Skip to content
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ሃምዳን ደጋሎ “ኤርትራን እንበቀላለን” ሲሉ አስጠነቀቁ፤ የትህነግ አርሚ መጨረሻ አዲስ አበባ? 

    June 5, 20250

    በአድርቃይ የትግራይ ሃይሎች ጦርነት ከፍተው ሰዎች ገደሉ፣ ከ500 ባላይ እንስሳት ዘረፉ፤ ቤት አቃጠሉ – ቢቢሲ

    June 7, 20240

    የኢትዮጵያን መጻዒ ዕድል የሚወስኑ “ሁለቱ የውሃ አካላት”

    March 3, 20240

    በሼክ መሐመድ ክስ በስጦታ የተሰጠ ሃብትን አስመልክቶ ለጊዜው የቀረበ ክስ የለም፤ “አብነት የተፈረደባቸው የወሰዱትን የከሳሽ የአክሲዮን ትርፍ እንዲመለሱ ነው”

    October 27, 20240
    Prev Next Showing 1 Of 1866
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    “ልጆቻችን የት ናቸው?” የትህነግ አዲሱ ፈተና “ግፋ በለው” ሲሉ የነበሩ ሚዲያዎች የከበሩበት፣ የድሃ ልጆች ያለቁበት…

    April 21, 20230

    «የሳይበር ዘመቻው ማጠንጠኛ ‘የትግራይ ዘር ማጥፋት’ የሚል የሐሰት ትርክት ነው» ጌት ፋክት

    August 23, 20220

    የትህነግ ታጣቂዎች ከምሽግ እየወጡ ነው፤ ኤርትራና ኢትዮጵያ ተስማምተዋል

    November 29, 20220

    ከህገወጥ ተቋማትና ነጋዴዎች ከ42 ቢሊዮን በላይ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ተደረገ

    April 29, 20250

    የፀጥታ ስጋት ዝርፊያና ሌብነት በትግራይ “ከጦርነቱ በላይ የከበደን ዘረፋ ሆኗል”

    June 4, 20220
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  ማህደር  እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ (ከ1915-2015 ዓ.ም)
ማህደር

እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ (ከ1915-2015 ዓ.ም)

Ethioreview newsEthioreview news—November 24, 20230
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በሰርፀ ፍሬስብሃት

በሀገራችን ሙዚቃ ውስጥ ያለው የሴት ሙዚቀኞች ተሳትፎ፤ ከድምጻዊነት ተሻግሮ፣  በሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋችነት እና በሙዚቃ አቀናባሪነት እንዲያም ሲል፣ በሙዚቃ ቀማሪነት ደረጃ፣ እስከ ዛሬ ለማየት ባልታደልንበት ኹኔታ፤ እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ ግን፤ የመጀመሪያ ቅድምና ይዘው፣ በዚህ በክላሲካል ሙዚቃ ዘርፍ በብቸኛ የሙዚቃ ቀማሪነት እና ፒያኒስትነት ጉልህ የታሪክ ቦታ ይዘዋል።

እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ (ከምንኩስናቸው በፊት ይጠሩበት በነበረው ስማቸው የውብዳር ገብሩ) ታኅሣሥ 4 ቀን 1915 ዓ.ም. አዲስ አበባ ነበር የተወለዱት። ገና የስድስት ዓመት ሕጻን ሳሉ ከታላቅ እኅታቸው ከሥንዱ ገብሩ ጋር ወደ ስዊትዘርላንድ ሔደው “ሞንት ሚራል” በተባለ አካዳሚ ትምህርት ይጀምራሉ። በትምህርት ቤቱ ውስጥ ከቀለም ትምህርቱ በተጓዳኝ ቫየሊን እና ፒያኖ አጥንተዋል።

