Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  POLITICS  ኦፌኮ “ቃል ኪዳን” ያለው አንቀጽ 39 ላይ መንግስት ስልታዊ ጥቃት እየፈጸመ ነው ሲል ተቃውሞ አሰማ
POLITICS

ኦፌኮ “ቃል ኪዳን” ያለው አንቀጽ 39 ላይ መንግስት ስልታዊ ጥቃት እየፈጸመ ነው ሲል ተቃውሞ አሰማ

Ethioreview newsEthioreview news—July 21, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ገዢው ፓርቲ ብልጽግና በህገ-መንግስቱ የተረጋገጠውን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ስልታዊ በሆነ መንገድ የሚያንኳስስ አንድ ወጥ ሀገራዊ ትርክትን ማራመድ ሊሽረው እንዳሰበ ጠቅሶ ተቃውሞ አሰማ። የራስን በራስ ዕድል መወሰን እስከ መገንጠል የሚለውን አንቀጽ “ኢትዮጵያን አንድ ላይ የያዘ ቃል ኪዳን ” ሲል አግንኖታል። በተደጋጋሚ በተደረጉ ውይይቶች ይህ ስሜት የፖለቲካ ፓሪ አመራሮች እንጂ የጥቅል የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት እንዳልሆነ በተደጋጋሚ የሚገለጽ ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል።

በተለያዩ ትርክቶች ይህንኑ አንቀጽ የማንኳሰስ ስራ እንደሚሰራ የጠቆመው የኦፌኮ መግለጫ፣ ተግባሩን “ቃል ኪዳን” ያለው አንቀጽ 39 ላይ ጥቃት የመሰንዘር ያህል እንደሆነ ጠቁሟል። አክሎም “የአስርት ዓመታት የህዝባችን የትግል ውጤቶችን ወደ ኋላ መመለስና የሀገሪቱን ህዝቦች ወደ መበታተን መግፋት ነው” ሲል አሳስቧል።

አንቀጽ 39ን አስመልክቶ አሁን በህግ የተሰረዘው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግም አቋም መሆኑ ይታወሳል። ትህነግ ወደ ትግራይ ከፍገፈገ በሁዋላ “የፌደራሊስ ኃይሎ” ሲል ባቋቋመው አዲስ ጥምረት በዋናነት መንግስትን ሲከስ የነበረው ” የህገ መንግስቱ የማዕዘን ድንጋይ የሆነው አንቀጽ 39ን ሰርዞ አገሪቱን ወደ አሃዳዊ መንግስትነት ለመመለስ እየተሰራ ነው” በማለት እንደነበር ይታወሳል።

“በመንታ መንገድ ላይ ያለች ሀገር፥ ለአንድነት፣ ለሰላምና ለአዲስ ዲሞክራሲያዊ ጉዞ የቀረበ ጥሪ” በሚል ርዕስ አዘጋጅቶ ፓርቲው ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ፣ ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና በጸጥታ ችግር ያለችበትን ሁኔታ ግምገማውን አስቀምጧል። ሊደረግ ይገባዋል የተባለውን አሳብም በርዕስ ለይቶ አስታውቋል።

More stories

ደቡብ ሱዳን ስድስተኛ ሀገር ሆና የናይል ስምምነት ማዕቀፍን አጸደቀች

July 12, 2024

“ትህነግ ጦሩን እስጠግቷል፤ የጦርነት ስጋት አለብን” የጠለምት ወሰንና ማንነት አስመላሽ

June 7, 2025

“የኢትዮጵያን ህልውና የሚበይኑት የተፈጥሮ ሀብቶች…”

September 2, 2024

“ዘመን ትውልድን ይገነባል ፤ ትውልድም ዘመንን ይገነባል”

September 10, 2023

ኦፌኮ ባወጣው መግለጫ መንግስትን በጽረ ዴሞክራሲያዊነት ከሶ አገሪቱን ታጣቂዎች ከየአቅጣጫው መሳሪያ እንዲያነሱ ማስቻሉን አመልክቷል። ከሶማሊላንድ ጋር የተደረገውን ስምምነትም ኮንኗል። በትግራይ ያለውን የሰላም መሳሳት አንስቷል። ኦሮሚያና አማራ ክልል የሚደረገውን ጦርነት፣ እንዲሁም በጋዜጠኖች፣ በፖለቲካኞችና በአክቲቪስቶች ላይ ማሳደድ፣ እስርና ግድያ ይፈጸማል ያለው መግለጫው የኤርትራን ጣልቃ ገብነትም ሆነ የትግራይ ኃይሎችና የሻዕቢያን ኢህገመንግስታዊ ግንኙነት አስመክቶ ያለው ነገር የለም።

የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት አቶ በቀለ ገርባ ሰሞኑን “…. ሚዲያን ያለአግባብ ኢ-ሞራላዊ በሆነ መንገድ፤ በገፍ በመጠቀም አድማጭን በማደናገር እና የመጡብህ ፖለቲካ ፍርሃትን በማሰራጨት ፖለቲካዉን በጣም አቆሽሾታል» በማለት ለጀርመን ድምጽ መናገራቸው ይታወሳል። እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ በርካቶች በኢትዮጵያ አክቲቪዝም፣ ጋዜጠኛነትና ፖለቲካ ተቀላቅለው አገሪቱን ወደ ቀውስ እየነዷት እንደሆነ በርካታ ምሁራንና ሕዝብ አደባባይ በምሬት ሲገልጹ መስማት የተለመደ ነው። ኦፊኮ በደፈናው መንግስትን ከመቃወሙ በዘለለ ሙያቸውንና ኃላፊነታቸውን አክብረው የማይሰሩትን አስመልክቶ ምንም አላለም። የመግለጫውን ሙሉ ቃል ከስር ያንብቡ።

“በመንታ መንገድ ላይ ያለች ሀገር፥ ለአንድነት፣ ለሰላምና ለአዲስ ዲሞክራሲያዊ ጉዞ የቀረበ ጥሪ”

የሀገራዊው ቀውስ ማዕከል፣ ማዕከላዊና አምባገነናዊ መንግስትን እንደገና ለመመስረት ታስቦ በህብረ-ቤሄራዊ ፌደራላዊ ሥርዓት ላይ የሚካሄደው ስልታዊ የማዳከም ዘመቻ ነው። ይህ ጥቃት በተለያዩ ስውር ዘዴዎች እየተፈጸመ ነው፤ ከእነዚህም መካከል፦ የክልል መንግስታትን ስልጣን የሚጋፉና በማዕከል የሚቆጣጠሩ “ኮማንድ ፖስቶችን” መትከል፤ የክልሎችን ራስን በራስ የማስተዳደርና ህገ-መንግስታዊ ስልጣን ላይ የሚደረግ የፖሊሲና የህግ ጣልቃ ገብነትና ወረራ፤ እንዲሁም በህገ-መንግስቱ የተረጋገጠውን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የሚያንኳስስ አንድ ወጥ ሀገራዊ ትርክትን ማራመድ ይገኙበታል። ይህ ኢትዮጵያን አንድ ላይ የያዘውን ቃል ኪዳን በቀጥታ ማጥቃት፣ የአስርት ዓመታት የህዝባችን የትግል ውጤቶችን ወደ ኋላ መመለስና የሀገሪቱን ህዝቦች ወደ መበታተን መግፋት ነው።

“በመንታ መንገድ ላይ ያለች ሀገር፥ ለአንድነት፣ ለሰላምና ለአዲስ ዲሞክራሲያዊ ጉዞ የቀረበ ጥሪ”
መግቢያ

ሀገራችን በከባድ ሀገራዊ አደጋ ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት፣ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ጥልቅ ውይይቶችን ካደረገ በኋላ በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ይህንን የመጨረሻ ግምገማ ያቀርባል። በታሪካዊ ዴሞክራሲያዊ መደላድል ተስፋ የተጀመሩት ያለፉት ሰባት ዓመታት፣ ‘የባከነ ተስፋ’ ዜና መዋዕል ሆነው ተጠናቀዋል። ዛሬ ኦሮሚያ እና መላው ኢትዮጵያ አንዱ ሌላውን በሚያባብስ አውዳሚ አዙሪት ውስጥ በወደቁ የፖለቲካ፣ የጸጥታ፣ የኢኮኖሚና የሰብዓዊ ቀውሶች ተወጥረዋል።

ፓርቲያችን ቢሮዎቹ እየተዘጉና አባላቱ የማያባራ ስደት ፤እስራትና ግድያ እየደረሰባቸው የዚህ ዴሞክራሲያዊ ሂደት መጨንገፍ ሰለባ ቢሆንም፣ የኦፌኮ ጽናት ለሰላማዊ ትግል መንገድ ያለንን የማይናወጥ ቁርጠኝነት ማሳያ ነው። ከዚህ የመርህና የጽናት አቋም በመነሳት የሀገራችንን ደዌዎች በመመርመር ወደ ፍትሃዊና የተረጋጋ ነጌያችን ለመጓዝ የሚያስችልን መንገድ እንጠቁማለን።

