የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እየወሰደ ባለው ማጥቃት የአሸባሪውን ኃይሎች ከአማራ ክልል እያስወጣ እንደሆነ የክልሉ መንግስት አስታወቋል። ክልሉ ወደ ሙሉ ማጥቃት መዛወሩን ይፋ ባደረግ በቀን ውስጥ ነው ይህን ያለው። የአሸባሪ ቡድኑ ወረራ በአማራ ክልል ተወስኖ ስላማይቀር የሌሎች ክልሎች ኃይሎችም የህልውና ዘመቻውን እየተቀላቀሉ መሆኑን ክልሉ ይፋ አድርጓል።
በሌላ በኩል በጦርነቱ ከተለያዩ ቦታዎች ተፈናቅለዉ ቆቦ የሚገኙ ነዋሪዎች ርዳታን እየጠየቁ ነዉ።
የአማራ ክልል እንዳስታወቀው ህዝብ ለቅረበለት ጥሪ ከበቂ በላይ ምላሽ ሰጥቷል። የአሸባሪው ኃይሎች በሰሜናዊ የአማራ አካባቢዎች ወረራ መፈጸማቸውን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በተደረገ የክተት ጥሪ ተቀብለው በርካቶች ትግሉን ተቀልቅለዋል። ትግሉን ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ ሆነው ስምሪት የሚጠብቁም ይልቃሉ።
የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን የመንግስት ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለጀርመን ድምጽ እንድተናገሩት የክልሉ ልዩ ሃይል አሸባሪው ቡድን ይዟቸው የነበረውን አካባቢዎች እያጸዳና እያስልቀቀ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
“የአሸባሪው ጥቃት በአማራ ክልል ተወሰኖ እንደማይቀርና ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንደሚሰራ በዓለምአቀፍ ሚዲያዎች ጭምር ያረጋገጠው ነው” ያሉት አቶ ግዛቸው ይህን ሴራ ለመበጣጠስ ሌሎች ክልሎችም የፀጥታ ኃይሎቻቸውን ወደ አማራ ክልል እየላኩ እንደሆነ አስረድተዋል፣ እስካሁንም ኦሮሚያና ሲዳማ ክልሎች ልዩ ኃሎቻቸውን ልከዋልም ብለዋል፡፡
አሜሪካና አንዳንድ የአውሮፓ አገራት ሕወሓት በማይካድራ በቅርቡ ደግሞ በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ግድያና ማፈናቀል ሲደርስ አንድም ቃል ሳናገሩ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ፍትሃዊ አለመሆኑንን ሃላፊው አስታውቀዋል።
ሃላፊው አይገለጹት እንጂ አላማጣን ጨምሮ የትህነግ ቡድን ለአንድ ቀን ተቆጣጥሯቸው የነበሩትን ስፋርዎች የአማራ ልዩ ሃይል አስመልሷል። እንደሚሰማው ከሆነ የአማራ ልዩ ሃይል በጦርነቱ የበላይነት ይዟል። ይሁን እንጂ አሁንም ሰላማዊ ውይይት እንደሚሻል በስፋት አስተያየት እየተሰጠ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ተፈናቅለው በቆቦ የሚገኙ ወገኖች ችግር ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ አንድ የራያ አማራየወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አመራር ለዶቼ ቬለ እንዳሉት ተፈናቃዮች በየዘመዱ ቤት ተጠግተው እንደሚገኙና አሁን እርዳታ ለማቅረብ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አስቸጋሪ መሆኑንን አመልክተዋል።
- ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?ኢራን በእስራኤልና በአሜሪካ የተከፈተባትን ጦርነት ለመመከት በሚል ሰበብ በገልፍ ሃገራት ላይ በተለይም በዱባይ አረብ ኤምሬትስ ሚሳኤልና ዱረን እየተኮሰች ቀጠናውን እያናጋች ትገኛለች። በዚህ ቀውጢ… Read more: ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?
- አስቸኳይ የአርበኛነት ጥሪ ለኢትዮጵያንኢትዮጵያን እንወዳለን፣ ኢትዮጵያ አገሬ ናት፣ ኢትዮጵያ እናቴ ናት፣ ሌላ እናት የለኝም የምትሉ ሁሉ፤ በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የምትሉ የመንግስት አካላት፣ ተቀናቃኝ ድርጅቶች፣ በየትኛውም የፖለቲካ… Read more: አስቸኳይ የአርበኛነት ጥሪ ለኢትዮጵያን
- ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡዶናልድ ትራምፕ ትኩረታቸውን ወደ ፐርሽያ ገልፍ ባላንጣቸው ኢራን በመመለስ፣ ቀደም ሲል በደቡባዊ ቻይና ባህር ትንቀሳቀስ የነበረችውን ግዙፏን “አብርሃም ሊንከን” የጦር መርከብ (Aircraft carrier)… Read more: ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡ
- “ኢትዮጵያ ወደ ባህር የመውጣት ፍላጎቷን እውቅና እንሰጣለን” ሶማሊላንድቪኦኢ – በዳቮስ የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሐመድ (ኢሮ) ያስመዘገቡት ዲፕሎማሲያዊ ድል፣ በአፍሪካ ቀንድ ለዘመናት የነበረውን የኃይል ሚዛን የናጠ ታሪካዊ… Read more: “ኢትዮጵያ ወደ ባህር የመውጣት ፍላጎቷን እውቅና እንሰጣለን” ሶማሊላንድ
- የብር እርሻ – ስደተኛው ፋኖ “ገንዘብ በእህል ሚዛን እየተካፈሉ ነው” ስራ ብዙው የሰመራ ኢምግሬሽን የአሻራ ክፍያአዲስ ሪፖርተርት – “ነፍጥ ያነገቡ ከፍተኛ ሃብት እያፈሩ ነው” እጃቸውን ባፋቸው ጭነው የሚታዘቡ። ወደ ኬንያ ድንበር ያሉት የሸኔ ታጣቂዎች ወርቅና ሌላ ማዕድን ይዝቃሉ።… Read more: የብር እርሻ – ስደተኛው ፋኖ “ገንዘብ በእህል ሚዛን እየተካፈሉ ነው” ስራ ብዙው የሰመራ ኢምግሬሽን የአሻራ ክፍያ






