Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ኤርትራና ትህነግ በጥምረት ውጊያ ሊከፍቱ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት ለተመድ አስታወቀ፤ “ንግግር ይቅደም”
News

ኤርትራና ትህነግ በጥምረት ውጊያ ሊከፍቱ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት ለተመድ አስታወቀ፤ “ንግግር ይቅደም”

Ethioreview newsEthioreview news—October 8, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ኢትዮጵያ ኤርትራን በተመለከተ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያስገባችው ደብዳቤ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ከቀደመው ይልቅ ጠንካራ ይዘትና አቋም የተንጸባረቀበት ሁለተኛው ደብዳቤ ለተመድ የተላከው በቅርቡት በኤርትራ መሪነት፣ በትህነግና ፋኖ ጥምረት በወልደያ አቅጣጫ የተሞከረው የተቀናጀ ጥቃት ከከሸፈ በሁዋላ መሆኑ ኢትዮጵያ ምን አስባ ነው? የሚል ጥያቄ እያስነሳ ነው። መንግስት ግን ንግግር እንዲቀድም ተማጽኗል።

በወልደያ አቅጣጫ በተለያዩ በሮች በፋኖ ስም ተከፍቶ የነበረው ጦርነት ሻዕቢያና ትህነግ በግልጽ የተሳተፉበት እንደነበርና አሁንም ድረስ ይኸው እንቅስቃሴ ቦታ እየለያየ የሚካሄድ መሆኑን የድርጅቶቹ ሚዲያዎችና ተባባሪዎች በይፋ እያስታወቁ ይገኛሉ። በተለይም የትህነግና የሻዕቢያ ሚዲያዎች እንደሆኑ የሚታወቁ በወቅቱ ጥቃቱን በሰበር ድል ሲቀባበሉት መሰነበታቸው አይዘነጋም። 

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርትራን በተመለከተ ለሁለተኛ ጊዜ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳፉት ደብዳቤ ይህንኑ እውነታ ሉዓላዊነትን የመጋፋት ድርጊት እንደሆነ አመልክቷል። ከጀርባ የዕቅዱ ባለቤት ኤርትራ እንደሆነች አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ለአንቶኒዮ ጉቴሬዝ የላከው ደብዳቤ ለሁለት አስርት ዓመታት “No war – No peace ሰላም አልባ፣ ጦርነት አልባ” ሆኖ የኖረውን የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነት በማስወገድ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የወሰዱትና ዓለም ያደነቀው እርምጃ አደጋ ላይ መውደቁን ያወሳል። 

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ኢትዮጵያ በለውጡ ማግስት የወሰደችው እርምጃ ተዘግቶባቸው ለነበሩ፣ ተለያይተው ለቆዩ ቤተሰቦች መልካም አጋጣሚ ሆኖ የትንግርት ያህል ዓለም ሲያወደሰው እንደነበር አይዘነጋም። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም ይህንኑ ታላቅ ተጋባር በመፈጸማቸው የኖቤል ተሸላሚ መሆናቸው አይዘነጋም። 

አሁን ላይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳመለከተው የሃገራቱን ግንኙነት መርህ ተኮር በሆነ ዘላቂ ግንኙነትና ጥቅም ላይ ለመመስረት የተደረገው ጥረት ሁሉ በኤርትራ መንግስት የግትርነት እና የተለላኪነት ባህሪ ችግር እንደገጠመው አስታውቋል።

ደብዳቤ አክሎም “የኤርትራ መንግስት ፅንፈኛ የትህነግ አመራሮችን ጨምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ታጣቂዎችን በጦር መሳሪያ በመደገፍ ኢትዮጵያን ለማያባራ ቀውስና ትርምስ ለመዳረግ እየሰራ መሆኑን በመጥቀስ ኢትዮጵያ ኅልውናዋን በማረጋገጥ ሉዓላዊነቷን ለማስከበር አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እንደምትገደድ አበክሮ ያስተነቅቃል። 