I. የሀገራዊው ቀውስ ግምገማ

የሃገሪቱ ሌሎች ቀውሶች ሁሉ የሚመነጩበት መሰረታዊው ቀውስ ፖለቲካዊ ነው። የ2010ሩ ተስፋ፣ አንባገነናዊ መንግስት ለመገንባት በታቀደ ፕሮጀክት ተከድቷል። ይህ የሆነው ከፖለቲካዊ ውይይት ይልቅ ወታደራዊ ኃይልን በተደጋጋሚ በመምረጥ ሲሆን፣ ይህም በሶስት ተያያዥ ጥቃቶች የሀገራችንን ማህበራዊ መዋቅር በታትኖታል።

ሀ. የፖለቲካ እና የጸጥታ ውድቀት፡

መንግሥት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታን በዘዴ አፍርሷል። ይህ ጥቃት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ጋዜጠኞችን፤ማህበራዊ አንቂዎችን እና የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎችን ማሰር፣ በግዳጅ መሰወር እና መግደልን ያጠቃልላል። በፓርቲዎች፤ በመገናኛ ብዙኃንና በሲቪል ማህበረሰብ ላይ የወጡ አፋኝ ህጎች፣ ለማሻሻያ ሳይሆን ትችት የሚያቀርቡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ ሚዲያዎችንና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ለመዝጋት እንደ መሳሪያ በመዋል የፖለቲካ ተቃውሞን አዳክመዋል። ዴሞክራሲያዊ ሂደቱ ራሱ በህገ-ወጥ ሕገ-መንግስታዊ ማሻሻያዎችና 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሙሉ በሙሉ በመጭበርበሩ ተዛብቷል።

እነዚህ ድርጊቶች በድምር የፖለቲካ ምህዳሩን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ለበርካታ ተቃዋሚ ኃይሎች ጦርነት ብቸኛ አማራጭ እንዲመስል አድርገዋል። የማይቀረው ውጤትም አሁን ሀገሪቱን እየበላ ያለው አውዳሚ ጦርነት ነው፦ ኦሮሚያ የማያባራ ጦርነት ማዕከል ሆናለች፣ በአማራ ክልልም ከባድ ጦርነት እንደቀጠለ ነው፣ በትግራይም ያለው ስስ ሰላም እየተሸረሸረ ነው።

ይህ የሀገር ውስጥ ጦርነት ቀስቃሽነት በአፍሪካ ቀንድ አለመረጋጋትን በሚያስፋፋ ኃላፊነት የጎደለው የውጭ ፖሊሲ ላይም ይንጸባረቃል። ከሶማሌላንድ ጋር በብቸኝነት የተደረገው የመግባቢያ ሰነድ (MoU) የሶማሊያ ፌደራላዊ መንግሥትን ማግለል ብቻ ሳይሆን፣ የሀገርን ሉዓላዊነት በተመለከተ የታወቁ ዓለም አቀፍ ደንቦችን የጣሰ ከባድ የዲፕሎማሲ ስህተት ነበር። ይህም ተግባር ኢትዮጲያ በአፍሪካ ቀንድ የግጭትና አለመረጋጋት ምንጭ ተደርጋ እንደትታይ አድርጓታል። ይህ የቀይ ባህር መዳረሻን ለማግኘት የሚደረገው ግትር ጥረት፣ እየጨመረ ከመጣው የጦርነት ነጋሪት መጎሰም ጋር ተዳምሮ ከኤርትራ ጋር ያለውን ውጥረት በአደገኛ ሁኔታ አባብሶ የጦርነት ስጋት እንዲያንዣብብ አድርጓል። የሃገራችን የባህር በር የማግኘት ብሔራዊ ጥቅም የሚካድ ባይሆንም፤ ይህን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር እየተኼደበት ያለው አደገኛ መንገድ ለሃገራችን ከፍተኛ መዘዝን እንዳያስከትል መጠንቀቅ ያሻል። በገዛ ድንበሩ ውስጥ ሰላምን ማረጋገጥ ያልቻለው ሥርዓቱ፣ በውጭ አዳዲስ ጠላቶችን በንቃት እየፈበረከ ነው።

