Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  POLITICS  የብር እርሻ – ስደተኛው ፋኖ “ገንዘብ በእህል ሚዛን እየተካፈሉ ነው” ስራ ብዙው የሰመራ ኢምግሬሽን የአሻራ ክፍያ
POLITICS

የብር እርሻ – ስደተኛው ፋኖ “ገንዘብ በእህል ሚዛን እየተካፈሉ ነው” ስራ ብዙው የሰመራ ኢምግሬሽን የአሻራ ክፍያ

Ethioreview newsEthioreview news—November 7, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

አዲስ ሪፖርተርት – “ነፍጥ ያነገቡ ከፍተኛ ሃብት እያፈሩ ነው” እጃቸውን ባፋቸው ጭነው የሚታዘቡ። ወደ ኬንያ ድንበር ያሉት የሸኔ ታጣቂዎች ወርቅና ሌላ ማዕድን ይዝቃሉ። ሲመችም ይዘርፋሉ። ፋኖ ግብር ጥሎ ይሰበስባል። በመናበብ / ገንዘብ አሁን አለ እየተባለ / ባንክ ይዘርፋል። እያገተ በህጋዊ የባንክ አካውን ብር ይሰበስባል። ወደ ሰሜን ወሎ ብረት አውርደው ኦፓል የሚዝቁ አሉ። የትግራይ ታጣቂ አመራሮች ደግሞ ማሽን ተክለው ወርቅ ይዝቃሉ፤ መንግስት የሚልከውን በጀት ከሕዝብ ነጠቀው ያመነዥጋሉ። ሕዝብ በሁሉም ክልሎች “ነጻ እናወጣሃለን” በሚሉ ቡድኖች እየተዘረፈ፣ እየተሰቃየ፣ ልጆቹ ላይ ድንቁርና ታውጆባቸው ወዘተ ኑሮ ይገፋል። ከነዚህ ሁሉ ጀርባ “ጋዜጠኛ” የሚባሉ የሚዲያ አርበኞች አሉ። ይህ በተለያዩ አጋቦች ሕዝብ የሚለው ሃቅ ነው።

ከአማራ ክልል ወሎ የሚመጡ ወጣት ልጃገረዶች የፓስፖር አገልግሎት ለማግኘት ሠመራ ይመጣሉ። የመታወቂያውና የሌላው ክፍያ ቀርቶ ለአሻራ ከአንድ ስው እስከ ሀምሳ ሺ ብር የሚያስከፍሉ የኢምግሬሽን ሰራተኞች ሂሳቡ በየትኛው የክፍያ ተመን ያወራርዱት ይሆን? በሚል የሚጠይቁ

40/60 የሚባሉትን ጨምሮ በሃይማኖት ተቋማትና ዕምነት ላይ የተንጠለጠሉ ሚዲያዎች በተመሳሳይ የብር እርሻ ላይ ናቸው። “የት ይደርሳሉ” የተባሉ የመብት ተከራካሪዎች ሳይቀር በብር እርሻ ተይዘው የሰው ልጆችን መከራ ዘንግተዋል። እዛም እዚህም የብር እርሻ “በይዞ መገኘት” ስሌት እያስፋፉ ነው። እነዚሁ ከሁሉም አቅጣጫ ብር ማምረት ላይ የተጠመዱት “ የብር አራሾች” በከተሞች ውስጥ ንብረት እያስገዙ ሃብት እየከመሩ ነው። ወደፊት በመረጃ እንመጣባቸዋለን። አሰተምሮቱ የጃዋር እንደሆነ የሚያስምኑ ጣጣው ብዙ መሆኑንን በስጋት ይናገራሉ።

ሟቹ የ30 ዓመት ወጣት ደስታ ከትግራይ ክልል አፅቢ ወረዳ ነበር ሞትን እያሸተተ የኢትዮጵያ ድንበር ተሻግሮ በጂቡቲ ያመራው። ከጅቡቲ ወደ የመን አምርቶ ሳውዲ ዐረብያ ድንበር ደረሰ። ሳዑዲ የደረሰው አንድ ወር በፈጀ አድካሚ የበረሃ ጉዞ ነበር። አንድ ወር ሙሉ በስቃይ በረሃውን የተጓዘው ደስታ፣ የሳዑዲ ድንበር ሲደርስ ሞተ፡፡ ተገደለ። ደስታ እንደተከንተራተተ አለፈ፡፡ ደስታን የገፋው ችግር ኝ አሁንም ሌሎችን እየገፋቸው ነው። ወደ ሞት!!

