Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  law  በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን የክስ መቃወሚያ ብይን ተሰጠ
lawTIPS 1

በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን የክስ መቃወሚያ ብይን ተሰጠ

Ethioreview newsEthioreview news—May 27, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ፍርድ ቤቱ በአዋጅ 882 መሰረት የቀረበው ክስ ከባድና ከ10 ኣመት በላይ እስር ፍርድ ስለሚያስከትል የዋስትና መብት ጥያቄውን በዛሬው ችሎት ውድቅ አድርጓል።ፍርድ ቤቱ ጠበቆች አቃቤ ህግ ሆን ብሎ በዚህ አዋጅ የከሰሰው የዋስትና መብት ለማስከልከል ነው ብለው ያቀረቡትንም መቃወሚያ በክስ ሂደት የሚጠራ መሆኑን ጠቅሶ ዋስትናውን ሳይፈቅድ አልፎታል፡፡

ዛሬ ያስቻለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሶስተኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት «ከባድ አታላይነት የሙስና ወንጀል እና ሰነዶችን አስመስሎ የማዘጋጀት» የክስ ሂደት ላይ የተከሳሾች ጠበቆች መቃወሚያ ብይን ለመስማት ቀርበዋል። በችሎቱ አንደኛ ተከሳሽ ቀሲስ በላይ ከሁለተኛ ተከሳሽ ጋር ቀርበው የክስ መቃወሚያ ብይናቸውን ስሰሙ የሶስተኛ ተከሳሽ የክስ መቃወሚያም ዛሬ በጠበቃቸው በኩል ቀርቧል፡፡ አራተኛ እና አምስተኛ ተከሳሾች ግን ዛሬም ስላልቀረቡ ፖሊስ በቀጣይ ችሎት እንዲያቀርባቸው አሁንም ትእዛዝ ተላልፏል፡፡

የዋስትና ጥያቄ ክርክር

ሶስቱ ተከሳሾች በቀረቡበት ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በተለይም የአንደኛ እና ሁለተኛ ተከሳሾች ጠበቆች በደንበኞቻቸው ላይ በሀሰተኛ ሰነድ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል የቀረበው ክስ፤ የመንግስት ወይም እንደ ባንክ ያሉ ህዝባዊ ድርጅት ሰራተኞች ባልሆኑበት የማታለል ወንጀል ክሱ የሙስና ወንጀሎች ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 32 (2/3) መሰረት የሚሸፈን አይደለም ብለው ተከራክረው ነበር የአቃቤ ህግ ክስ ላይ መቃወሚያቸውን ያቀረቡት፡፡ የቀሲስ በላይ መኮንን የችሎት ውሎጠበቆች አክለውም ተጎጂ ሊሆን ነበር በተባለው በህዝባዊ ድርጅቱ ላይ የደረሰ ጉዳት ወይም በተከሳሾች የተገኘው ጥቅም በሌለበት አግባብ አቃቤህግ ክሱን አክብዶ ያቀረበበት ሂደቱ አግባብነት የሌለውና ተከሳሾች የዋስትና መብት እንዳያገኙ ሆን ብሎ ያደረገው ነው በማለትም ክሱን ተቃውመውታል፡፡ ጠበቆች አክለውም ተከሳሾች በተለይም አንደኛ ተከሳሽ የሀይማኖት አባትና ተሰሚነት ያላቸው ግለሰብ እንደመሆናቸው፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪና ቋሚ አድራሻ ያላቸው መሆኑን እንዲሁም ታማሚ መሆናቸው ግንዛቤ ውስጥ ገብቶ በወንጀል ህግ ተጠይቀው የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው በሚል ተከራክረዋል፡፡ 

በዚሁ የጠበቆች መቃወሚያ ላይ ዝርዝር ምላሽ የሰጠው ከሳሽ አቃቤህግ በተከሳሾች ሊደርስ የነበረው ጉዳት ከፍተኛ ስለነበር፤ በጸረ-ሙስና ልዩ የስነስርዓትና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 434/2005 እንዲሁም በአዋጅ 882/2007 በተሻሻለው አንቀጽ 2/3 መሰረት ከ10 ዓመት በላይ በሚያስቀጣ የሙስና ወንጀል የተከሰሱ በመሆኑ የዋስትና መብት በግልጽ ያስከለክላል በማለት መቃወሚያውን ውድቅ ይደረግ ሲል ሞግቷል፡፡ አቃቤህግ አክሎም ተከሳሾች “በወንጀሉ ሊያገኙት ነበር” ካለው “ያልተገባ ጥቅም” በተጨማሪ ካላቸው የገንዘብ አቅምና እውቅና አንጻር ወደ ውጪ ሊያወጡ የሚችሉ መሆኑን እንዲሁም “አሁንም በእስር ላይ ከሚገኙ ተከሳሾች ጋር በግብራበርነት የተሳተፉ” ያሏቸው ሌሎች ሁለት ተከሳሾች በምርመራ ወቅት ተፈልገው ያልተገኙ ከመሆኑ አንጻር “በህግም ሆነ በሁኔታ ሊሰጥ የሚችለው የዋስትና መብት ውድቅ እንዲደረግ” በማለት ፍርድ ቤቱ ወደ ቀጣይ የክርክር ሂደት እንዲገባም ጠይቋል፡፡የእነ ቀሲስ በላይ መኮንን የችሎት ውሎ

