Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  የአብይ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት “የኢትዮጵያ ታሪክ የሚቀየረው በስራ ነው”
News

የአብይ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት “የኢትዮጵያ ታሪክ የሚቀየረው በስራ ነው”

Ethioreview newsEthioreview news—September 10, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ “ዕድገትና ብልጽግና የቅብብሎሽ ውጤት ነው” በማለት በህዳሴው ግድብ አሻራቸው ለታተመ ሁሉ ምስጋና አቀረቡ። “የጀመራችሁ፣ ያስቀጠላችሁ፣ ለፍጻሜ የታገላችሁ ስማችሁን በሕዳሴ ግድቡ ላይ ጽፋችኋል፡፡ በገንዘብ፣ በዕውቀት፣ በጉልበት፣ በሚዲያ፣ በዲፕሎማሲ፣ በሞያ፣ ወዘተ. የምትችሉትን ያበረከታችሁ ሁሉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ሆናችሁ በታሪክ ሠፍራችኋል።” ሲሉም አክለው ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአዲሱ የ1918 ዓ.ም “እንኳን አደረሳቹህ” መልዕክት ሲያስተላለፉ ” ኢትዮጵያ ማንሠራራት በጀመረችበት እና ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በተመረቀበት ጊዜ ለሚከበረው አዲስ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ” ብለዋል። ሙሉ መልዕክታቸውን ከስር ያንብቡ

ያለፈው ዓመት ፈጣሪ ከጎናችን፣ ስኬት በደጃችን መሆኑን ያየንበት ዓመት ነበር፡፡ በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በማዕድን፣ በአምራችነት እና በአይሲቲ ዘርፎች ያስመዘገብናቸው ውጤቶች ይሄንን ይመሰክራሉ፡፡ ኢትዮጵያን ያህል ሀገር፣ ኢትዮጵያውያንን ያህል ሕዝብ ይዘን በትጋት ከሠራን፣ ከዚህ በላይ ድል ልናሳካ እንደምንችል ምስክራችን የሕዳሴ ግድብ ነው፡፡

ከእርግዝና ወራት ሁሉ እጅግ አስቸጋሪዎቹ፣ እጅግ አስፈሪዎቹ እና እጅግ ፈታኞቹ የመጨረሻዎቹ ሰዓታት ናቸው ይባላል፡፡ በሕዝብ ልብ ውስጥ ለዘመናት የተጸነሰውን የሕዳሴውን ግድብ ኢትዮጵያ እንድትወልደው ብዙ ፈተናዎችን መሻገር ግድ ነበር፡፡ ብዙ አስቸጋሪ ጊዜያትን ማለፍ ይገባ ነበር፡፡ አያሌ አስፈሪ ተግዳሮቶችን መቋቋም ወሳኝ ነበር፡፡ በተለይም የመጨረሻዎቹ ጊዜያት ወገብን አሥሮ፣ ሐሞትን አምርሮ፣ ወኔን ቋጥሮ፣ ወጥመድን ሰብሮ፣ ሞትን ተሻግሮ መሄድ የሚያስፈልግባቸው ጊዜያት ነበሩ፡፡ ከፈጣሪ ጋር፣ በሕዝባችን ጽናት፣ በፕሮጀክት ሠራተኞቻችን ብርታት፣ በጸጥታ አባሎቻችን መሥዋዕትነት ያን ሁሉ አልፈን ለምርቃቱ በቅተናል፡፡

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

……. ንሥር ከምድር ሲነሣ ብዙ ወፎች እና ነፍሳት አብረውት ሊነሡ ይችላሉ፡፡ ለተወሰነ ጊዜም አብረውት ይበራሉ፡፡ የተወሰነ ሰዓትም ሊሸፍኑት ይደርሳሉ፡፡ የበለጠ ወደ ላይ በመጠቀ ቁጥር ግን ብዙዎቹ ወደታች ይቀራሉ፡፡ በመጨረሻም በሕዋው ላይ የሁሉንም ታሪክ እየተመለከተ ንሥር በድል መጓዙን ይቀጥላል፡፡

የምናከብረው የዓመትን መለወጥ ብቻ አይደለም፡፡ የታሪክን መለወጥ ጭምር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ገጽታ፣ የኢትዮጵያ ትርክት፣ የኢትዮጵያ ጂኦ ፖለቲካዊ ቁመና ተቀይሯል፡፡ ቀደምቶቻችን ሲመኙት፣ አያቶቻችን ሲያስሱት፣ አባቶቻችን ሲጠብቁት፣ እኛ ስንታገልለት የነበረው የኢትዮጵያ ማንሠራራት እውን ሆኗል፡፡ ይሄ ለሺ ዘመን የከፍታ ጉዟችን መነሻ እንጂ መዳረሻ አይደለም፡፡ ጅማሬ እንጂ ፍጻሜ አይደለም፡፡ እኛ በዐቅምና በአቋም ከተደመርን፣ ሀገራችን ባለ ብዙ ጸጋ ናት፡፡ ለአፍሪካ እና ለዓለም የሚተርፍ ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ እና ተፈጥሯዊ ሀብት ሞልቷታል፡፡

2018 የኢትዮጵያን ማንሠራራት የበለጠ ሥር እና መሠረት የምናስይዝበት ዓመት ነው፡፡ በአንድ እጃችን ፈተናዎቻችንን እየተቋቋምን፣ በሌላው እጃችን ታሪካችንን እየቀየርን እንጓዛለን፡፡ ንሥር ከምድር ሲነሣ ብዙ ወፎች እና ነፍሳት አብረውት ሊነሡ ይችላሉ፡፡ ለተወሰነ ጊዜም አብረውት ይበራሉ፡፡ የተወሰነ ሰዓትም ሊሸፍኑት ይደርሳሉ፡፡ የበለጠ ወደ ላይ በመጠቀ ቁጥር ግን ብዙዎቹ ወደታች ይቀራሉ፡፡ በመጨረሻም በሕዋው ላይ የሁሉንም ታሪክ እየተመለከተ ንሥር በድል መጓዙን ይቀጥላል፡፡