በመጨረሻም ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር የተገለለችበት መንገድ ቅቡልነት የሌለው በመሆኑ ኢትዮጵያ በሕጋዊ መንገድ የወደብ ባለቤት ለመሆን የያዘችው ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል በደብዳቤው ያለማመንታት ግልጽ አድርጓል።

በኤርትራ መንግስት እና በትግራይ ህዝብ ነፃነት አውጪ ግንባር (ትህነግ) መካከል የተፈጠውን ጥምረት ወይም ጥምዶ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የተቀናጀ ጥቃት ለመፈፀም የተደረገ መሆኑ ያወሳው ደብዳቤው፣ ሁለቱ አካላት ኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ለመፈጸም በዝግጅት ላይ መሆናቸውን “ደርሼበታለሁ” ብሏል። አክሎም ሁለቱ ቡድኖች እያደረጉ ያሉትን በመረጃ የተደገፈ ዝግጅት መታገስ የማይችልበት ደረጃ መድረሱን በመግለጽ “ሃይ በሉልኝ” ሲል ተማጽኗል። 

ሰሞኑን በወልድያ ከተማ መውጫና መግብያ በሮችን ጨምሮ በተለያዩ የከተማዋ ቀበሌዎችና አከባቢዎች እነዚሁ ቡድኖች በቅንጅት ባቀነባበሩት የወረራ ሙከራ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን ደብዳቤው ጠቁሟል። ውጥኑንም በግልጽ ቋንቋ በትህነግ እና በኤርትራ መንግስት ድጋፍ ነውጥ ለማካሄድ የተያዘ ውጥን እንደነበር አመልክቷል።

በተጠቅሱት አካባቢዎች ከታየው በከባድ መሳርያ የታገዘ ጦርነት መካሄዱን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዮስ የላኩት ጠንካራ ደብዳቤ ይህ እስከተጻፈ ድረስ በገሃድ ምላሽ አልቀረበበትም። 

ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ ማክሰኞ፣ መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም የተላከው ደብዳቤ በትህነግ እና በተባባሪው የኤርትራ መንግስት መካከል በተፈጠረው ጥምረት ሳቢያ በአገር ሉአላዊነት ላይ አደጋ የሚጥል እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን በጥልቅ የሚያስረዳ ነው። 

ጌድዮን ጢሞትዮስ በፃፉት ደብዳቤ፣ ቀደም ሲል በሁለቱም አካላት መካከል የተፈጠረውን ቅንጅት መንግስት መረጃ እንደነበረውና ይህንን መረጃ ለሰፊው ህዝብ ሰላም እንዲሁም የፌደራሉ መንግስት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ተቀስቅሶ የነበረውን ግጭት ዳግም እንዳይቀሰቀስ በሚል ሲሆን፣ምንም እንኳን አካሄዳቸው ጸረ ሰላም ቢሆንም መንግስት በያዘው በዚሁ የሆደ ሰፊነት አቋሙ ሳቢያ በታጋሽነት ለማለፍ መገደዱን አስረድተዋል።

ጌድዮን አክለውም፣ በኤርትራ መንግስት ዋና ጠንሳሽነት እንዲሁም በትህነግ አስተባባሪነት በፋኖ ታጣቂ ሀይሎች ተዋናይነት በወልድያ ከተማ የተሞከረውን የአመፃ እንቅስቃሴ፣ እየተጠነሰሰ ያለውን ሴራ የተባበሩት መንግስት ድርጅት የተላዩ ኃላፊዎችና በይተለይም ለዋና ፀሐፊው አንቶንዮ ጉቴሬዝ “እወቁልን” ብለዋል።

በወልድያ እና አከባቢ ተቀስቅሶ በነበረው ግጭት አድማሱን እንዲሰፋ በማድረግና በተለይም በአንዳንድ የሕገመንግስት እና የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው አከባቢዎች ግጭት ለመቀስቀስ ያለመ ተልእኮ እንደነበረው በመዘርዘር ሚኒስትሩ ለአንቶኒ ጉቴሬዝ በደብዳቤው ገልውላቸዋል።