የዋስትና መከልከል ብይን

More stories

በማስገደድ በመውሰድ ከባድ የውንብድና ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በ11 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

May 25, 2021

የሙዚቀኞች የሮያለቲ ክፍያ  የፊታችን ሀምሌ 1 ወደ ስራ ሊገባ ነው

April 2, 2025

ሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል ጥፋተኛ የተባለው ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ዐቃቤ ህግ ጠየቀ

July 15, 2021

ከአምስት አመት በፊት በእንጀራ እናቷ ተገደለች የተባለችው ግለሰብ በህይወት ተገኘች

April 18, 2021

ይህን የግራ ቀኝ ክርክሩን ያደመጠው ፍርድ ቤቱ በተለይም በአዋጅ 882 መሰረት የቀረበው ክስ ከባድና ከ10 ኣመት በላይ እስር ፍርድ ስለሚያስከትል የዋስትና መብት ጥያቄውን በዛሬው ችሎት ውድቅ አድርጓል፡፡ ፍርድ ቤቱ ጠበቆች አቃቤ ህግ ሆን ብሎ በዚህ አዋጅ የከሰሰው የዋስትና መብት ለማስከልከል ነው ብለው ያቀረቡትንም መቃወሚያ በክስ ሂደት የሚጠራ መሆኑን ጠቅሶ ዋስትናውን ሳይፈቅድ አልፎታል፡፡

ፍርድ ቤቱ የክሱ ትክክለኛነትን በተመለከተ በጠበቆች የቀረበውን መቃወሚያ እና በጠበቆች መቃወሚያ ላይ ዛሬ ከሳሽ አቃቤህግ በጽሁፍ ያቀረበውን ምላሽ ተመልክቶ ብይን ለመስጠት ለግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም በተመሳሳይ ጭብጥ የክስ መቃወሚያቸው ዛሬ በጠበቆች የቀረበው የሶስተኛ ተከሳሽ መቃወሚያ ላይም ከተለዋጭ ቀጠሮው አስቀድሞ የአቃቤ ህግ የጽሁፍ ምላሽ ተሰጥቶ አንድ ላይ ብይን እንዲሰጥ እና እስካሁን ያልተያዙ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾችም በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡

ሊቀአዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን እና ሌሎች ተከሳሾች ዛሬ የዋስትና መብትን በፍርድ ቤቱ መነፈጋቸውን ተከትሎ ፖሊስ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ብጠይቅም፤ ቀሲስ በላይ ያቀረቡት የህክምና ክትትል ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ እስከ ቀጣይ ቀጠሮ ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ብቻ አሁን በሚገኙበት ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ ችሎቱ አዟል፡፡

ሊቀ ዐዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በሚያዚያ ወር መጀመሪያ የአፍሪካ ኅብረት ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ “ከኅብረቱ የክፍያ ሰነድ ጋር ተመሳስለው የተዘጋጁ” በተባሉ ሀሰተኛ ሰነዶች በመጠቀ ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ከህብረቱ የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ ሒሳብ ለማዘዋወር ሲሞክሩ ተገኝተዋል በሚል በፖሊስ መያዛቸው ጠቅሶ የጀርመን ድምጽ ከችሎት ዘግቧል

homelaw
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ሁሉም ይረዳን  አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ነን” የራያ ነዋሪዎች ጩኸት “በአላማጣ ከተማም በሌሊት የተደራጀ ዘረፋ እየተካሄደ ነው”
ቦይንግ ኩባንያ የአፍሪካ ዋና ጽሕፈት ቤቱን አዲስ አበባ ሊከፍት ነው፤ የአውሮፕላን አካላትንና መለዋወጫዎችን የማምረት ስምምነት ተደረሰ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
law

ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀል የፈጸሙ 123 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሒሳብ ታገደ

September 20, 2025
TIPS 1

WFP Country Director Says Ethiopia Registered Significant Economic Transformation by Focusing on Rural Dev’t, Poverty Reduction

July 28, 2025
law

እነ ቀሲስ በላይ በሙስና ወንጀል ሊፈርድባቸው እንደማይገባ ጠቅሰው ያቀረቡት ይግባኝ ውድቅ ሆነ

July 26, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2