Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ፔይትሮ ሳሊኒ የሕዳሴውን ግድብ የዕንባ ሚስጢር ገለጡ፤ “ኃይል የነገ መሰረት ነው”
News

ፔይትሮ ሳሊኒ የሕዳሴውን ግድብ የዕንባ ሚስጢር ገለጡ፤ “ኃይል የነገ መሰረት ነው”

Ethioreview newsEthioreview news—September 10, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

“ዛሬ ግድቡ ሞልቷል። በሙሉ አቅሙ ኃይል እያመረተ ነው። ህልማችን ዕውን ሆኗል። ማንም ሊደግፉት አልፈለጉም። በፖለቲክና በርካታ ጉዳዮች ተተብትቦ ነበር። ነገር ግን ኢትዮጵያዊያን አደረጉት” ይህ እንባን የሚያዋልድ፣ ቁጭትን የሚንድ ንግግር ነው።

“ዛሬ እዚህ ሆነን የምናየው እውነት ከዚህ በፊት የሚሆን አይመስልም ነበር” የሚለው የፔትሮ ሳሊኒ ንግግርና የህዳሴው ግድብ እንዴት ዕውን ሊሆን እንደቻለ ለሚያውቁና ለሚረዱ እጅግ ትርጉም ያለው እንደነበር ስለ ፕሮጀክቱ መረጃ ያላቸው ይናገራሉ።

በ1960ዎቹ ኢትዮጵያ ሲመጡ ጨለማ እንደነበር ያወሱት ሳሊኒ፣ ዛሬ እውን የሆነው የአባይ ግድብ ተሳክቶ ሊታይ የሚችል እንደማይመስል ያስረዱት በብዙ ማብራሪያዎች ላይ ነው።

የጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ፔትሮ ሳሊኒ በየታላቁ ሕዳሴ ግድብ ምርቃት ሥነ ስርአት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት “ዛሬ እዚህ ሆነን የምናየው እውነት ከዚህ በፊት የሚሆን አይመስለንም ነበር፤ ይኸው ከ14 ዓመታት በኋላ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እውን ሆኗል” ብለዋል። በፍጹም ኢትዮጵያዊ ስሜት ስኬቱን ሲያጎሉ የነበሩት ሳሊኒ ግድቡን ሲያንቋሽሹና ተልዕኮ ወስደው ሲያሰናክሉ ከነበሩ “ኢትዮጵያዊያን” ከሚባሉት ጋር ሲመዘኑ ምላሹ “ታሪክና ትውልድ ይፍረድ” ከማለት ውጭ ምንም ማለት እንደማይቻል በበዓሉ ላይ የተገኙ ነግረዋናል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ብቻ ሳይሆኑ በርካቶች ማንባታቸውን ያወሱት እነዚህ ወገኖች የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያኪጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ እንዳሉት ተልዕኮ የወሰዱ እስከ 200 ኪሎሜትር ዘልቀው በመግባት ቦንብ ቀብረዋል። የኢትዮጵያ ምርጥ ልጆች በቦንብ ላይ ተረማምደው አምክነዋል። ለኝባታው ምርት የሚመረቱባቸውን ፋብሪካዎች ለማፈንዳት በዙ ተሚክሯል። የግብአት ውጤቶች ወደ ፕሮጀክት እንዳይደርሱ ሲደረግ መስዋዕት ተከፍሏል። ይህ የሆነው በባዕድ ሳይሆን በ”ተገዙ ወገኖቻችን” ነው።

“ግድቡ ዛሬ ላይ በሚፈለገው የውኃ መጠን ሞልቶ፣ ተርባይኖቹም የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀምረዋል” ያሉት ፔትሮ፣ “ሁሉም ነገር በትክክል እየሠራ ነው፤ ይህ እጅግ አስደናቂ ነው፤ እጅግ ደስ የሚል ነገር ነው” ማለታቸው ትርጉም የሚሰጠው ግድቡ በላብ፣ በደም፣ በሕይወት፣ በአገር ሐብትና የህዝብ ገንዘብ መገንባቱንና በኝባታው ሂደት የታለፈበትን አስቸጋሪ ጎዳና በወጉ መረዳት ሲቻል ብቻ ነው።

“ይህ ለእኔ እና ለኢትዮጵያ እውን የሆነ ሕልም ነው፤ ዛሬ ምን ያህል እንደኮራሁ ልነግራችሁ እወዳለሁ፤ ልቤ የኢትዮጵያውንን አንድነት እየዘመረች ነው” ሲሉም ሳሊኒ የተሰማቸውን ጥልቅ ስሜት የገለጹት እንዲሁ ውዳሴ ለማሳመር የማይሆነውም በዚሁ ምክንያት ነው።

