Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  OPINION  የአቶ ኦሉማ “የዝቅጠት ቁልቁለት፣ የፖለቲካዊ መበስበስ አደጋ በኢትዮጵያ!” ስጋት ላይ እኔ ላክልበት
OPINION

የአቶ ኦሉማ “የዝቅጠት ቁልቁለት፣ የፖለቲካዊ መበስበስ አደጋ በኢትዮጵያ!” ስጋት ላይ እኔ ላክልበት

Ethioreview newsEthioreview news—August 14, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

“የዝቅጠት ቁልቁለት፣ የፖለቲካዊ መበስበስ አደጋ በኢትዮጵያ!” በሚል ገዢ አሳብ አቶ Oluma’s በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ያጋሩትን ስጋታቸውን ሙሉ በሙሉ እጋራለሁ። ያለ ይሉንታ አሳቡን ማንሳታቸውን አደንቃለሁ። እሳቸው የጠቀሱት የ”ባለ ጊዜነት” እሳቤና የ”ባለ ጊዜዎች አጫፋሪዎች” አገሪቱ ላይ እያደረሱ ያለው ጥፋት፣ ቀውስ፣ እንዲሁም አደጋ ሙሉ ስዕል እንዲኖረን ቢያደርጉ ስል ተመኝቻለሁ።

እንደ ዛሬው ሚዲያው ስላልፈላ አደባባይ አልወጣም እንጂ የግል እስር ቤትና ፍርድ ቤት ያላቸው ወረበላ ባለስልጣናትና ጭፍሮቻቸው ነበሩ። በዚሁ ባደራጁት መዋቅር የራሳቸው ወታደር ያደራጁ ባለጊዜዎች፣ የባለጊዜዎቹ አሸርጋጆች፣ ባለሃብቶችና ምስለኔዎች፣ ሽቅብ የሚተፉ ባለጌዎች ወዘተ አሁን ድረስ ራሳቸውን ያልሸሸጉ ማጅራት መቺዎች ነበሩ። አሁን ድረስ ካባ ቀይረው ይህንኑ ልምዳቸውን እያስፋፉ ነው።

አዲስ አበባን እንደቅርጫ እየበለቱ ሲቸበችቡ የነበሩ፣ በዘርና ደም ግንኙነት የማይችሉት የኃላፊነት ወንበር ላይ እየተሰቀሉ በዝርፊያ የናጠጡ፣ ያስናጠጡ፣ አደባባይ ላይ ሕዝብ የሚያውቃቸውን ግንባታዎች የቆለሉ ቁጥራቸው እልፍ ነው። እነዚህ ሌቦች ትንሽ ደፍሮ የሚነካቸው ካለ በገሃድ ሲገርፉ፣ ሲያስገርፉና ሲያስወግዱ ነበር። ይህ የተመዘገበ ቀን የሚቆጠርለት እውነት ነው። ቤተ መንግስቱ ሲታረስ የተገኘው ጉድም ብዙ ምስክርነት ሰጥቷል እሱም ቀኑ ሲደርስ ይፋ መሆኑ አይቀርም።

የፈለጉትን ሰው እያሰሩ በድርድር፣ በደላላ ገንዘብ የሚቀበሉ፣ አግተው የሚደራደሩ፣ ሲያሻቸው የሚሰውሩ ነበሩ። አሁን ድረስ ይህ መዋቅር ስለመክሰሙ እርግጠኛ መሆን አይቻልም። እንደውም ከላይ እንደተባለው እንደ ዛሬው ሚዲያ ባለመኖሩ በወቅቱ አልተገለጠም እንጂ አሁን አደባባይ የወጣው ጉድ የዚያ ፍሬ ስለመሆኑ በርካታ ምልክቶችና ማስረጃዎች አሉ።

More stories

“በነዉጥና በኃይል የበለፀገ ሀገር የለም”

May 2, 2023

ወያኔያዊ አማራነትን አማራ “አማራ ነኝ”

December 6, 2022

ሰውን “ሰው” የሚያደርገው ምንድነው? ከእኛ ይልቅ የጥንቶቹ ዘመናዊ ነበሩ

November 1, 2024

ወግ አጥባቂው የኦክላሆማ ሴናትር ማ’ናቸው?