More stories

ደቡብ ሱዳን ስድስተኛ ሀገር ሆና የናይል ስምምነት ማዕቀፍን አጸደቀች

July 12, 2024

“ትህነግ ጦሩን እስጠግቷል፤ የጦርነት ስጋት አለብን” የጠለምት ወሰንና ማንነት አስመላሽ

June 7, 2025

“የኢትዮጵያን ህልውና የሚበይኑት የተፈጥሮ ሀብቶች…”

September 2, 2024

“ዘመን ትውልድን ይገነባል ፤ ትውልድም ዘመንን ይገነባል”

September 10, 2023

ደስታ የሳውዲ ድንበር ለመሻገር ሲሞክር ሕይወቱ ማለፉን ወላጆቹ ሰሙ። የፈረደበት ቤተሰብ፣ በተለይም እናት ሃዘን አንጀቷን እያቃጠለው አለች። ይህን ያሉት የትግራይ ክልል ወቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሐዲሽ ስባጋድስ ናቸው። 

በትግራይ ብቻ ሳይሆን በአማራ ክልልም ዕድሜያቸው ለአቅመ አዳም ያልደረሰ ታዳጊዎችን ጨምሮ ሰፊ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ቀዬያቸውን ጥለው እየፈለሱ ነው። የአፋሯ ሰመራ ከተማ ለዚህ ብቁ ምስክር ናት፡፡ በሰመራ እስር ቤት የተከማቹት ኮብላዮችን “ማን ይዘንላቸው?” የሚለው ጥያቄ ከተነሳ ቆይቷል። ሰሚ ግን የለም። እንዲያውም ጉዳዩ ቢሮ ለተቀመጡ “ ታጋዮች” ሲሳይ ሆኗል ነው የሚባለው። መረጃም የሚቀርበው። ጭካኔ!! ታላቁ መምህር ፕሮፌሰር መስፍን “ ከሽፈናል” ያሉት ይኸው ታይቷቸው እንደሆነ አስተያየት ሲሰጥ ያልገባቸው ዛሬ። ዛሬ የኔታን በ “ነብሳቸውን ይማረው” እያሰቡ ናቸው።

“ለትግራይ እናቶች አልቅሶ እርም ማውጣት “ታላቅ” ወግ ነው። ቁርጣቸውን ሳያውቁ ዘወትር ደጅ ደጁን እያዩ ልጆቻቸውን እየናፈቁ ከሚኖሩት ወላዶች ይልቅ፣ ሃዘን የተቀመጡ “ዕድለኞች” ተብለዋል። “ልጆቹ ምን ያድርጉ እቀዬያቸው ቢሆኑም ጦርነቱ ይበላቸዋል። ሲሰደዱም በረሃ፣ ወይም ጥይት፣ ወይም ውሃ ይበላቸዋል፤ የሻርክ ቀለብ ይሆናሉ። ምን ይሻለን ይሆን? ሁሉም ጋር ሞት ነው” የሚሉ ይህ ሁሉ ጣጣ ስልጣንና ገንዘብ በማይጠግቡ ህሊን ቢሶች ሳቢያ እንደሆነ ይናገራሉ። ብር ማቁጠር ያቃታቸው ዘራፊዎች በእህል ሚዛን ሲካፈሉ ያዩ ሲመሰከሩ የሚሰማበት ዘመን ላይ ተደርሷል።

አፋር ክልል የፀጥታ አካላት በአደባባይ ስደተኛ ወጣቶችን የታደጉ ልመስላሉ፤ በበርሃ ሕይውታቸው እንዳያልፍ በቁጥጥር ስራ ማዋላቸው አግባብ ቢሆንም፣ ከደላላ የተረፈች ገንዘባቸውን እነሱም እንደሚቀበሉዋቸው የከፈሉ ይናገራሉ፤

በትውልድ አገሩ ስደተኛው ፋኖ መሆኑን የሚናገረው ጎበዝ “ገንዘብ መቁጠር ስላልተቻለ፣ በእህል ሚዛን እየቆጠሩ ሲካፈሉ አየሁና አበቃሁ” ይላል፡፡ ለነጻነት ትግል ጠብ መንጃ ለማንሳት መገደዳቸውን የሚገልጹ ቡድኖች ገንዘብ በወፍጮ ቤት እህል እየመዘኑ መካፈላቸው ለሚሰሙ እናቶች መጥኔ ከማለት ውጭ ምንም ሊባል እንደማይችል ይኸው ምስክር ያናገራል። “ጨዋታው ብር ነው፣ ንግድ ነው፣ ዝርፊያ ነው …” የሚሉት ለካስ እውነታቸውን ነው።