ወንድማቸው ኮ/ል ዳዊት ገብሩ “ከንቲባ ገብሩ የኢትዮጵያ ባለውለታ” ባሉት መጽሐፋቸው ላይ፤ የእማሆይን የልጅነት ትዝታ ከራሳቸው ከእማሆይ ማስታወሻ ወስደው እንዲህ ሲሉ አስፍረውታል። “በዚያው በሰባት እና በስምንት ዓመት ዕድሜዬ አካባቢ ከሥነ ፍጥረት ጋር ወዳጅነት ነበረኝ። አበቦች ውብ ልዕልቶች፣ ዛፎች… እንደ ዘበኞቻቸው፣ ነፋስ… ወጣት መልዕክተኛ፣ ፀሐይ…ደግሞ የዓለም ኹሉ ንግሥት ኾነው ይታዩኝ ነበር። ያን ጊዜ በአዳሪ ትምህርት ቤቱ ውስጥ በኔ ዕድሜ ልጅ ስላልነበረ አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ ብቸኝነት የሕጻንነት ጓደኛዬ ኾኖ አብሮኝ አደገ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አንድ የኀዘን ስሜት፣ የመንፈስ ዕረፍት ዕጦት አደረብኝ። ሙዚቃ እወድ ነበርና ስሰማው የኀዘን ስሜት ያመጣብኝ ነበር። ለገና ሥጦታ ለገና አባት ደብዳቤ ጽፌ፤ ቫየሊን ጠይቄ ሲሰጠኝ ወዲያው አስተማሪ ተመድቦልኝ መማር ጀመርኩ። የአስተዳዳሪው ዘመድ የኾነች ልጅ ፒያኖ ስትጫወት እየተመለከትኩ እኔም እየተፍጨረጨርኩ መምታት እንደቻልኩ የመጀመሪያ ሙዚቃዬን ጀመርኩ። ስሙን ሲጠይቁኝ The storm ነው አልኳቸው። “ማዕበል” ለማለት። ቫየሊኑን ተወት አድርጌ ወደ ፒያኖ በማድላት ብዙውን ጊዜ ፒያኖን ነበር የማጠናና የምጫወተው።” ይላሉ እማሆይ በማስታወሻቸው።

More stories

ደበበ ሰይፉ – የኪነት ፀሐይ

November 27, 2024

ጊዜ መስታወቱ!! ተስፋዬ ገብረአብ ማነው?

January 1, 2024

ጋዜጠኛና ደራሲ ዜናነህ መኮንን አረፈ፣ እንዲህ ሲታወስ

November 11, 2024

የፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ አጭር  የህይወት ታሪክ

August 30, 2024

የውብዳር ገብሩ 11 ዓመት ሲኾናቸው፣ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ። በዚህ ጊዜ ጣሊያን ኢትዮጵያን ወራ ነበር። ከንቲባ ገብሩም መላ ቤተሰባቸውን ይዘው ወደ ጎሬ ለመሠደድ ተገደዱ። የእኅቶቻቸው እና የእርሳቸው ትምህርት ተቋርጦ ከደስታ ገብሩ እና ከገነት ገብሩ ጋር በስደት ቆይተዋል። እንደ ወንድማቸው እንደ ዳዊት ገብሩ ገለጻ፤ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በእስር ወደ ጣሊያን ተወስደው ነበር። እዚያም በእስር ላይ እንዳሉ ወንድሞቻቸው በጥይት ተደብድበው ስለተገደሉ፤ “ይህ ሁሉ የባሰውን የመንፈስ ጸጥታዬን እያጠፋው ይሔድ ነበር” እንዳሉ ጽፈውላቸዋል።

የሙዚቃ ፍቅራቸው እጅግ ጠሊቅ እንደነበር በግል ማስታወሻቸው በርካታ ቦታዎች ላይ ተጠቅሷል። እማሆይ ጽጌ ማርያም የጽሕፈት መኪና መምታት ተምረው ስለነበረ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ለጥቂት ጊዜ በጸሐፊነት ሠርተዋል። ሙዚቃን በከፍተኛ ደረጃ ለመማር ቁርጥ ውሳኔ ላይ የደረሱት ከዚህ ጊዜ በኋላ ነበር። ይህን ውሳኔያቸውን በማስታወሻቸው እንዲህ ሲሉ አስፍረውታል። “እንደገና አባባን አስቸግሬ፤ ጃንሆይን እንዲለምኑልኝ አስደርጌ ወደ ውጪ ሀገር ሔጄ የሙዚቃ ትምህርቴን እንድቀጥል ተፈቅዶልኝ ወደ ካይሮ ሔድኩኝ። ትካዜ እንደ ጓደኛ አይለየኝም ነበር። ብዙ የፍቅር መጻሕፍትን ስለማነብ ስለ ሰው ልጅ ጥሩ አስተሳሰብ አልነበረኝም። ሰው አታላይ ነው፣ ውሽታም ነው በማለት ሰውን እምብዛም አላምንም ነበር።” ይላሉ እማሆይ።