October 6, 2022

በርካቶቹ ወንጀሎች ሲፈጸሙና በቅጽበት ለሚዲያ ፍጆታ ሲውሉ ማየትና መስማት ለምን ተለመደ? በሚል የሚጠይቁ በመገረም የሚገልጹት የድጊቱን የማህበራዊ ሚዲያ ስርጭት ነው። ግፉ፣ ወንጀሉ ወይም ጥቃቱ በተፈጸሙ በቅጽበት በማህበራዊ ሚዲያ የሚቀርቡት ፍጥነት እነዚህ ወንጀሎች በቅብብሎሽ በደቂቃዎች ውስጥ እንደ ሸቀጥ የሚሰራጩበት ትስስር አስገራሚ ነው


⦁ የሚያሰራጩት ዓላማው የገባቸውም ያልገባቸውም ናቸው
⦁ ዓላማው የገባቸው ብሶት ማዋለጃ እርዕስ በማከል ሕዝብ “ምን ጉድ መጣ” በሚል በምሬት እንዲያለቅስ ይኮረኩሩታል። ምን ፈረደብን ብሎ ምሬት እዲያረግዝ ያደርጉታል
⦁ ድራማው የገባቸው ደግሞ በሚችሉት ሁሉ ሊከላከሉ ይታገላሉ። እነዚህ ወገኖች የስድብና የማስፈራሪያ እንዲሁም የፍረጃ መዓት እንዲወርባቸው ይደረጋል። ለማሸማቀቅ የተደራጀ ዘመቻ ይከፈትባቸዋል።
⦁ አንዳንዶቹ የታቀዱ ወንጀሎች ትርክት እየተሰራላቸው ለሕዝብ ይቀርቡ እንደነበር የድራማው ተዋናዮች እየነገሩን ነው።
⦁ “ሰነድ ተገኘ” የሚባለውን ጨምሮ ዜናዎች፣ ሪፖርቶች፣ ቃለ ምልልሶች እየተፈበረኩ እንደሚወጡ ተጋልጧል።

በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ለውጡን ተከትሎ ገሃድ የወጡ በገፊና ጎታች፣ በስልትና በዕቅድ፣ በዓላማና በግብ ወዘተ መፈጸም የጀመሩት አስከፊ ወንጀሎች፣ ግፎች፣ ግድያዎች፣ መፈናቀሎች፣ ዝርፊያዎች፣ እገታዎች፣ የኢኮኖሚ ደባዎች፣ ሌብነት፣ ዓይን ያወጣ ነጥቂያ፣ ጠብመንጃ በመያዝ በየስርቻው የተፈለፈሉት የጎጥ አለቆች ወዘተ እጅግ አደገኛ እና አቶ ኦሉማ እንዳሉት የፖለቲካ መበስበስ ምልክቶች ናቸው። ያስፈራሉ። እዚህ ላይ ጥያቄ የለም።

እሳቸው እንዳሉት የሚሰሙት ክፉ ዜናዎች ሁሉ የ”ዝቅተት ቁልቁለት” ናቸው። እሳቸው በግርድፉ ያስቀመጡት ጥልቅ ትንተናና ምርመራ የሚያሻቸው ጉዳዮች መንግስት የተወቀሰበትን ያህል በአገሪቱ ያሉትን ሚዲያዎችን ከተጠያቂነት አያድናቸውም። ይህ ችግር በአገሪቱ የሚፈሩ ሚዲያዎችና የሚዲያ ሰዎች ያለመኖር ችግር ሲሆን በሌላ ጎኑ አገሪቱን ወደ ቁልቁል እየመሩ ያሉት ሌቦች የራሳቸው ሚዲያ ባለቤት መሆናቸውንም መዘንጋት አይገባም።

በ97 ምርጫ ወቅት ተቃዋሚዎች የፓርቲያቸው ሳይሆን የግላቸው ሚዲያ ነበራቸው። ይህ ራሳቸውን የሚከላከሉበትና የማይፈልጉትን የሚበሉበት ሚዲያቸው ያደረሰው ጉዳት “በሱናሚ” ተሰይሞ የመለስን “ማዕበል” ጭጭ ያደረገውንና ሕዝብ የተጋደለበትን ምርጫ በዜሮ እንዲጣፋ አድርጎታል። ንጹሃን በከንቱ እንዲሞቱ አስተዋጾ አድርጓል። ይህን ክፉ ልምምድ ሲያጋፍሩ የነበሩት “ጋዜጠኛ” ተብዬዎች ናቸው ዛሬ ድፍረስ ሲያሻቸው እየበሩ፣ ለካሽ ለቀማው እንዲመች በግል ሆነው አሁን ድረስ የሙጥኝ ብለው በባንዳነትና በብሄር ስም ተወሽቀው አገር እየናጡ፣ ፖለቲካውን እያገሸቡ ያሉት። አቶ ኦሉማ ያጋሩት ስጋት ይህን ኡደት ቢያዩት ብዬ እንደመኝ አድርጎኛል።

