Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  POLITICS  “ኢትዮጵያዊያን በህዳሴ ግድብ ታሪክ ሰርተን ታሪክ ላይ ቆመን ለማውራት በቅተናል” አብይ አሕመድ
POLITICS

“ኢትዮጵያዊያን በህዳሴ ግድብ ታሪክ ሰርተን ታሪክ ላይ ቆመን ለማውራት በቅተናል” አብይ አሕመድ

Ethioreview newsEthioreview news—September 9, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጥቁሮች እንደምንችል እና እንደምናሳካ ያሳየንበት ታላቅ ስራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያውያን ሕብረ ብሔራዊነት መገለጫ የሆነውን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ዛሬ ጳጉሜን 4 ቀን 2017 በይፋ መርቀዋል፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ፣ የሀይማኖት አባቶች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኦማር ጌሌ፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዴት፣ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ፣ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ፣ የስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚሶ ድላሚኒ፣ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሕሙድ ዓሊ ዩሱፍ፣ የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ እና በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክላቨር ጋቴቴ ተገኝተዋል፡፡

More stories

ደቡብ ሱዳን ስድስተኛ ሀገር ሆና የናይል ስምምነት ማዕቀፍን አጸደቀች

July 12, 2024

“ትህነግ ጦሩን እስጠግቷል፤ የጦርነት ስጋት አለብን” የጠለምት ወሰንና ማንነት አስመላሽ

June 7, 2025

“የኢትዮጵያን ህልውና የሚበይኑት የተፈጥሮ ሀብቶች…”

September 2, 2024

“ዘመን ትውልድን ይገነባል ፤ ትውልድም ዘመንን ይገነባል”

September 10, 2023

በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያዊያን በህዳሴ ግድብ ታሪክ ሰርተን ታሪክ ላይ ቆመን ለማውራት በቅተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ህዳሴ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ህዝቦች ታሪክ ሆኖ የሚኖር ነው ብለዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት አባይ እግር እንጂ አፍ አልነበረውም፣ ለዚህም ኢትዮጵያዊያን ሲያወሩለት ነበር ዛሬ ግን አባይ ራሱ ማውራት ጀምሯል ብለዋል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በጉባ ተገኝተው ይህን ታሪክ፣ ገድል፣ ማየት አለባቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህን የትውልድን ገድል ሁሉም መመልከት አለበት ብለዋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጥቁሮች እንደምንችል እና እንደምናሳካ ያሳየንበት ታላቅ ስራ ነው ብለዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የትናንት ቁጭት ማሰሪያ የመጪው ንጋት ማብሰሪያ መሆኑን አንስተው ባለፉት አምስት ዓመታት 74 ትሪሊዮን ሊትር ውሃ መያዝ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያን ጥልቅ ጨለማ፣ ከጥልቅ እንቅልፍ ያነቃ በመሆኑ የተያዘው ውሃ ንጋት መባሉን ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብልጽግና እና ልክ አይቀሬ መሆኑን ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች፤ ኢትዮጵያ ተረጂነቷ አብቅቶ ረጂ ሀገር ትሆናለችም ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን ከኛ ጋር የተገኙ ወዳጆቻችን ኢትዮጵያ ካላት ነገር ሁሉ ታቋድሳችኃላች ብለዋል፡፡

ለታችኛው የተፋሰስ ሀገራት ኢትዮጵያ ህዳሴን የገነባችው ለመበልጸግ እና አካባቢውን በብርሃን ለመሙላት እንዲሁም የጥቁር ህዝብን ታሪክ ለመቀየር እንጂ በፍጹም ወንድሞቿን ለመጉዳት አይደለም ብለዋል፡፡

ለወደፊት በምንሰራቸው ታላላቅ ስራዎች በትብብር በጋራ እንድንቆም ከአደራ ጭምር ላሳስባችሁ እወዳለው ብለዋል፡፡ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ገደሉን ተሻግረናል፣ ገድል በህዳሴ አትመናል ብለዋል፡፡

በሌላ ዜና ተመሳሳይ ዜና የኢፌዴሪ አየር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ለዘመናት የለፋንበት የኢትዮጵያ ከፍታ ማብሰሪያ የሁሉም ኢትዮጵያዊ አሻራ ያረፈበት ግድብ ለምርቃት መብቃቱን ጠቅሰው፤ በቦታው ተገኝተው ይህን በማየታቸው እንደ አንድ የሀገር ጦር መሪ ትልቅ ኩራት እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል የግድቡ መሠረተ ድንጋይ ሲጣል ጀምሮ ለምርቃት እስከበቃበት ጊዜ ድረስ የቀጠናውን የአየር ክልል በአስተማማኝነት በመጠበቅ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ካለፉት ዓመታት በተለየ ሁኔታ ተቋሙ የምድር አየር መከላከል አቅም ማሳደጉን ገልጸው፤ በሰማይ የጠላትን ዒላማ በአስተማማኝ ሁኔታ ገና ከመነሻቸው ማውደም የሚችሉ ተዋጊ የጦር ጄቶችን መታጠቁን ገልጸዋል፡፡

ግዳጅን ባጠረ ጊዜ በላቀ ብቃት የመፈፀም እምቅ አቅምና ቴክኖሎጂውን መጠቀም የሚችል የሠው ኃይል በማደራጀት በማንኛውም ሰዓት የአየር ክልሉን የማያስደፍር የሀገር ኩራት የሆነ አየር ኃይል መገንባቱንም ተናግረዋል፡፡

ዘገባው የኢዜአ ነው


POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
አቡነ ማትያስ ለህዳሴው ግድብ ምርቃት “እንኳን ደስ አላችሁ” አሉ
የአብይ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት “የኢትዮጵያ ታሪክ የሚቀየረው በስራ ነው”
Related posts
  • Related posts
  • More from author
POLITICS

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

March 28, 2026
POLITICS

አስቸኳይ የአርበኛነት ጥሪ ለኢትዮጵያን

March 4, 2026
POLITICS

ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡ

January 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2