Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  POLITICS  ጀርመን ፖሊሲ በሃማስ – “ጸረ ሴማዊነትንና ሽብርን የሚደግፉ የጀርመን ፓስፖርታቸውን ይነጠቃሉ”
POLITICS

ጀርመን ፖሊሲ በሃማስ – “ጸረ ሴማዊነትንና ሽብርን የሚደግፉ የጀርመን ፓስፖርታቸውን ይነጠቃሉ”

Ethioreview newsEthioreview news—October 18, 2023
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ጀርመን የኢሚግሬሽን ህጓን እያሻሻለች መሆኑን የጠቀሱት ክሊንግቢል ጸረ ሴማዊነትን እና ሽብርን የሚደግፉት ግን የጀርመን ፓስፖርታቸውን ይነጠቃሉ ብለዋል።

በእስራኤል ሃማስ ጦርነት ጀርመን የምትከተለው ፖሊሲ

በእስራኤል ሃማስ ጦርነት ጀርመን የምትከተለው ፖሊሲ
ጀርመንን ጨምሮ በአውሮጳ፣ አሜሪካና ሌሎች ሃገራት “አሸባሪ” ተብሎ የተሰየመው ሐማስ በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 7 ቀን 2023 ዓ.ም የጋዛን አጥር ሰብሮ በመግባት በሙዚቃ ድግስ ላይ የነበሩትን ስቪል እስራኤላውያን ላይ በፈጸመው ጥቃት ከ260 በላይ እስራኤላውያን መሞታቸውን ተዘግቧል። ከዚያም ቀጥሎ ሃማስ ወደ እስራኤል በተኮሳቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ተወንጫፊ ሮኬቶችና ከባድ መሳሪያዎች እንዲሁም እስራኤል በወሰደችው የአጸፋ እርምጃ ከሁለቱም ወገኖች በርካታ ንጹሃን ስቪል ዜጎች አልቀዋል። እስከዛሬ ረፋዱ ድረስ የነበሩ የጉዳት መጠንን የሚያመላክቱ ይፋዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት እስራኤል በፈጸመችው የበቀል እርምጃ ከፍልስጤማውያን በኩል 2,800 ገደማ ሲሞቱ  ሃማስ ባስወነጨፋቸው ሮኬቶችና መድፎች ደግሞ ከ 1,400 በላይ እስራኤላውያን ሞተዋል።  ከሁለቱም ወገን ከ6ሺህ የማያንሱ ሰዎች እንደቆሰሉም የተለያዩ ዘገባዎች ያመላክታሉ።
በሁለቱም በኩል የቀጠለውና ሁለተኛ ሳምንቱን ያሳለፈው ጦርነት ወደ አካባቢው ሐገራት እንዳይዛመት አስግቷል። በተለይም “ከጀርባ አለች” የምትባለው ኢራን በቀጥታ እጇን ካስገባች ጦርነቱ ከቀጠናዊ ጉዳይንነት ወጥቶ ዓለም አቀፋዊ ቅርጽ ሊይዝ እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።
የተለያዩ የዓለም ሃገራት በዚህ ጦርነት ላይ የሚከተሉት ፖሊሲና ሊኖራቸው ስለሚገባ ሚና በይፋ እየገለጹ ነው። ጀርመንም ጦርነቱን በተመለከተ የምትከተለውን ፖሊሲና በሃገር ውስጥም መተግበር ስለሚገባቸው መመሪያዎች ይፋ አድርጋለች።
የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስ ለምክር ቤት እንደራሴዎች ባደረጉት ንግግር እንደተናገሩት።

” በዚህ ወቅት ጀርመን አንድ አማራጭ ብቻ ነው ያላት፤  ከእስራኤል ጎን መቆም። ይህም  ለእስራኤል ደህንነት መቆም ትልቁ የጀርመን መንግስት ቁርጠኝነት ነው ማለታችን ነው። ከራሳችን ታሪክ ከሆሎኮስት የመነጨው ሃላፊነት፤ የእስራኤልን መንግስት ህልውና እና ደህንነት መደገፍ ዘልአለማዊ ያደርገዋል።
 በእስራኤል የሃገሪቱን ዜግነት የወሰዱ በሺዎች የሚቆጠሩ ጀርመናውያን አሉ። በዚህ በጀርመንም በሺዎች የሚቆጠሩ የጀርመን ዜግነት የወሰዱ እስራኤላውያን ይኖራሉ። በሃማስ ከታገቱት መካከል በርካታ ጀርመናውያን ይገኙበታል።”

