Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  POLITICS  የሰላም ሚኒስቴር ማብራሪያ – ብሄርተኛነት የሃብት ማሰባሰቢያ መንገድ
POLITICS

የሰላም ሚኒስቴር ማብራሪያ – ብሄርተኛነት የሃብት ማሰባሰቢያ መንገድ

Ethioreview newsEthioreview news—April 29, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ኢትዮጵያ ውስጥ “ሥር የሰደዱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ” ምክንያቶች ለግጭት ተጋላጭነት መነሻ ኾነዋል ሲል የሰላም ሚኒስቴር ገለፀ። “ብሔር ” አንዱ የሀብት መሰብሰቢያ መንገድ ስለሆነ “ለብሔርተኝነት መስፋፋት” መነሻ ሆኗል ሲሉ የሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ የተቋሙን ዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም አቅርበዋል።

የግጭት ተጋላጭነት ምክንያቶችና የሰላም ሚኒስቴር ማብራሪያ 

ኢትዮጵያ ውስጥ “ሥር የሰደዱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ” ምክንያቶች ለግጭት ተጋላጭነት መነሻ ኾነዋል ሲል የሰላም ሚኒስቴር ገለፀ። “ብሔር ” አንዱ የሀብት መሰብሰቢያ መንገድ ስለሆነ “ለብሔርተኝነት መስፋፋት” መነሻ ሆኗል ሲሉ የሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ የተቋሙን ዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲያቀርቡ ገልፀዋል። የሀገሪቱ ዋና ዋና የፀጥታ እና የደኅንነት ተቋማት ተጠሪነታቸው ለሚኒስቴሩ በነበሩበት ወቅት በሕዝብ ዘንድ ስለ ሰላም የተያዘው አመለካከት እንዳለ ነው ያለው ሚኒስቴሩ ተቋሙ አሁን ያለው አደረጃጀት መከለሱ በዚህ ረገድ አንድ ችግር መሆኑ ተጠቅሷል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያለው “የፀጥታ መደፍረስ” ከፍተኛ መሆኑንና ይህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ገጠሙኝ ካላቸው ዋነኛ የሰላም ችግሮች አንዱ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር ገልጿል። 

More stories

ደቡብ ሱዳን ስድስተኛ ሀገር ሆና የናይል ስምምነት ማዕቀፍን አጸደቀች

July 12, 2024

“ትህነግ ጦሩን እስጠግቷል፤ የጦርነት ስጋት አለብን” የጠለምት ወሰንና ማንነት አስመላሽ

June 7, 2025

“የኢትዮጵያን ህልውና የሚበይኑት የተፈጥሮ ሀብቶች…”

September 2, 2024

“ዘመን ትውልድን ይገነባል ፤ ትውልድም ዘመንን ይገነባል”

September 10, 2023

ሚኒስቴሩ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ “የአስተዳደር ወሰን” ግጭቶች፣ ኢ-መደበኛ የተባሉ ታጣቂዎች እንቅስቃሴዎች እና የብሔር መልክ ያላቸው ግጭቶች በዘላቂነት እንዴት ሊፈቱ ይገባል? ሚኒስቴሩስ ምን እየሠራ ነው የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበውለታል። ለዚህ ምላሽ የሰጡት ሚኒስትር ድዔታ ቸሩጌታ ገነነ “ሥሩ የሰደዱ” ያሏቸውን ምክንያቶች ዘርዝረዋል። 

“አንዱ የግጭት ተጋላጭነት ምክንያት ሥር የሰደዱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ምክንያቶች ናቸው። እነዚህ ናቸው ስንል አለመግባባቶች አሉ፣ ድህነት አለ፣ ድህነት ዋናው ምክንያት ነው”። የታጣቂዎችን እንቅስቃሴ “በውይይት እና በሰላማዊ መንገድ” ብቻ የሚፈታ መሆኑን የገለፁት ባለሥልጣኑ ችግሮቹ መዋቅራዊ በመሆናቸው በቀላሉ እና በአጭር ጊዜ ለመፍታት  እንዳልተቻለ ገልፀዋል። 

“የማሕበረሰብ ዓላማ አስፈጽማለሁ ብሎ ይነሳል፣ በመሰረታዊነት ኢኮኖሚያዊ ይሆናል”

ዋና ዋና የሚባሉት የፀጥታ እና የደኅንነት ተቋማት ተጠሪነታቸው በሥሩ ሆነው የተቋቋመው የሰላም ሚኒስቴር ተቋሙ ከተፈጠረ ጀምሮ በኢትዮጵያ “ሰላም ርቋል” የሚል ብርቱ ትችት እየቀረበበት ቆይቷል። ሕልውናው ላይም ጥያቄ ሲነሳበት ነበር። ዛሬ ሰኞ የዘጠኝ ወራት ሥርራውን ለውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲያቀርብ ግን ይህ ወቀሳ “የተሳሳተ አመለካከት” ስለመሆኑ አስታውቋል። ሚኒስቴሩ አደረጃጀቱ ከነበረው ተሻሽሎ የተስተካከለ ቢሆንም አሁንም ስለ ሚኒስቴር የተያዘው አተያይ ግን አንድ መሠረታዊ ችግር እንደሆነባቸው ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ ኢድሪስ ተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ

የሰላም ሚኒስትር ድዔታ ቸሩጌታ ገነነ እንዳሉት በዚህ ሀገር የተፈናቃይ ዜጎች ጉዳይ ከሰብአዊ ጉዳይነት እየወጣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መልክ መላበሱንም አብራርተዋል። 

“ተፈናቃዮችን መመለስ የሚባለው ጉዳይ ሰብአዊ ከሆነው ነገር አንዳንዴ እየወጣ ነው አስቸጋሪ ያደረገው”

የሰላም ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ ኢድሪስ መሠረታዊ የሀገሪቱ የፀጥታ ችግሮችን የሰላም ምኒስቴር ብቻ እንዲፈታ መጠበቅ ተገቢ እንዳልሆነ ተናግረዋል። ትርክቶችን ለበጎ ነገር መጠቀም፣ በወጣቶች ላይ አንድነትን ማስረጽ፣ የሃይማኖት ተቋማት ስለ ሰላም አጥብቀው እንዲሠሩ ማድረግ የሚመሩት ተቋም “ሰላምን ለማስፈን” ጥረት እያደረገባቸው ያሉ እንቅስቃሴዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። DW news


ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡  @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter


POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“የንግድ ጥሰት የፈጸሙ ከ250 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርገዋል”
የግብጽና የጅቡቲ ሴራ – ሻዕቢያ አሰብን እያጸዳና እያሟጠጠ ነው
Related posts
  • Related posts
  • More from author
POLITICS

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

March 28, 2026
POLITICS

አስቸኳይ የአርበኛነት ጥሪ ለኢትዮጵያን

March 4, 2026
POLITICS

ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡ

January 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2