“መኖሪያዬን ከበቡት። ቁጥራቸውን በትክክል አላወኩትም። እኔም ፋኖ ነኝ። እነሱም ፋኖ ናቸው። ምን እንደሰሙብኝ አልገባኝም። አኩርፌ ኝ ነበር። ነገሩ ዘረፋ በመሆኑ አልወደድክትምና ተለይሁዋቸው። አንድ ቀን በሌሊት መጡና እጄን እንድሰጥ ጠየቁኝ። ይህኔ ገጠምን” ሲል የገጠመውን ያስረዳል። “ስደተኛው ፋኖ በሉኝ” ያለው ዑመር (ስም የተቀየረ) የጎንደር አካባቢ ተወላጅ / አካባቢውን መግለጽ አግባብ እንደማይሆን በመጠየቁ አልተገለጸም/ የአገር ውስጥ ስደት ህመም እንደሆነ ያስረዳል። 

“አሁን በትክክል የት ነው በስደት ያለኸው?” ለተባለው “ ጊዜው ገና ነው” የሚል መልስ በመስጠት ወደ ግጥሚያው አመራ። “ እኩለ ለሊት ጀምሮ ገጠምን። በሁለት አቅጣጫ መሳሪያ ጠምጄ ቦታ እየቀያየርኩ ተታኮስን” መጨረሻ ላይ “ ወገኖቼ” የሚላቸው ፋኖዎች ሊነጋጋ አካባቢ ተኩስ አቁመው ተሳድበውና ዝተው  ሄዱ” 

ውሃ ጠምቶት ስለነበር ከድካሙ ጋር ተያይዞ እንቅልፍ እዛው አነጣጠረበት መደብ ስር ጣለው። ሲነቃ ጀንበር ደጁን ዘልቃለች። “ስድስት የሚሆኑትን እንደጣልኩ አስታውሳለሁ” ያለው ስደተኛው ፋኖ ለአካባቢው አስተዳደር እጁን ሰጠ። 

እጁን የሰጠበት የመንግስት መዋቅር የጸጥታ ኃላፊ በመኪናቸው ይዘውት ወደ ቢሮ እየወሰዱት እያለ ስልካቸው ጮኸ። አነሱት። ሰላምታ ከተቀያየሩ በሁዋላ “ ያ … /ሃይማኖቱን ጠርቶ እንደሰደበው ይናገራል/ ስድስት ጣለብን። ቆይ እያሉ ሲነጋገሩ ሰማሁ። ወዲያው ከሰው ጋር ነኝ በሁዋላ እደውላለሁ አሉና ስልኩን ዘጉት” ውዲያው የጸጥታው ኃላፊ “ስድስቱን ጣልካቸው” ሲል ጠየቀው። ይህኔ ፋኖዎቹና የጸጥታ ኃላፊው ወዳጅ መሆናቸውን ተገለጸለት። እዛች አካባቢ መቆየት አደጋ እንደሆነበት አመነና ወዲያው ስደተኛ ለመሆን ወስኖ “ስደተኛ” ሆነ። እስከመቼ ? የሚታወቅ ነገር የለም። ወደ ሳዑዲ እንደሚያቀና ግን ተናግሯል። የስልክ ምልልሳችን እንዳበቃ “የደስታና ደስታን መሰሎች እጣ እንዳይገጥምህ” አልነው፡፡

ሰሞኑን የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ይፋ ባደረገው መረጃ በቻይኖች ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰዎችን አግተው አራት ሚሊዮን ብር የተቀበሉትን፣ ብሩ የገባበትን አካውንት ተከትሎ ብሩ እንዳይነቀሳቀስ በማድረግ ጠቅላላ ተጠርታሪዎችን መያዙን አስታውቋል። ምነው አማራ ክልል እንዲህ ማድረግ ከባድ ሆነ? የበርካቶች ጥያቄ ነው። ነገሩ ሁሉም በመናበብ ብር አቸዳ ላይ ናቸዋ!! ምስኪን ይዘረፋል!!

በአፋር በኩል ወደ ሳዑዲ ለመሸጋገር ከትግራይ ክልል የሚኮበልሉት አብዛኞቹ ወንዶች ናቸው። የሰመራ ተባባሪዎች ባሰባሰቡት መረጃ መሰረት የትግራይ ተወላጆች ወደ አፋር የሚኮበልሉት ተስፋ ቆርጠው ነው። ስራ የለም። ጦርነት ጎድቷቸዋል። አሁን ደግሞ ሌላ ጦርነት ሊነሳ እንደሚችል ስጋት ስለገባቸው ነው። 