ዛሬ በዓይነትና በስፋት ደርጅቶ ሌቦችን የሚከላከሉ ሰፋፊ ሚዲያዎች፣ ሃያ አራት ሰዓት ከማህበራዊ ጭፍሮቻቸው ጋር ሆነው የሚረጩት መርዝ መነሻም የቀደመው ልምምድ ነው። በሪፎርም የተጀመረውና ሁሉንም ያግበሰበሰው ለውጥ ቢሰክን ከላይ የተዘረዘሩትን ወንጀለኞች በሽግግር ፍትህ ስለሚቀረጥፍ በየአካባቢ ታጣቂ አደራጁብን። ብሄርንና ብሶትን ተንተርሰው፣ በብሶትና ምሬት እያፋፉት እዚህ ያደረሱት ሌቦች የፖለቲካ ድርድር፣ ስምምነት፣ ውይይት ወዘተ እንዳይካሄድ በሚቀልቡትና በሚልኳቸው ሚዲያዎች አማካይነት የማክሸፊያ ፕሮፓጋንዳ እያሰሩ ዛሬ ላይ ደርሰዋል። የሻዕቢያና ግብጽ ባሬያዎቹን ጨምሮ።

ለውጡ ያግበሰበሳቸው እነዚህ ወገኖች በደም ቆጠራ፣ በሃይማኖት፣ በሰፈር ልጅነት በመቧደን አንድ እግራቸውን መንግስት ውስጥ ካስቀመጡ “ጥቁር ለባሾች” ጋር አንድ ላይ ሆነው አገሪቷን እየናጡ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም።

መንግስት አብረውት የመጡትን ሌቦች አስቀድሞ እንዳያራግፍ ቀድመው ጦርነት፣ ሁከት፣ ሃሰተኛ ትርክት፣ አድማና የኢኮኖሚ አሻጥር በመጎንጎን ተብትበው የያዙት ወንጀለኞች የጀመሩት አደጋ እያደር ተባብሶ ወደ ፖለቲካዊ መበስበስ ቢሸጋገር አይገርምም። ለውጡን አብረው የጀመሩ መራገፋቸው፣ አንዳንዶቹ ክልል ማፍረሳቸው፣ የተቀሩትም የብሄር ነጻ አውጪ ታጋይ ሆነው ካስወገዱት አገዛዝ ሰፈር ተመልሰው ለማኝና ተላላኪ ሆነው ታይተዋል። የግርድና ሱሳቸው አለቅ ብሏቸው የቀድሞ ሰፈር ሄደው እየተንደባለሉ ነው። መንግስት ውስጥ ያላቸውን ሴል እያንቀሳቀሱ ሕዝብ መከራ እይሳዩ ነው። ሴሉ የዋዛ ባለመሆኑ ዋጋ እያስከፈለን ነው።

አቶ ኦሉማ ያነሷቸው ነጥቦች “ሳይቃጠል በቅጠል” መሆኑ ትክክል ነው። በነካ እጃቸው ሚዲያውንና የዛሬውን መዳረሻ መነሻ ቢዳስሱ ጥቆማቸው ሙሉ በሆነ ነበር። ከዚያም በላይ የሚሰጠውን ሳያስተውል፣ ሳይመረምር እንዳለ የሚውጠው ትውልድ ሆን ተብሎ ጠያቂ እንዳይሆን ተደርጎ በብሄር ማጥንት ታጥኖ ማደጉን ቢጠቁሙ አስተያየታቸው ለውይይት ሙሉ ይሆን ነበር የሚል ዕምነት አለኝ። ከዚህም በተጨማሪ “ራሳቸውን በመጨረሻ ይበላሉ” ሲሉ የገለጿቸው ባለስልጣናት ጠያቂና ተመራማሪ በማያደርገው የ”ከሸፈ” የትምህርት ሂደት ታጥነው እዚህ የደረሱ መሆኑን አብረው ቢጠቁሙ ይበልጥ አስተያይታቸው ምሉዕ በሆነ ነበር። ለሁሉም ከማክበርና አድናቆት ጋር ጽሁፋቸውን አያይዤዋለሁ።