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ለመንግሥታቸው የደስታ መግለጫ መልዕክት መላካቸውንም ፔትሮ ሳሊኒ አስታውቀው ስለ ኃይልና ነገ አያይዘው ንግግር ሲያደርጉ፣ የኢትዮጵያንም ፍትሃዊነት አስረግጠው በማስረጃ አመልክተዋል።

ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ የሚመነጨው የኤሌትሪክ ኃይል ኢትዮጵያ አሁን ያላትን በሦሰት እጥፍ የሚጨምር መሆኑንም ያስታወሱት ፔትሮ ሳሊኒ ከሕዳሴ ግድብ ጋር የሚስተካከል የኒውክሌር ማበልጸጊያ ሲጨመር ደግሞ ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል በመሸጥ ወዳጅነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር እና ቀጣናዊ ልማትን ለማፋጠን ያገለግላል ብለዋል። በዚህ ድንቅ ሥራ ከጅማሮው እስከ ፍፃሜው ሂደት አሻራቸውን ላሳረፉ ሁሉም ሠራተኞች ምስጋና አቅርበዋል።

በዚህ ግድብ ግንባታ ሥራ ላይ እየተሳተፉ በነበረ ወቅት በተለያዩ አደጋዎች ሕይወታቸውን ላጡ ሠራተኞች ክብር እንደሚሰጡ እና በኅሊና እንደሚያስቧቸው ሳሊኒ ሲናገሩ የተከፈለው ዋጋ ለገባቸውና በቅርብ ለሚያዉቁ እንባቸው ማቆሚያ አልነበረውም። “ከጅምሩ ለኢትዮጵያ ውድቀት በኢትዮጵያዊ ካባ የሚጫወቱና ዘረኝነት ያጠመቃቸው ክፍሎች ሲጀመር የተከፈለው ዋጋ ስለማይገባቸው አያለቅሱም። የሚያለቅሱ ዜጎች ሲያዩም ለመቀበል ይቸገራሉ። በተልዕኳቸው መጠን በዕንባ ሊሳለቁ ይታያሉ” ሲሉ እዛው ግድቡ ላይ ዕድሚያቸውን የገፉ ይናገራሉ። እነዚህ ወገኖች ግድቡ እውን እንዲሆን የተከፈለውን ዋጋ አንድ ቀን በዝርዝር ሲቀርብና በታሪክ ለትውልድ ሲሰነድ እነዚህ ወገኖችም የህዳሴው ታሪክ የተቃራኒው ወገን ምድብተኞች እንደሚሆኑ አመልክተዋል።

“ታላቁ የሕዳሴ ግድብን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነባራዊ ሁኔታዎችን በመጋፈጥ ዛሬ ለምናየው ፍሬ አድርሰውታል” ሲሉ ፔትሮ ሳሊኒ ምስክረነታቸውን ለታሪክ አኑረዋል።

ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ” ፕሮጀክቱ ልምድ በሌለው ኮንትራክተር እንዲሰራ በመወሰኑ መንግስት 450 ሚሊየን ዩሮ ካሳ ከፍሏል” ሲሉ የሰጡትን ዝርዝር መረጃ የሰሙ ዜጎች ለውጡ ባይመጣ ኖሮ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ሰባት ዓመታት ቀርቶ ዕድሜ ልኩን ሊጠናቀቅ እንደማይችል እየገለጹ ነው። በተመሳሳይ ፕሮጀክት ዓይነት ድርሽ ብለው የማያውቁ ባለሙያዎች ተመድበውበት በነበረበት ወቅት ግብጽ ግድቡ እንደማይጠናቀቅ አውቃ ዝም ብላ ተቀምጣ እንደነበር ያስታወሱት ኢንጂነሩ ከሪፎርሙ በሁዋላ ግድቡ በወጉ መሰራት ሲጀመር ግብጽ በተለያየ መንገድ ስትገዳደር እንደነበር አመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ “የተደረገለንን ስለማውቅ ፈጣሪዬን ማመስገን እፈልጋለሁ” በማለት ከዓመት በፊት መናገራቸው የዚሁ ሚስጢር እንደሆነ የገለጸልን አንድ ሰራተኛ፣ የሕዳሴ ግድብ ብዙ ዋጋ የተከፈለበት እንደሆነ ያስረዳል። እያያቸው የተሰናበታቸው የስራ ባልደረቦቹ መኖራቸውንም ጠቁሟል።

