እስራኤል አድብታ የኢራንን ቁልፍ የጦር መሪዎችና ሳይንቲስቶች በቅጽበት በመግደል የጀመረችው ጥቃት ከኢራን አጻፋ እየተሰጠው ዛሬ ደርሷል። ጦርነቱ መጀመሩን ተከትሎ የሚወጡ መረጃዎች ስለ መሳሪያዎቹ አስገራሚነትና አውዳሚነት አስገራሚ መረጃ እያሰሙ ነው። ሁሉም ወገኖች ማውደምና መደምሰሳቸውን እያስታውቁ ነው። ኢራን በመቶዎች፣ እስራኤል በሃያና ሰላሳዎች መላከል ሕይወት መጥፍቱን ይገልጻሉ፣ በቅንብር ከምኪሰራጩት የውድመት ቪዲዮና ምስሎች ውጪ ሁለቱም ወገኖች አምነው በሚለቁት ፊልም ውድመቱ ክፉ ነው፡፡
አሜሪካ ፈራ ተባ ስትል ቆይታ የሌሊት መዶሻ ባለችው መሳሪያዋ የኢራንን ሶስት የኒኩሌር ጣቢያዎች ማውደሟን ካስታወቀች በሁዋላ ነገሮች እየተቀየሩ ነው።
- ሰሜን ኮሪያ ለኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ልታቀርብ ተዘጋጅታለች። [ Iranina media ]
- የኢራን ባለስልጣናት አያቶላ አሊ ካሚኒን ከኢራን ጠቅላይ መሪነት ለማንሳት እያጤኑ እንደሚገኙ ዘ-ጀሩሳሌም ፖስት እና የአሜሪካ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
- የመን በይፋ ጦርነቱን ተቀላቅላለች መርከቦቻችሁን ከክልላቸን አታስጠጉ ብላለች
- የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አገራቸው በኢራን ላይ የፈጸመችውን ጥቃቶች “በሁሉም የኒውክሌር ይዞታዎች” ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ፤ እንዲሁም “ማውደም የሚለው” የሚገልጸው ነው ብለዋል። ሆኖም የተባበሩት መንግሥታት የኒውክሌር ተቆጣጣሪ አካል የደረሰውን ጉዳት በትክክል ማረጋገጥ እንዳልቻለ ገልጿል።
- የኢራን የጦር ጄነራሎች ለአሜሪካ ጥቃት “ቆራጥ ምላሽ” እንደሚሰጥ አስጠነቅቀዋል። የኢራን ጦር ዋና አዛዥ አሚር ሃታሚ የጦር መኮንኖቻቸውን በወታደራዊ ክፍል ሲያነጋግሩዋቸው የሚያሳዩ ቪዲዮ የአገሪቱ ሚዲያዎች አውጥተዋል። አሜሪካ ከዚህ ቀደም በኢራን ላይ በፈጸመቻቸው “ወንጀሎች ቆራጥ ምላሽ ሰጥተኛል እናም የአሁኑም ተመሳሳይ ይሆናል” ብለዋል። የኢራን ጦር ኃይሎች ዋና ኢታማዦር ሹም አብዶልርሃም ሞሳቪ በበኩላቸው አሜሪካ በፈጸመችው ጥቃት በቀጣናው ባሉ ወታደሮቿ ላይ ጦራቸው “ማንኛውንም እርምጃ” ሊወስዱ የሚችሉበትን እድል ከፍታለች ብለዋል። ቢቢሲ
- የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን የአገዛዝ ለውጥን በተመለከተ በሰጡት አስተያየት አሁን ያለው አገዛዝ ኢራንን እንደገና ታላቅ ማድረግ ካልቻለ ለምን የመንግሥት ለውጥ አይመጣም? የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።
- ትራምፕ አገራቸው በኢራን ላይ የፈጸመችውን ጥቃቶች “በሁሉም የኒውክሌር ይዞታዎች” ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ፤ እንዲሁም “ማውደም የሚለው” የሚገልጸው ነው ብለዋል። ሆኖም የተባበሩት መንግሥታት የኒውክሌር ተቆጣጣሪ አካል የደረሰውን ጉዳት በትክክል ማረጋገጥ እንዳልቻለ ገልጿል።
- የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ሞስኮ አቅንተው ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ይገናኛሉ።
- በተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ ላይ የእስራኤል ተወካይ አለም ሁሉ ትራምፕን ሊያመሰግነው ይገባል ሲሉ የኢራኑ ተወካይ በበኩላቸው የአሜሪካን “ጥቃት አውግዘዋል።
- አሜሪካ በኢራን ላይ የፈጸመችውን ጥቃት በማውገዝ በተለያዩ የአለም ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል።
- በኢራን ጥቃት ለመፈጸም ተሰማርተው የነበሩት ቦምብ ተሸካሚዎቹ ቢ-2 ተዋጊ ጄቶች ወደ አሜሪካ ጦር ሰፈር መመለሳቸው ተገልጿል።
- ኢራን ወሳኝ የሆነውን ቁልፍ የነዳጅ መተላለፊያ መስመር እንዳትዘጋ ተጽእኖ ለመፍጠር አሜሪካ ለቻይና ጥሪ አቀረበች
- ትራምፕ የኢራን የኒውክሌር ይዞታዎችን “አውድመናቸዋል” ሲሉ፤ ተመድ ጉዳቱ ግልጽ አይደለም አለ
- አሜሪካ ኢራን ውስጥ ፎርዶን እና ሌሎች የኒውክሌር ተቋማትን በቦምብ ደበደበች
- ፕሬዚደንት ትራምፕ በዋይት ሐውስ በሰጡት መግለጫ ኢራን ሠላም ታውርድ ወይም የወደፊቱ ጥቃት “ከበድ ያለ ይሆናል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል
- ፕሬዝዳንት ትራምፕ በፎርዶ እና ሌሎች ሁለት የኒውክሌር ተቋማት ላይ የደረሰውን ጥቃት “አስደናቂ ወታደራዊ ስኬት” ብለውታል
- የኢራን ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን የፎርዶ የኒውክሌር ተቋም “በጠላት የአየር ጥቃት ደርሶበታል” ሲሉ የዘገቡ ሲሆን የጥቃቱን መጠን ግን ባለስልጣናት አላረጋገጡም
- የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የአሜሪካ ጥቃት “የማያባራ መዘዝ” ያስከተላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል
- እስራኤል እና ኢራን ግጭት “መስፋፋት ማንም ሊቆጣጠረው የማይችል እሳት ሊያቀጣጥል ይችላል” ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አሳሰቡ
- ኢራን በእስራኤል ያልተጠበቀ ጥቃት የተፈጸመባት “ከአሜሪካ ጋር የኒውክሌር አቅምን አስመልክቶ ተስፋ ሰጪ ዲፕሎማሲያዊ ሂደት ላይ በነበረችበት ወቅት” መሆኑን አስታወቀች።