ስለ ኢራን

ከሃማስ ጀርባ ኢራን እንዳለችበት አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ሃገራት ይከሳሉ። መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስም ከኢራን ድጋፍ ውጭ ሃማስ ይህን ጥቃት ሊፈጽም እንደማይችል ነው ያስረዱት።

“ሃማስ ከአለፉት ዓመታት ጀምሮ ያለኢራን ድጋፍ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ጥቃት በእስራኤል ግዛት ውስጥ ሊፈጽም አይችልም። የኢራን አገዛዝ ባለስልጣናትና አንዳንድ የመንግስት ተወካዮች ጥቃቱን አስመልክተው የሰጡአቸው መግለጫዎች በጣም የወረዱ እና ደስ የማይሉ ናቸው። በቴህራን ውስጥ ያለው አመራር ያለምንም ሃፍረት እውነተኛ ገጽታውን እየገለጠ ነው። ይህም በጋዛው ጦርነት ላይ ያለውን ሚና ያረጋገጠ ነው።”

More stories

ደቡብ ሱዳን ስድስተኛ ሀገር ሆና የናይል ስምምነት ማዕቀፍን አጸደቀች

July 12, 2024

“ትህነግ ጦሩን እስጠግቷል፤ የጦርነት ስጋት አለብን” የጠለምት ወሰንና ማንነት አስመላሽ

June 7, 2025

“የኢትዮጵያን ህልውና የሚበይኑት የተፈጥሮ ሀብቶች…”

September 2, 2024

“ዘመን ትውልድን ይገነባል ፤ ትውልድም ዘመንን ይገነባል”

September 10, 2023

ስለፍልስጤም ባለስልጣናት

 ከዚ በተጨማሪ ሾልስ በእስራኤል ስለደረሰዉ ጥቃት የፍልስጤም ባለስልጣናት ዝምታን አውግዘዋል።

“የፍልስጤም ባለስልጣናት እና ፕረዚደንት ማህሙድ አባስ ለምን ይህን የሽብር ጥቃት አላወገዙም ብዬ እራሴን እጠይቃለሁ። ዝምታቸው አሳፋሪ ነው ለማለት እወዳለሁ።”

ለፍልስጤም ስለሚደረጉ የልማት ድጋፎች

 ሾልስ ለፍልስጤማውያን ስለሚደረገው ድጋፍም መንግስታቸው የሚከተለውን ፖሊሲ ይፋ አድርገዋል። ከፍልስጤም ጋር የሚኖረው የልማት ትብብር እንደሚያጤኑት እና የእስራኤልን ደህንነትና ጸጥታን በሚያረጋግጥ መልኩ እንደሚፈጸም አስረድተዋል። ከጀርመን መንግስት በኩል የሚደረጉ ማንኛውም ድጋፎች በሃማስ እጅ እንዳይወድቁ መንግስታቸው ብርቱ ጥንቃቄ እንደሚያደርግም ነው መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስ ይፋ ያደረጉት።
በጀርመን ስለሚኖሩ የሃማስ ደጋፊዎች
ሌላው መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስ ያነሱት ጉዳይ በጀርመን ውስጥ የሚኖሩ የሃማስ ደጋፊዎችን በተመለከተ ነበር። የሃማስ ደጋፊዎች በተለያዩ የጀርመን ከተሞች ባካሄዷቸው ሰልፎች የእስራኤልን ባንዴራ አቃጥለዋል፤ ጀርመንን ጨምሮ በአውሮጳና አሜሪካ እንዲሁም በሌሎች ሃገራት “አሸባሪ” ተብሎ የተፈረጀውን ሃማስን እንደሚደግፉ ገልጸዋል። መራሄ መንግስቱ በእነዚህ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ነበር አስረግጠው የተናገሩት። የሃማስን ድርጊት አጥብቀን እናወግዛለን ያሉት ሾልስ ከምንም በላይ ይህን ጥቃት በመላው አካባቢው ላይ ወደለየለት ግጭት እንዳይቀየር የምንችለውን ሁሉ እያደረግን ነው፤ እናም ሁሉም ሰው በዚህ ሁኔታ ሽብርን ከማባባስና ከማስቀጠል እንዲቆጠብ እናስጠነቅቃለን ሲሉም አክለዋል።
ይህን ሽብር የሚያወድስና የሚደግፍ ሁሉ ተጎጂዎችን ማዋረድ ብቻ ሳይሆን ሰብአዊ ክብርንና የጀርመንን ህገመንግስት የረገጠ ተግባር ነው። እንደዚህ አይነት ተግባር ያስደነግጠኛል ትክክልም አደለም። በማለትም ለሸንጎው አስረድተዋል።

