በዛሬው ዕለት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን የውይይት ኮሚሽን አባላትን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። አባላቱ ከመስከረም 13 እስከ 15 ዝግጅት እንዳላቸው ተገልጿል።
ሁለቱም ወገኖች የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ክርስቲያናዊ የሞራል እሴቶችን ለመጠበቅ ያላቸው የጋራ ቁርጠኝነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ክርስቲያኖች ስደት በሚደርስባቸው ክልሎች ላይ የጋራ ድጋፍ የማድረግን አስፈላጊነትም አረጋግጠዋል ሲል በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ አሳውቋል።
ስፑንቲክ