ለከፍተኛ የሙዚቃ ትምህርት ወደ ግብጽ ሔደው “ቬሉኑስ ኮንሰርቫቶሪ ኦፍ ሉቺኒያ” በተባለው የሙዚቃ ትምህርት ቤት አሌክሳንደር ኮንትሮቪች በተባለ ፖላንዳዊ የሙዚቃ መምህር ሥር ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። አሌክሳንደር ኮንትሮቪች ኋላ ላይ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ፤ በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ትዕዛዝ የክብር ዘበኛ ሙዚቃን አደራጅቶ፤ በ1948 ዓ.ም. የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኦርኬስትራ ሙዚቀኞች በመምራት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የነበረው የሙዚቃ ባለሙያ ነበር። እማሆይ ከትምህርታቸው በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው የሙዚቃ ቅማሬዎቻቸውን ማዘጋጀት ጀመሩ። “በዚህ ጊዜ ውስጥ” ይላሉ ወንድማቸው ኮ/ል ዳዊት ገብሩ። “በዚህ ጊዜ ውስጥ ከዕለታት አንድ ቀን የንጉሣዊ በተሰብ የኾኑ አንድ ሰው ለኹለት ዓመት ትምህርት ወደ እንግሊዝ እንድትሔድ የቅድሞሽ ቢከፍሉላትም፣ የይለፍ ወረቀቱን ኹሉ ይዛ ሳለ፣ ‘ከበላይ የመጨረሻ ፈቃድ አልተገኘም’ ተብላ ቀረች። ይህ ልክ በእኔ የደረሰብኝ ዓይነት ነው፤” ይላሉ ኮ/ል ዳዊት ገብሩ በመጽሐፋቸው። “አባቴ በ1922 ዓ.ም. …ለትምህርት ወደ ጀርመን ሊልኩኝ ቢያስቡም፤ የትምህርት ሚኒስትሩ ሳህሌ ጸዳሉ ተመሳሳይ ዕግድ በማድረግ የትምህርት ዕድሌን አጨናግፈውብኛል። እኔ ብዙ ስላየሁ ቻልኩት እኅቴ ግን አልቻለችውም።” በማለት አጋጣሚውን በኀዘን ይገልፁታል።

ከዚህ በኋላ የወጣቷ፣ በሙዚቃ ብዙ የመግፋት ጉጉት የነበራት የየውብዳር ገብሩ የሕይወት መስመር ሌላ አቅጣጫ ያዘ። የዚህ ዕድል መሰናከል ምን እንዳስከተለ የእማሆይ ማስታወሻ እንዲህ ይገልፀዋል።“የመጨረሻ ዕድሌ በመሰበሩ፣ መንፈሴ ተሰባብሮ፣ ሞትን ብቻ ፈለግኹ። ከ15 ቀን በላይ እህል ውኃ ሳልቀምስ ጥቁር ባዶ ቡና ብቻ እየጠጣሁ ስሰነብት፤ ያው የሞት ጥላ በላዬ ላይ ሲያንዣብብ፣ የመጨረሻ ቁርባን እንዲሰጠኝ ጠይቄ አንድ ቄስ እስከነበርኩበት ምስካየ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም አጠገብ እነበረው ሆስፒታል ድረስ መጥተው አቆረቡኝ። የዚህ ዓለም ፍቅር እና የመኖር ፍላጎት ከኅሊናዬ  ፈጽሞ ተወገደ፤” ይላሉ።