ሰናይት መድህኔ አዳማ 01 ነዋሪ

የዝቅጠት ቁልቁለት፡ የፖለቲካዊ መበስበስ አደጋ በኢትዮጵያ! Oluma’s Views’s post


ቀጣዩን ሀተታ ለመፃፍ ያነሳሳኝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንዳንድ ጋጠ-ወጥ ቆሻሻ ግለሰቦች እና ለእነዚህ አፀያፊ ግለሰቦች ስልጣን እና ሃላፊነትታቸውን ተጠቅመው ከለላ የሚሰጡ እብሪተኛ የመንግስት ተሿሚዎች የፈጠሩት ቅሬታ እና ተስፋ መቁረጥ ነው። ይህ ግለሰቦችን ከህግ እና ከጤነኛ ፖለቲካዊ እሴቶች በላይ እንዲሆኑ ይፋዊ ባልሆነ መንገድ (tacitly) የፈቀደው ሁኔታም የሀገራችንን ወደ ፖለቲካዊ መበስበስ (political decay) የመግባት አደጋ አመላካች ሆኖ ስለታየኝም ነው።

Samuel P. Huntington “የፖለቲካዊ መበስበስ” መንስኤ እና መገለጫ ካላቸው ውስጥ በተለይ ሶስቱ ለዚህ ፅሁፍ አላማ ጠቃሚ ናቸው። እነሱም (1) የተቋማዊነት መሸርሸር (declining institutionalization)፣ (2) የሀገራዊ አቅም መዳከም (weakened state capacity)፣ እና (3) ፖለቲካዊ መካረር እና ግጭት (political polarization and conflict) ናቸው።

የመጀመሪያው (የተቋማዊነት መሸርሸር) ግለሰቦች እና ቡድኖች ተቋማዊ አሰራር እና ዲሲፕሊንን በመጣስ በማን አለብኝነት፣ በዘፈቀደ እና በተበለሻሸ ሁኔታ በመስራታቸው በህዝብ ዘንድ የሚፈጠረውን ሀገራዊ የአመኔታ እጦት አደጋ ያመለክታል።

ሁለተኛው (የሀገራዊ አቅም መዳከም) ከመንግስት የሚጠበቁ ስርዓት ማኅበር፣ ህግ ማስከበር እና መንግስታዊ አገልግሎቶችን በፍትሃዊነት እና በህግ አግባብ አለማቅረብ የሚፈጥረውን የቅቡልነት ቀውስ እና ህዝባዊ ተስፋ መቁረጥ ይመለከታል።

ሶስተኛው (ፖለቲካዊ መካረር እና ግጭት) ፖለቲካዊ ልዩነቶችን በማጥበብ ሀገራዊ ችግርን በመፍታት ፋንታ ሆን ብሎ እና ለግለሰባዊ እና ቡድናዊ ጥቅም ሲባል የተካረሩ እና ግጭት ቀስቃሽ ሁኔታዎች እንዲኖሩ አስቻይ ሁኔታ መፍጠር ነው።

ከላይ በተገለፀው የሀሳብ ማዕቀፍ (framework) ውስጥ ሆነን በሀገራችን ባለፉት ጥቂት አመታት እየተለመዱ የመጡ ጋጠ-ወጥነቶችን እና የተጠያቂነት (accountability) አለመኖር ካየን፤ ሀገራችን የተጋረጠባትን የፖለቲካዊ መበስበስ አደጋ መረዳት አይከብድም። ለዛሬ ትኩረቴን በዋናነት የማደርገውም በመንግስት ደጋፊነት በተኮለኮሉ፤ “እኔ የእከሌ ብሄር” እያሉ የግል ጥቅማቸውን በሚያሳድዱ “ተረኛ” ኮልኮሌዎች ላይ ነው። ጥቂት ምሳሌዎችን ልጥቀስ፦

የመንግስት ኃላፊነት የተሰጣቸውን ግለሰቦች እንደ ከለላ በመጠቀም በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ከኮንትራባንድ እስከ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ማጭበርበር በመሳተፍ ሀገሪቱን ህግ እና ተቋም አልባ ያስመሰሉ ድርጊቶች [ምሳሌ፦ በቅርቡ በንግድ ባንክ ላይ በመንግስት ሀላፊነት ላይ ባሉ እና በሌሉ ግለሰቦች ጥምረት የተፈፀመው የሰባት ቢሊየን ብር ምዝበራ]፣

ለሀገራቸው ሰላም እና ደህንነት በየዕለቱ መስዋዕትነት እየከፈሉ ላሉት ክቡር የመካከያ ሠራዊታችን እና የፖሊስ አባላት ብቻ የተፈቀዱ የደንብ ልብሶችን ለብሶ/አልብሶ ርካሽ እና ከፋፋይ (የብሄር/የሃይማኖት) ፖለቲካ መሸቀጥ፣ ዝርፊያ መፈፀም፣ ግለሰቦችን ማስፈራራት፣ በሶሻል ሚዲያ ላይ ብሄር እና ሃይማኖትን እያጣቀሱ የጥላቻ ንግግርን ማሰራጨት፣ በህዝባዊ ስፍራዎች አምባጓሮ መፍጠር፣ መንግስታዊ ሀላፊነት ላልተሰጣቸው ግለሰቦች እጀባ ማድረግ፣…ወዘተ፣