ከአማራ ክልል የሚኮበልሉት ደግሞ በበዛት ሴቶች ናቸው። ከወሎ ያነጋገርናቸው እንደሚሉት እነዚህ ኮብላዮች በብዛት የሚነሱት ትምህርት ቤቶች በተዘጉባቸው አካባቢዎች ሲሆን፣ የሚኮበልሉት ቤተሰብ ሳያውቅ በድብቅ ነው። እናም እግራቸው ከቤት ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቤተሰብ ሃዘን ያውጃል።

ከጦርነት በኋላ ወደ አፋር የሚፈልሱት የትግራይና የአማራ ወጣች በጅቡቲ በኩል ድንበር በማቋረጥ ወደ የመንና ሳዑዲ ለማምራት ነው፤ እነዚህ ወገኖች ከጦርነት የተረፈች ነፍሳቸውን ለማዳን በረሃ ለበረሃ ሲንከራተቱ የአውሬ፣ የአሸባሪና የውሃ እራት ይሆናሉ

አስኮብላዮቹ አሁን አሁን ዓይን አውጥተዋል። መጀመሪያ የሚከፈል ገንዘብ እንደሌለ በማስረዳት ልጆቹን በደላላ ያስኮበልላሉ። ልክ ጅቡቲ ድንበር ሱያደርሷቸው እስከ 400 ሺህ እንዲያስገቡ ስልክ ያስደውላሉ። የፈረደበት ቤተሰብ ንብረት ሸጦ፣ ለምኖ፣ ተበድሮ “አስገቡ” በተባሉበት አካውን የተጠየቁትን ገንዘብ ያስገባል። በመከራ የተሰብሰበውን ገንዘብ ወኪል፣ ደላላ ወይም ቤተሰብ ያለ አንዳች መሸማቀቅ ባንክ ሄዶ ይረከባል፤ ወይም …

ከሰመራ ከተማ ኮብላዮች እንዳስረዱን ከሆነ ያልተያዙትን ፖሊስ በየመንገዱ ገንዘብ ይቀበላቸዋል። ኢምግሬሽን ፓስፖርት ለማውጣት የሚሄዱትን ደግሞ “የአሻራ” በማለት ሃምሳ ሺህ ያስከፍሏቸዋል። የሰመራ መታወቂያም እንዲሁ በብር ይሰራላቸዋል። 

የትግራይ ልጆችን መስለው በርካታ ኤርትራዊያንም መታወቂያ እየተሰራላቸው ህጋዊ አገልግሎት እያገኙ እንደሆነ የሚጠቁሙ አሉ። 

ዛሬ በሕዝብ ስም “ነጻ እናወጣሃለን” የሚሉ ብር መቁጠር አቅቷቸው በእህል ሚዛን እየመዘኑ እየተካፈሉ ነው። በሰሜን ወሎ ኦፓል የሚያፍሱ “ነጻ አውጪዎች”፣ በትግራይ ወርቅ የሚያመርቱ፣ በጋምቤላ፣ በሞያሌ ኬንያ ድንበር፣ በወለጋ፣ እንዲሁ ማዕድን መዛቅ ንግድ የሆነላቸው እርቅን አይሹም። ማዕድኑ ጋር ያልደረሱ “ከማን አንሼ” በሚል እገታና ዝርፊያ ላይ ተሰማርተዋል። ይህን ትግልና እንዲህ ያለውን የትግል ፍሬ ነው በውጭ አገር ተቀምጠው ዶላር በማሰባሰባሰብ ድጋፍ እንዲደረግ በቅብብሎሽ ቅስቀሳ የሚደረገው። ህዝብ እየጮኸ ነው!! ህዝብ እያለቀሰ ነው!!

ማሳሰቢያ በአማራና ትግራይ ወጣቶች ላይ ትኩረት ያደረገው ሪፖርት በቀጣይ የኦሮሚያን ጉዳይ አካቶ ያተናከረውን መረጃ ያቀርባል። መረጃ ያላችሁ

ፎቶ = ሰመራ በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ የአማራና ትግራይ ወታቶች ናቸው። የላይናው መሪ ፎቶ የኦሮሞ ተወላጆች ጅቡቲን ሲያቋርጡ ሂውማን ራይጽ ዎች ይፋ ያደረገው ምስል ነው

POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ስማቸው የሚደበቅላቸው ታጣቂዎች በአርሲ የፈጸሙት ግድያ “ከፖለቲካ ፍጆታ በላይ ሊታይ ይገባል”
የኢሳያስ ዕቅድ እንደሆነ የተነገረለት ወረራ በአፋር ክልል ተፈጸመ፤ አፋር ክልል “ራሴን እከላከላለሁ” አለ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
POLITICS

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

March 28, 2026
POLITICS

አስቸኳይ የአርበኛነት ጥሪ ለኢትዮጵያን

March 4, 2026
POLITICS

ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡ

January 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2