“ይህ ግድብ እንዲገነባ ማንም አልፈለገም ነበር፤ ማንም የፋይናንስ ድጋፍ አላደረገለትም፤ በርካታ የፖለቲካ ችግሮችም ነበሩ፤ ቀላል ውሳኔዎች አልነበሩም ያሉት ፔትሮ፣ የኢትዮጵያን ባህሪ ግን በፈተናዎች እና በተግዳሮቶች መጠንከር ነው፤ ኢትዮጵያውያን ፈተናዎችን አይፈሩም” ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

“ኢትዮጵያውያን ፅኑ ናቸው፤ ተገዳዳሪ ወይም ጠላት ሲያጋጥማቸው አቅማቸውን በእጥፍ በማባዛት ማሸነፍ ይችሉበታል” ሲሉም ሳሊኒ የኢትዮጵያዊያንን አልበገርም ባይነት አጉልተዋል። እሳቸው እንዳሉት ጥቂት ባንዳዎች ቢኖሩም አብዛኞች በአገራቸው ስለማይደራደሩ ሁሉም በድል ተጠናቋል።

“ኢትዮጵያውያን ለማንም አይንበረከኩም፤ ያመኑበትን እና የፈለጉትን ነገር ከማድረግም ወደ ኋላ አይመለሱም፤ ለዚያም ነው ኢትዮጵያ ሁሉንም ተቃውሞ እና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን አልፈው ይህንን ፕሮጀክት ያሳኩት” ብለዋል።

መጀመሪያ ተቃውሞ እና ፍራቻም ነበር፤ አሁን የሕዳሴ ግድብ ውኃን የሚይዘው ንጋት ሐይቅም ሙሉ ለሙሉ ሞልቷል ያሉት ፔትሮ ሳሊኒ፣ በፊት ሲፈራ እንደነበረው ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ምንም ስጋት አለመሆኑን አስመስክሯል ሲሉ ገልጸዋል።

ቤተሰባቸው ከቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ጊዜ ጀምሮ ከኢትዮጵያ ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳለው ተናግረው ከለገ ዳዲ ግድብ እስከ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመሥራት ለኢትዮጵያ የንፁህ መጠጥ ውኃ እና የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት መሳካት ሚና መወጣቸውን ጠቁመዋል። ዛሬ በሕዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ የጋበዙት ልጃቸውም ከኢትዮጵያ ጋር መሥራት እንዲቀጥሉም ኃላፊነት ሰጥተዋቸዋል።

“ስለ ኢትዮጵያ ወርቅ አንብቤ ነበር፤ ይህ ወርቅ ግን እንደምናስበው ውዱ ብረት አይደለም፤ ይህ የኢትዮጵያ ወርቅ ውኃዋ ነው” በማለት ሳሊኒ ፔትሮ ተናግረዋል።

የቀጣዩ ዘመን ወርቅ ውሃ በመሆኑ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሶስት ግድቦችን ለመገንባት ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች ተሰምቷል። ኢትዮጵያ ማንንም ሳትጎዳ ያላትን የተፈጥሮ ሃብት ለመጠቀም እንደምትሰራ ይፋ አድርጋለች። ግብጽ በበኩሏ የተለመደውን ክሷን በመያዝ ወደ ጸጥታው ምክር ቤት ማምራቷ ተሰምቷል። ሳሊኒ የህዳሴው ግድብ በመገደቡ ግብጽም ሆነች ሱዳን አንድ ሲኒ ውሃ እንዳልጎደለባቸው ደጋግመው ተናግረዋል።

የአባይ ግድብና ኢትዮጵያ ብቻ በዓለም ታሪክ የጸጥታው ምክር ቤት አጀንዳ መሆናቸው ባለፉት ዓመታት እጅግ መነጋገሪያና እንደነበር አይዘናጋም። በሌላም በኩል ግድቡ መሸጡን፣ ለሌላ አካል መተላለፉን፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ክህደት መፈጸሙን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስም በመጥራት ሲዘግቡና አደባባይ ሲተነትኑ የነበሩ ይህ እስከተጻፈ ድረስ ይቅርታ ወይም ማስተባበያ አልሰጡም። ይልቁኑም የግንባታውን ውጣ ውረድ፣ የተከፍለውን መስዋዕትነት እንዲሁም በሁሉም አቅጣጫ ተከፍቶ የነበረውን ጫና በማሰብ አምላካቸውን በዕንባ ያመሰገኑ ላይ ሲዛበቱ ታይተዋል።


NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የአብይ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት “የኢትዮጵያ ታሪክ የሚቀየረው በስራ ነው”
ቴዎድሮስ ጠ.ሚ አብይን በይፋ አመሰገኑ፤ ድርጅታቸው ትህነግ ስለግድቡ ምንም አላለም
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2