እኛም ለኢትዮጵያ ንጋት እና ምጥቀት ያስፈልገናል፡፡ 2018 የኢትዮጵያ ታላቅነት የበለጠ እየነጋ፣ የበለጠ እየበራ፣ የበለጠ እየፈካ የሚሄድበት ነው፡፡ የሕዳሴ ግድብን ባየን ቁጥር የኢትዮጵያን አይበገሬነትና ቻይነት እናስታውሳለን፡፡ ሐይቁን ባየን ጊዜ ደግሞ የኢትዮጵያን ንጋት እናስባለን፡፡ “ንጋት ሐይቅ” የተባለውም ለዚህ ነው፡፡ ግድቡ እስካሁን የነበረውን ይናገራል፡፡ ሐይቁ ከዚህ በኋላ የሚመጣውን ያበሥራል፡፡

ንሥር ከትንሽ ከትልቁ ጋር በሆነ ባልሆነው አይከራከርምም፤ አይነጋገርም፡፡ ወደላይ በመጠቀ ቁጥር ፈተናው እየቀነሰ፣ ዐቅሙ እየጨመረ፣ ታሪኩ እየተቀየረ እንደሚሄድ ያውቀዋል፡፡ ስለዚህም ከግራ ከቀኝ የሚወረወረው እየቻለ ወደ ላይ ይመጥቃል፡፡ እኛም ወደ ላይ ከፍ ባልን ቁጥር ፈተናችን እየቀረ፣ ድላችን እየተጨመረ እንደሚሄድ ዐውቀን፣ አእምሯችንን እና እጆቻችንን ለሥራ ማሰለፍ አለብን፡፡ ኢትዮጵያን የሚቀይራት የልጆቿ ፍጥነትና ፈጠራ ነው፡፡

የዓባይን ታሪክ የቀየረው ሥራ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክ የሚቀይረውም ሥራ ነው፡፡

በየቢሮው፣ በየእርሻው፣ በየግንባሩ፣ በየድርጅቱ፣ በየትምህርት ቤቱ፣ በየተቋማቱ ያለን ኢትዮጵያውያን ሁሉ ልባችንን፣ ሐሳባችንን፣ ዕውቀታችንን እና ጉልበታችንን ለኢትዮጵያ ብልጽግና እናውለው፡፡ ስንሠራ ምን እንደምንቀይር ከሕዳሴው ግድብ አይተናል፡፡ እኛ ለስኬት ስንረባረብ ፈጣሪ ምን ያህል እንደሚረዳን እኛው ምስክር ነን፡፡ የሺ ዘመናትን ጥያቄ እንድንመልስ ኃይል የሰጠ ፈጣሪ፣ የዓመታትንና የወራትን ጥያቄ ለመመለስ አይሳነውም፡፡ 2018 ዓመት ይሄንን ይበልጥ የምናረጋግጥበት እንደሚሆን አምናለሁ፡፡

ዛሬ ዓይኞቻችን ያዩትን ለማየት፣ ጆሮዎቻችንም የሰሙትን ለመስማት እንዲችሉ መሥዋዕትነት ለከፈላችሁት ሁሉ እጅ እንነሳለን፡፡ በሁሉም መስክ የተሳተፋችሁትን ሁሉ ኢትዮጵያ ታከብራችኋለች፡፡ ከጎናችን የነበራችሁትን ወዳጅ ሀገሮች እና ሕዝቦች ሁሉ በኢትዮጵያ ስም እናመሰግናችኋለን፡፡ ዕድገትና ብልጽግና የቅብብሎሽ ውጤት ነው፡፡ የጀመራችሁ፣ ያስቀጠላችሁ፣ ለፍጻሜ የታገላችሁ ስማችሁን በሕዳሴ ግድቡ ላይ ጽፋችኋል፡፡ በገንዘብ፣ በዕውቀት፣ በጉልበት፣ በሚዲያ፣ በዲፕሎማሲ፣ በሞያ፣ ወዘተ. የምትችሉትን ያበረከታችሁ ሁሉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ሆናችሁ በታሪክ ሠፍራችኋል፡፡

ይህ ተጋድሏችን፤ ይህ ትብብራችን፤ ይህ ለብሔራዊ ጥቅም በአንድነት መቆማችን፤ ይህ ለራሳችን፣ በራሳችን፣ ከራሳችን መሥራታችን ነገም መቀጠል አለበት፡፡ ኢትዮጵያ ከዚህ በላይ ይገባታል፡፡ ኢትዮጵያ ከዚህም በላይ ታላላቅ ሥራዎች ይጠብቋታል፡፡ ይሄንንም አብረንና ተባብረን ልናሳካላት ይገባል፡፡

አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያ ማንሠራራት የበለጠ መሠረት የሚይዝበት እንደሚሆን አምናለሁ።

በድጋሚ መልካም አዲስ ዓመት ይሁን

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ! ጳጉሜን 5 ቀን 2017 ዓ.ም


NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ኢትዮጵያዊያን በህዳሴ ግድብ ታሪክ ሰርተን ታሪክ ላይ ቆመን ለማውራት በቅተናል” አብይ አሕመድ
ፔይትሮ ሳሊኒ የሕዳሴውን ግድብ የዕንባ ሚስጢር ገለጡ፤ “ኃይል የነገ መሰረት ነው”
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2