ይሁንና፣ የከተማዋ ነዋሪዎች ባሳዩት ሆደ ሰፊነት የግጭቱን አድማስ በታቀደው ልክ ሳይስፋፋ እና  በኤርትራ መንግስት እንዲሁም በትህነግ አንጃ ቡድን መካከል የተጠነሰሰው ሴራ ሳይሳካ መቅረቱን የገለፁት ሚኒሰትሩ፣ ይህም ኢትዮጵያ ወደ ቀይባህር ለመመለስ እያደረገችው ያለችውን ጥረት ለማደናቀፍ የተሸረበ ሴራ እንደነበር አመልክተዋል።

ለዚህ ተግባር የኢትዮጵያ የሉዓላዊነት የሚጥስና የማያከብር አለፍ ሲልም  የትብብር መንፈስን የሚጥስ ተግባር በመሆኑ የዓለምዓቀፉ ማሕበረሰብ ጉዳዮን በአንክሮ እንዲከታተለው፣ እንዲሁም በዚሁ ስርዓት የጣሰ ተግባር ላይ እየተሳተፉ ያሉ አካላትን እንዲገስፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞትዮስ በደብዳቤያቸው ጠይቀዋል።

በተለያዩ ጊዜያቶች በኤርትራ መንግስት እና በትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ትህነግ) መካከል ሲፈጸሙ የቆዩትን የሽብር እንቅስቃሴዎች ምንም እንዃን የፌደራሉ መንግስት በቂ መረጃ ቢኖረውም ፣ በጋራ ለመስራት ካለው ጥልቅ ፍላጎት አንፃር ጉዳዮን በዝምታ ለማለፍ እንደመረጠ በደብዳቤው ላይ ተመላክቷል።

ይሁን እንጂ፣ በወልድያ ከተማ መግብያና መውጫ በር  አከባቢዎች በተጠቀሱት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በፀጥታ ኃየሰሎች ላይ የተከፈውን ጥቃት የፌደራሉ መንግስት በአገር ሉአላዊነት ላይ የተቃጣ ጥቃት አድርጎ እንደሚመለከተው፣ መንግስትም በአጻፋው ለሚወስደው እርምጃ ውርድ ከራሴ ብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞትዮስ ኢትዮጵያ እንደ አገር የቀይባህር ተጠቃሚነቷን ለማረጋገጥ እያደረገች ያለው ጥረት የሌሎችን አገራት ጥቅም ባከበረ፣ በውይይት እንዲሁም በመቀራረብ የሚከናወን መሆኑ በደብዳቢያቸው አምልክተዋል።

የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ታዮ አፅቀ ስላሴ በበኩላቸው መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም የሕዝብ እንደራሴዎች የጋራ ምክርቤት ላይ የአዲሱ በጀት ዓመት መክፈቻ አስመልክተው ባደረጉት ንግግር የባሕር በር ጉዳይ አስመልክተው ኢትዮጵያ የማያወላዳ አቋም እንዳላት መግለፃቸውን አይዘነጋም። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም ጉዳዩ ያለቀ መሆኑን ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው።

ወደ ቀይ ባህር ለመመለስ ኢትዮጵያ ያቀረበቻቸው አመክንዮዎች በዓለማቀፉ ማሕበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱ በተገለጸበት ቅጽበት፣ ራሳቸውን “በኢትዮጵያዊነት” የሚጠሩ ሚዲያዎችና በ”ጋዜጠናነት” ስም የሚታወቁ የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤትነት በመቃወም ሌርትራ በመወገን በግልጽ የውግዘት ዘመቻ ላይ እንዳሉ የሚታወቅ ነው።


NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የራስ ደስታ ሆስፒታል አስተዳደር ለገምጋሚዎች ያዘጋጀውን ድግስ ራሱ በላው
አብን “ሁለት-ረገጥ አካላት” ያላቸው የአማራ ክልል አመራሮችን ተጠያቂ አደረገ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2