተኞችን እና ምሩቃንን ለማሰልጠን፣ ለፈጠራ እና ለቢዝነስ ኢንኩቤሽን ድጋፍ ለመስጠት ያለመ ነው።
ሁሉም የመንግስት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች መመሪያው ከፀደቀ በስድስት ወራት ውስጥ ማዕከሉን የማቋቋም ግዴታ አለባቸው።
አዲሱ መመሪያ ተማሪዎች በየዓመቱ ቢያንስ አንድ ጊዜ የማዕከሉን አገልግሎት እንዲጠቀሙ የሚጠይቅ ሲሆን፣ ይህን አገልግሎት መጠቀም ለምረቃ ቅድመ ሁኔታ እንደሚሆን ተገልጿል።
ማዕከሉ አገልግሎቱን ከሶስት ዓመት በፊት ለተመረቁ የቅርብ ጊዜ ምሩቃንም ይሰጣል። መመሪያው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ለመመዘን እንደ አንድ መለኪያም ያገለግላል ተብሎ ይጠበቃል።


