የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ” የህዳሴ ግድብ ” በሚይዘው የውሃ መጠን ፣በፋይናንስ ምንጭ፣ በማመንጨት አቅሙ፣ በሚሰጠው ትርጉም እንዲሁም በሌሎች በርካታ ምክንያቶች ከሌሎች ፕሮጀክቶች ለየት ያደርገዋል ” ብለዋል። ኃላፊው ይህንን ያሉት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የአባይ ግድብ ምርቃትን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።
ህዳሴ ግድብ ከተጀመረ አንስቶ እስካሁን 233 ቢሊየን ብር ገንዘብ ለግንባታ ወጥቶበታል ያሉት አቶ ሞገስ ከአጠቃላይ ወጪው ውስጥ 223 ቢሊየን ብር ወይም 91 በመቶ ገንዘብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘ ነው ብለዋል።
ቀሪው 9 በመቶ የሚሆነው ከህዝብ ተሳትፎ የተገኘ ገንዘብ :-
➡️ 18.9 ቢሊየን ብር በኢትዮጵያውያን እና በትውልደ ኢትዮጵያዊን የቦንድ ሽያጭ።
➡️ 1.6 ቢሊየን ብር በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያን የቦንድ ሽያጭ እና ስጦታ ።
➡️ 3.2 ቢሊየን ብር ከስጦታ ተሰብስቧል ብለዋል።
ከደኅንነት አንጻር ሁለት አይነት ሀሳቦች እንደሚነሱ ያነሱት አቶ ሞገስ የመጀመሪያው ከግድብ ደኅንነት አንጻር ተያይዞ በሚነሳው ሃሳብ ላይ ግድቡ ምንም አይነት የጥራት ጉድለት እንደሌለው በባለሞያዎች ጭምር የተረጋገጠ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ሁለተኛውና በተለይም በግብፅ በኩል ይነሳል ያሉት የውኃ ደኅንነት ጉዳይ በተመለከተ ኃላፊው ይህ የቀኝ ግዛት ውሎችን መሰረት ተደርጎ የሚነሱ ኃሳቦች ናቸው ሲሉ የጋራ ተጠቃሚነትን ባከበረ መልኩ ግድቡ መጠናቀቁን በማንሳት የውኃ ፍሰቱ የሚገደብ እንዳልሆነ ነው ያነሱት።
” በ2017 ዓም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል 29.5 ጊጋ ዋት ሰአት ሃይል ማመንጨት ችሏል 33 በመቶ የሚሆነው ከታላቁ የህዳሴ ግድብ የተገኘ ነው።
7 በመቶ የሚሆነው ከህዳሴ ግድብ የተገኘ ሃይል ወደ ውጪ ኤክስፖርት የተደረገ ነው አጠቃላይ የኤክስፖርት አቅሙ በእዚህ ልክ የሚገለጽ ነው ያሉ ሲሆን ሃይል ኤክስፖርት የሚደረገውም ማዕከላዊ የሃይል ቋት ከገባ በኋላ ነው።
በአሁኑ ሰአት ሁሉም የግንባታ እና የፍተሻ ስራዎች ተጠናቀው የምረቃ ዋዜማ ላይ እንገኛለን ከሁለት ሦስት ቀናት በኋላ የምረቃ መርሃ ግብሩ ይከናወናል።
በህዳሴ ግድብ የሚመነጨውን ሃይል በሁለት መስመሮች በደዴሳ ሆለታ አዲስ አበባ እና በበለስ የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በኩል በተገነቡ መስመሮች ወደ ግሪድ እየገባ ነው። ” ብለዋል።
የህዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ የሃይል ሽፋንን በምን ያህል መጠን ይጨምራል ?
” የህዳሴ ግድብ የኢነርጂ ተደራሽነታችንን ከስድስት አመት በፊት የነበረበትን 44 በመቶ ሽፋን ወደ 54 በመቶ አድርሶታል በሙሉ አቅሙ ሃይል ማመንጨት ሲጀምርም ተደራሽነታችንን እያሰፋው ይሄዳል።
ህዳሴ ኤሌክትሪክ ላልደረሰባቸው አካባቢዎች ብርሃን ለደረሰባቸው አካባቢዎች ደግሞ አስተማማኝ የሃይል ምንጭ መሆን ችሏል።
ህዳሴ ሲመረቅ አሌክትሪክ ያልተዳረሰባቸው አካባቢዎች ወዲያው ሃይል ይዳረሳል እንዲሁም ኤሌክትሪክ በነጻ ይሆናል የሚለው የተሳሳተ አመለካከት መታረም አለበት ኤሌክትሪክ መቼም በነጻ አይሆንም ይህ ሃሳብ መታረም አለበት።
ምርቃት መርሃ ግብሩ እንደ ሃገር የተዘጋጀ ነው በሃገር ደረጃ የምርቃት መርሃ ግብሩን የሚከታተል አብይ ኮሚቴ ተቋቁሙ ሲሰራ ቆይቷል ለተለያዩ የሃገር ውስጥ እና የውጭ እንግዶች ጥሪ ተደርጓል። ” ብለዋል።
ህዳሴ ግድብ በግንባታ ላይ በነበረበት ወቅት ከግንባታ ጋር ተያይዞ በአጋጣሙ ክስተቶች በሰራተኞች ላይ ያጋጠመ የህይወት ህልፈት እና ተያይዞ ስለሚነሱ ቁጥሮች ጥያቄ የቀረብንላቸው አቶ ሞገስ ምላሽ ሰጥተዋል።
” በርካታ ኢትዮጵያውያን የደም እና የላብ መስዋእትነት ከፍለዋል ህይወታቸው ያለፉ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በሚመለከት ግን ትክክለኛው ቁጥር በሚመለከታቸው አካላት ቢገለጽ የተሻለ ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።
ሪፖርቱ የቲክቫህ ነው

