Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  ማህደር  ተደብቆ የቆየው የአጼ ምኒልክ ሞት
ማህደር

ተደብቆ የቆየው የአጼ ምኒልክ ሞት

Ethioreview newsEthioreview news—December 15, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በፊት በዚህ ሳምንት ታኅሣሥ 3 ቀን 1906 ዓ.ም የተከሰተው የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ሕልፈተ ሕይወት ነው።

መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ ‹‹የሃያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ፤ የዘመን ታሪክ ትዝታዬ ካየሁትና ከሰማሁት 1896- 1922›› በሚለው መጽሐፋቸው እንዳሰፈሩት፤ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጼ ምኒልክ አምስት ዓመት ከአራት ወር በሕመም ላይ ከቆዩ በኋላ ታኅሣሥ 3 ቀን 1906 ዓ.ም በዕለተ አርብ አረፉ፡፡

አቤቶ ኢያሱ በዚህ ሌሊት በአዲስ አበባ ፍልውሐ በመታጠቢያ ቤታቸው አድረው ነበርና የንጉሠ ነገሥቱን ሞት ሲሰሙ ወደ ቤታቸው መጥተው ተቀመጡ።

የንጉሠ ነገሥቱ አጼ ምኒልክ ሞት እንደተሰማ ሕዝብ ይሸበራል ተብሎ ስለተሰጋ የሞታቸው ዜና እንዳይነገር በጥብቅ ተከለከለ። በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ለቅሶ ጀምረው የነበሩትንም ወዲያውኑ አስቆሟቸው።

More stories

ተደብቆ የቆየው የአጼ ምኒልክ ሞት

December 15, 2024

ተስፋዬ ገ/አብ እንደ “ካቡጋ”

January 11, 2025

ደበበ ሰይፉ – የኪነት ፀሐይ

November 27, 2024

ራስ እምሩን በተመለከተ

August 8, 2023

አቤቶ ኢያሱ የንጉሠ ነገሥቱ ሞት እንዳይሰማና እንዳይገለጥ በማለት የሐዘን ምልክት ሳያሳዩ ቀሩ። እንዲያውም በማግስቱ ቅዳሜ ወደ ጃንሜዳ ሄደው በፈረስ ተቀምጠው ከአሽከሮቻቸው ጋር ጉግስ ሲጫወቱ ዋሉ። ይህም ሐዘን እንደሌለ ለማስመሰል የታቀደ ዘዴ ነበር፡፡

የንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ሞት በአቤቶ ኢያሱ ዘመነ መንግሥት ሁሉ ሳይገለጽ ተደብቆ ኖረ። ሆኖም ወሬው መሰማቱና መታወቁ አልቀረም። የምንጃር ገበሬ በጤፍ ውቂያ ጊዜ እንዲህ ብሎ እንደገጠመ በታሪክ ተቀምጧል።

እምዬ ምኒልክ ገንዘብ ስጠኝ ብዬ አላስቸግርህም

አምና ነበር እንጂ ዘንድሮ የለህም

ከዚህ በኋላም አጼ ምኒልክ በሕይወት አሉ እየተባለና እየተወራ እስከ ሰገሌ ዘመቻ ድረስ ሁለት ዓመት ከአሥር ወር ተደበቀ። የንጉሠ መንግሥቱ ሥራም በስማቸው ይካሄድ ነበር።

አጼ ምኒልክ የተወለዱት ነሐሴ 12 ቀን 1836 ዓ.ም ስለሆነ በሞቱበት ጊዜ ዕድሜያቸው ስድሳ ዘጠኝ ዓመት ከአራት ወር ነበር።

የፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ መጽሐፍ ስለ ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የሚከተለውን ይነግረናል።

‹‹…ምኒልክም ቢሆን እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚል አመለካከት አልነበረውም። ሌሎች ግፊቶች ባይታጡም በ1900 የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ያቋቋመበት አንዱ ምክንያት ለመንግሥት ድርጅታዊ መሰረትና ቀጣይነት ለመስጠት ከነበረው ፍላጎት ይመስላል፡፡››

ከምኒልክ ሕልፈተ ሕይወት በፊት ስለነበረው ሁኔታም የታሪክ መጽሐፉ ይህን ይነግረናል። የንጉሠ ነገሥቱ በሞትና ሕይወት መካከል ተንጠልጥሎ መቆየት የኢያሱን የፖለቲካ እድልም እንዲሁ በእንጥልጥል እንዲቀር አደረገው።

በ1905 ዓ.ም አጋማሽ ላይ በኢያሱና በግቢ ዘበኞች መካከል የተፈጠረው ግጭት መንሥኤም ይኸው የኢያሱ ትዕግሥት ማጣት ይመስላል። ከምኒልክ ውጭ ጌታ የማያውቁት ዘበኞች ቀደም ሲል ራስ አባተን ግቢ አናስገባም እንዳሉ ሁሉ፤ አሁንም ኢያሱ ምኒልክን ወደ አንኰበር ለማስወሰድ ሐሳብ አለ ማለትን ሰምተው እኛ ሳንሞት ንጉሣችን ከግቢ አይወጡም ብለው በኢያሱ ላይ በሩን ዘጉበት።

ኢያሱም ግቢውን ከቦ ዘበኞቹ ከውጭ ምንም ስንቅ እንዳያገኙ አደረገ። አምስት ሰዓት የቆየ ተኩስም ተከፍቶ አሥራ ሰባት ያህል ሰዎች ሞቱ።

ይህ ሽኩቻ ቀጥሎ ነው እንግዲህ ከዳግማዊ አጼ ምኒልክ መሞትና ከልጅ እያሱ መተካት በኋላ የሰገሌ ጦርነት የተከሰተው፡፡

አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 6 ቀን 2017 ዓ.ም

archive
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ጥንቃቄን የሚሻው የስኳር ህመም
Brinkmanship (ዲፕሎማሲያዊ ጡዘት): Ethiopia’s Forced Option!
Related posts
  • Related posts
  • More from author
Events

የመደመር መንግሥት አዕማዶች – የመጽሐፍ ዳሰሳ

October 8, 2025
ማህደር

የሦስት ሊቃውንት የአሻራ ቅብብሎሽ

October 5, 2025
ማህደር

“ኦሮሞ ‘ፈጣሪ ጥቁር ነው’ ይላል” የዋቄፈና እምነት

October 4, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2