በቤተሰቦቻቸው ርብርብ ሕይወታቸው ተርፎ ጥቂት የተጽናኑት እማሆይ፤ ቤተሰቦቻቸውን አዘናግተው ወደ ግሼን ደብረከርቤ ተጓዙ። “ለኹለት ዓመታት አንድ ቀን ሳይቋረጥብኝ ሰዓታቱንም፣ ቅዳሴውንም ሥራውንም ከዘለቅሁት በኋላ ስቆረጠልኝ። የኹለት ወር ፈቃድ እና ደመወዝ ይዤ ከአንድ ዓመት በፊት ከእናቴ ከወ/ሮ ካሣዬ ጋር ሔጄበት ወደነበረው ወደ ግሼን ማርያም ተጓዝኩ። ወደዚያ ስሔድ ግን ነፋስ መለወጥ አለብኝ ብዬ አባባን እና እናቴን አስፈቅጄ ነው። እነርሱ ምንም አልጠረጠሩም ነበረና ለሽርሽር የምሄድ መስሏቸው ፈቀዱልኝ።” ይላሉ። ከዚያም ለግሼኑ አቡነ ሚካኤል መመንኮስ እንደሚፈልጉ ይነግሯቸዋል። “ዘመዶችሽ በኋላ መጥተው ቢያስቸግሩስ?” ቢሏቸው፤ “በነፍሴ የሚያዝባት ሰው ካለ እኔ ሌላ የለም።” ስላሉዋቸው ምንኩስናው ተፈቀደላቸው። ከምንኩስናው በፊት በጸጉር የመላጨቱ ሥነ ሥርዓት ወቅት የተከሰተው ነገር እዚህ ላይ ሳይጠቀስ አይታለፍም። “ከእንክብካቤ እቅፍ ውስጥ ወጥቶ ተሞነጫጭሮ ትከሻዬ ላይ የተዘረገፈውን ፀጉሬን ዐይተው አቡነ ሚካኤል፤ ‘ይህ ጠጉር ደግሞ መላጨት አለበት፤ ’ አሉኝ። ቀጠል አድርጌ ኧረ እርሱስ ግድ የለም አልኳቸውና አባ ደሳለኝ የሚባሉትን የደሴ ግቢ መርቆርዮስ አስተዳዳሪ እንዲላጩኝ ጠየቅኳቸው። አባ ደሳለኝ ሲላጩኝ እጃቸው ለብዙ ጊዜ ሲያርፍ ‘ምን ኾነው ነው?’ ብዬ ዘወር ብዬ ሳያቸው፤ ዕንባ አውጥተው ሲያለቅሱ ዐየሁና ‘ምነው አባቴ ምን ኾኑ?’  ብላቸው፤ ‘አባቴ እንኳን ሲሞት አላለቀስኩም፣ እንዲያው አዝኜ ነው’ አሉኝ። እኔም ‘ምን ለፀጉሩ ነው ይህንን ያህል የሚያዝኑት’ ብዬ ቀለድኩባቸው። እንኳንስ ፀጉር ሌላም በነበረኝ ለጌታዬ የምሰጠው አልኳቸው።” ይላሉ። በዚህ ዕለት ማግስት የምንኩስና ሥርዓቱ ተፈጸመላቸው። ይህ ሲኾን ዕድሜያቸው 20ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነበር።

በወጣትነታቸው በወሰኑት በዚህ የምንኩስና ሕይወት አባትታቸው እና እናታቸው ከፍተኛ ኀዘን ላይ ወደቁ። ብዙም አልቆዩ፤ እማሆይ በመነኮሱ በኹለት ዓመታቸው አባታቸው ከንቲባ ገብሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ከዚያ በኋላ እማሆይ ሙሉ ጊዜያቸውን ለሙዚቃ ቅማሬ እና ለመንፈሳዊው ግልጋሎት ብቻ ወሰኑ። የመጀመሪያ ቅማሬያቸውን ለማስቀረጽ ወሰኑ። የዚህ ሙዚቃ የማስቀረጹ ውሳኔ፤ የራሱ የኾነ ምክንያት ነበረው። “ቅማሬዬን በሸክላ ለማስቀረጽ ያነሳሳኝ ዐቢይ ምክንያት ነበር። ጎንደር በነበርኩበት ጊዜ በየቤተክርስቲያኑ የማይጠገበውን ማኅሌት ሰምቼ ስመለስ፤ እደጅ የአገር ቤት ተማሪዎች በየሜዳው ጥቅልል ብለው ተኝተው አያለሁ። ብጠይቅ ሌሊት ቤተክስቲያን ያደሩ ናቸው፣ ጥግና ቤት የሌላቸው። በዚህም ልቤ ተነካ፣ አዘንኩ። እኔ ሀብት የለኝ፤ ያለችኝ ያቺው ሙዚቃዬ። ስለዚህ አስኪ ሙዚቃዬን ላስቀርጽ እና ሽያጩን እነዚህ ልጆች ገብተው በነጻ የሚያድሩበት ቤት ላቋቁም አልኩ። መከረኞቹም አሉ ሸክላውም ተቀረጸ። ነገር ግን ተንኮለኛ አይጠፋምና ለሽያጭ ከመቅረቡ በፊት እንጉሡ ጆሮ ስለ ደረሰ ሐሳቡ መና ቀረ መሞከሬ ግን አልቀረም።”