የጀርመን ካርታ
የጀርመን ፌደራላዊ ክፍለግዛቶችምስል DesignIt/Zoonar/picture alliance

በጀርመን ለሃማስ ድጋፍ ያረርጋሉ የተባሉት የተለያዩ አደረጃጀቶችም እንደሚታገዱም ነው ጀርመን ያስታወቀችው። ከነዚህም አንዱ ሳሚ ዱን የተባለ የፍልስጤም የትብብር መረብ እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የትብብር መረቡ አባላት በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ሃማስ በእስራኤላውያን ላይ ጥቃት በመፈጸሙ ደስታቸውን ሲገልጹ፤ እንዲሁም ለአላፊ አግዳሚው እንደቸኮሌት ያሉ ጣፋጭ ነገሮችን ሲበትኑ ታይቷል። መራሄ መንግስት ሾልስ ይህን ድርጊት የጀርመንን እሴቶች እንደሚጻረር በመግለጽ በጀርመን ውስጥ በምልክት ጭምር የሃማስን የወንጀል ድርጊቶችን ማወደስ በሕግ እንደሚያስጠይቅ በአጽንኦት አስረድተዋል።
በጀርመን ውስጥ ወደ 500 የሚሆኑ የትብብር መረቡ አባላት ያሉ ሲሆን አብዛኛዎቹ የጀርመን ዜግነት ያላቸው መሆኑን ይነገራል። የጀርመን የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ እንዲህ ዓይነት ድርጊት የሚፈጽሙትን ፓስፖርታቸው እንደሚነጠቁና እንደሚባረሩ ነው ያስጠነቀቀው።
ሚንስቴር መስሪያቤቱ  በሃማስ ደጋፊዎች ላይ ጠንከር ያለ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ በገለጸበት መግለጫው  የሃማስ ደጋፊዎችን ከሃገሩ እንደሚያባርራቸው በሚኒስትሯ በኩል ይፋ አድርጓል። የጀርመን የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር  ናንሲ ፌዘር የሃማስ ደጋፊዎችን ለማባረር ማንኛውም ሕጋዊ እርምጃ እንጠቀማለን ሲሉ ነው በመግለጫቸው የተናገሩት።
የ ናንሲ ፌዘር መግለጫ በሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪም ድጋፍ አግኝቷል። የፓርቲው መሪ ሎርስ ክሊንግቢል “የሃማስ ደጋፊዎች፤ በጎዳናዎች ላይ ወጥተው ሃማስን የሚደግፉ ከሆነ  ከጀርመን ይባረራሉ” ሲሉ ዝተዋል። አክለውም በሃማስ ደጋፊዎች ላይ ሁሉም ሕጋዊ እርምጃዎች ይወሰዳሉ ብለዋል።
ጀርመን የኢሚግሬሽን ህጓን እያሻሻለች መሆኑን የጠቀሱት ክሊንግቢል ጸረ ሴማዊነትን እና ሽብርን የሚደግፉት ግን የጀርመን ፓስፖርታቸውን ይነጠቃሉ ብለዋል።

dw report


  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
    ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ እስከታተመ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
    አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
    ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
    ቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በድንገተኛ… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
    ቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ ባለሙያዎች ስህተት”… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
China Focus: Belt and Road celebrates decade of achievements with fresh commitments
Awdal State Movement invited Ethiopia to own a Somali port
Related posts
  • Related posts
  • More from author
POLITICS

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

March 28, 2026
POLITICS

አስቸኳይ የአርበኛነት ጥሪ ለኢትዮጵያን

March 4, 2026
POLITICS

ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡ

January 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2