በፍርድ ቤት ትዕዛዝ “ተይዘው እንዲቀርቡ” የተባሉ ተጠርጣሪዎችን እና ምስክሮችን ይዞ በማቅረብ ፋንታ የመንግስት ደጋፊ ስለሆኑ ብቻ ወይም የመንግስት ኃላፊነት በተሰጣቸው ግለሰቦች ከለላ ስለሚደረግላቸው ብቻ የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ መጣስና እና ማንኳሰስ፤ በዚህም ዜጎች በሀገራዊ በተቋማት ላይ ያላቸውን የመነመነ ዕምነት ጭራሹኑ ማጥፋት።

በዜጎች/በብሄረሰቦች/በሃይማኖት ተቋማት ላይ በአደባባይ የግድያ ዛቻ፣ የጥላቻ ንግግሮችን እና ጥቃቶችን የሚፈፅሙ ጋጠ-ወጦችን በህግ አግባብ ይዞ እና መርምሮ ለፍርድ አለማቅረብ…ወዘተ።

ተደጋጋሚ የእገታ እና የግድያ ወንጀል በተፈፀመባቸው አካባቢዎች ተቋማዊ የመከላከል እና ዕርምጃ የመውሰድ ስራዎችን በመስራት ችግሩን ለዘለቄታው በመቅረፍ ፋንታ ለችግሮቹ “የጦስ ዶሮ” በመፈለግ ላይ የሀገር ሀብት እና ጊዜ ማባከን።



እነዚህ ከላይ የዘረዘርኳቸው የፖለቲካዊ መበስበሱ ማሳያ “tip of the iceberg” ሲሆኑ፤ አንዳንዱ ድርጊት ከዚህ በፊት በነበሩ አገዛዛዞች ስር ታይቶ የማይታወቅ የነውር ነውር ነው! ይህ ሁኔታ አሁን በያዘው መስመር እና ፍጥነት እንዲቀጥል ከተፈቀደም፤ ዛሬ ምናቸውም ያልተነካ እንደውም የሚጠቅማቸው የመሰላቸውን ግለሰቦች እና ባለስልጣናት ሳይቀር ውድ ዋጋ የሚያስከፍል ሀገራዊ ውርደትና ቀውስ ነው የሚፈጠረው። ይህን ሁኔታ ድምፃቸውን ጮክ አድርገው መቃውምም ሆነ በቻሉት መጠን መታገል ያለባቸውም በዋናነት የመንግስት ተቃዋሚዎች ሳይሆኑ ራሱ መንግስት እና ደጋፊዎቹ ናቸው! ሲመቸው እነሱኑ ራሳቸውን ቀርጥፎ የሚበላ አውሬ በቤታቸው እያደለቡ ነውና።
ልብ በሉ! ባለፉት ጥቂት ዓመታት መንግስትን በመቃወም እና በመደገፍ ስም በሀገራችን ብዙ ነውሮች እና ግፎች almost normalized ሆነዋል። አንዳንዶቹ ከመደጋገማቸው የተነሳ መፈፀማቸውን ስንሰማ መደንገጥ ትተናል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት እያየናቸው ያለውን የፖለቲካ መበስበሶች እና መበሳበሶችንም ቸል ብለን ካለፍናቸው፤ እንዲሁ ለምደናቸው ሀገራችንን እንደ ሔይቲ በወሮበሎች ልንነጠቅ እንችላለን። የተያያዝነው የዝቅጠት ቁልቁለት አጓጉል ሳያደርገን በፊት እንደ ህብረተሰብም እንደ መንግስትም ህጋዊ እርምጃ ይወሰድ ዘንድ አበክረን መወትወት አለብን!
“ሳይቃጠል፤ በቅጠል” ❗️

OPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ሻኪሶ አስተዳደሩ “ሲዖል አደረኳት” ያላት ከተማ፤ ” ኑ ወደ ለቅሶ ቤት እንሂድ” ነዋሪዎች
The time for just and fair utilization of the Nile is now – NaMA
Related posts
  • Related posts
  • More from author
OPINION

እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ…

April 8, 2026
OPINION

ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት!

April 8, 2026
OPINION

ሙስጠፌ ተረኛው ባለስልጣን – የሃሰት ትርክ ዘመቻ በደቦ

March 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2