ለ. የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ውድቀት፡-

ይህ የግጭት አዙሪት አጠቃላይ የኢኮኖሚ ውድቀትን አስከትሏል። የመንግስት ብልሹ አስተዳደር መሰረታዊ ፍላጎቶችን ችላ በማለት የገፅታ ግንባታ ላይ ፕሮጀክቶች ላይ በማተኮር ይገለጻል። በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መኖሪያና መስሪያ ቤቶች ያለ በቂ ካሳና ያለ ህጋዊ አካሄድ እንዲፈርሱና ዜጎች ጎዳና ላይ እንዲበተኑ አድርጓል። ‘የኢኮኖሚ ሊበራላይዜሽን’ በሚል ስም ሥርዓቱ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ለውጭ ጥቅሞች አሳልፎ የሰጠ ሲሆን፣ ለሚቀጥሉት ትውልዶች ከባድ ሸክም የሚሆን የሀገር ዕዳ አከማችቷል። ይህ ዕዳ ለከፍተኛው የኑሮ ውድነትና ህዝባችን ለሚጋፈጠው የዕለት ተዕለት ችግር ዋነኛ አንቀሳቃሽ ነው። ቀውሱ አሁን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች መሰረታዊ ፍላጎቶችን እንኳን ማሟላት በማይችሉበት ሰማይ የነካ የኑሮ ውድነት ይገለጻል። በተመሳሳይ ጊዜ፣ ወሳኝ የሆኑትን መምህራንንና የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝና ጥቅማጥቅም ማሻሻያ ሳያደርግ የቀረ ሲሆን፣ መንግስት ፍትሃዊና ህጋዊ ጥያቄዎቻቸውን ለመመለስ ፍላጎት እንዳሌለው በተደጋጋሚ አስመስክሯል ። ይህን የሚያባብሰው ደግሞ ሥርዓቱ በግልጽ የሚፈጸም መንግስታዊ ዝርፊያን ተቋማዊ ማድረጉ ነው፦ በተለያዩ ሰበቦች ከሀገራችን ገበሬዎች፣ ነጋዴዎችና ሰራተኞች ያለማቋረጥና በህገ-ወጥ መንገድ ገንዘብ መሰብሰብ የእለት ተግባር ሆኗል።

የጦርነቱና የኢኮኖሚ ውድመቱ ድምር ሸክም በወጣቶቻችን ላይ ከብዷል፤ ይህም በትምህርት እጦት፣ በስራ አጥነትና በተስፋ መቁረጥ የጠፋ ትውልድ ተፈጥሯል። ይህም ወጣቶች ወደ ውጭ ሀገራት አደገኛ ጉዞ እንዲጀምሩ የሚያደርግ ሰፊና አሳዛኝ የስደት ማዕበል አስከትሏል። በሺዎች የሚቆጠሩ በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ ሆነዋል፣ በባህር ላይ ሞተዋል፣ ወይም በሊቢያ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲና የመን በረሃዎች ጠፍተዋል፤ በህይወት የተረፉትም ብዙውን ጊዜ በውጭ ሀገራት ከባድ የኢኮኖሚ ብዝበዛ ይደርስባቸዋል። ይህ አጠቃላይ ጥፋት ሰፊ የማህበራዊ መበስበስን አስከትሏል፣ የማህበረሰብ ትስስርን አፈርስሷል፣ እንዲሁም የሀገራችንን የወደፊት ህልውና የሚያሰጋ የተስፋ መቁረጥ መንፈስ እንዲሰፍን አድርጓል።

ሐ. በህብረ ብሄራዊ ፌደራላዊ ሥርዓት ላይ የሚፈጸም ስልታዊ ጥቃት፡-

የሀገራዊው ቀውስ ማዕከል፣ ማዕከላዊና አምባገነናዊ መንግስትን እንደገና ለመመስረት ታስቦ በህብረ-ቤሄራዊ ፌደራላዊ ሥርዓት ላይ የሚካሄደው ስልታዊ የማዳከም ዘመቻ ነው። ይህ ጥቃት በተለያዩ ስውር ዘዴዎች እየተፈጸመ ነው፤ ከእነዚህም መካከል፦ የክልል መንግስታትን ስልጣን የሚጋፉና በማዕከል የሚቆጣጠሩ “ኮማንድ ፖስቶችን” መትከል፤ የክልሎችን ራስን በራስ የማስተዳደርና ህገ-መንግስታዊ ስልጣን ላይ የሚደረግ የፖሊሲና የህግ ጣልቃ ገብነትና ወረራ፤ እንዲሁም በህገ-መንግስቱ የተረጋገጠውን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የሚያንኳስስ አንድ ወጥ ሀገራዊ ትርክትን ማራመድ ይገኙበታል። ይህ ኢትዮጵያን አንድ ላይ የያዘውን ቃል ኪዳን በቀጥታ ማጥቃት፣ የአስርት ዓመታት የህዝባችን የትግል ውጤቶችን ወደ ኋላ መመለስና የሀገሪቱን ህዝቦች ወደ መበታተን መግፋት ነው።

ከኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ


POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
Ethiopia Poised to Become Africa’s Leading Pharmaceutical Export Hub with Urgent Strategic Actions
የኦሮሞ ፖለቲከኞች ከልደቱ “አብሮነት” አፈነገጡ? ባይተዋሩ ጃዋርና ልደቱ በእልቅና ጉዳይ አልተግባቡም
Related posts
  • Related posts
  • More from author
POLITICS

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

March 28, 2026
POLITICS

አስቸኳይ የአርበኛነት ጥሪ ለኢትዮጵያን

March 4, 2026
POLITICS

ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡ

January 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2