ይህንን በመሰለ “እርሳቸው ያልተረጋጋ” በሚሉት ሕይወት እስከ 1975 ዓ.ም. ከቆዩ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ሔዱ። እማሆይ በደብረ ገነት ኪዳነ ምሕረት ከሦስት ዐሥርት ዓመታት በላይ ኖረዋል። ላለፉት ሦስት ዐሥርት ዓመታት ስላሉበት ኹኔታ ምንም ዓይነት ዐዲስ ዜና ተሰምቶ ስለማይታወቅ በሕይወት መኖራቸውን የተጠራጠሩ ብዙዎች ነበሩ። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን፣ ሥራዎቻቸው የታላቅ ሙዚቀኞችን ቀልብ መሳብ ጀመረ። በወጣትነታቸው ብዙ መሥዋዕትነት የከፈሉለት፣ ማንም ልብ ሳይለው የዘሩት የረቂቅ ሙዚቃ የቅማሬ ዘር፤ ዛሬ ላይ ብዙዎች እርሳቸውን ብለው፣ የእርሳቸውን ሙዚቃ እንዲያጠኑ እያደረገ ነው።

የዓለም ታላላቅ የዜና አውታሮችም ከ2013 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ.) ጀምሮ ስለ እማሆይ ሙዚቃዎች አዳዲስ ነገሮችን ማቅረብ ጀምረዋል። በ2013ቱ የኢየሩሳሌም የባህል ክብረ በዓል ከተከናወኑ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ በእማሆይ ሕይወት ታሪክ እና የሙዚቃ ሥራዎች ዙሪያ ያተኮሩ ተግባራት ነበሩ። ባለኹለት ጥራዝ መጻሕፍትን በእማሆይ የሕይወት እና የሙዚቃ ሥራዎች ላይ መታተም ችለዋል። የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን በኖታ የያዘ ባለ 146 ገጽ መጽሐፍም ታትሟል። እንደ ናዳቭ ሀርፐር ያሉ የእስራኤል ታላላቅ ሙዚቀኞች ስለ እማሆይ ሥራዎች ጥልቀት ምስክርነት እየተሰጡ ይገኛሉ።

በወጣትነት ዕድሜ የተሠራ የአስተውሎት ሥራ የኋላ ኋላ የራሱ ትንሣኤ ይኖረዋል። የእማሆይ ጽጌ ማርያም ሕይወት በሙዚቃ በብዙ ተፈትነዋል። ከመንፈሳዊ ሕይታቸው ጋር የሚቃረን የሚመስላቸው አንዳንዶች፣ ሙያቸውን እና የሙዚቃ ፍቅራቸውን አጣጥለውባቸዋል። የሕይወታቸውን አቅጣጫ ፍጹም በማይገመት መንገድ እንዲጓዝ ያደረገም ነው። ከሀገራቸው አሰድዶ በሌላ በዓት ተነጥለው እንዲኖሩ ያደረገ ነው። ግን ከዚህ ኹሉ በኋላ የስማቸውን ትንሣኤ ዕድለኛ ኾነው፣ ከዘጠኝ ዐሥርት ዓመታት በኋላ በታላቅ ክብር ከብዙዎች ብድራቱን አግኝተውበታል። በቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቴአትር ቤት ከንጉሠ ነገሥቱ ብቻ በቀር ማንም በትዕግሥት ሊያዳምጠው ያልቻለው ኮንሠርታቸው፤ ሐምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ሥራዎቻቸውን በሚጫወቱ ወጣቶች አማካኝነት ከ1800 በላይታዳሚያን በተገኙበት በአድናቆት ተመልካች አግኝቷል። ገና ያልተደመጡት አዳዲሶቹ ስድስት ክላሲካል ቅማሬዎቻቸው በትልቅ ኦርኬስትራ ሊቀርቡ ዝግጅት እየተደረገ ነው።

(ይህ ጽሑፍ፤ በዐዲስ ነገር ጋዜጣ ላይ የጻፍኩት ጽሑፍ ነበር፣ ለክብርት እናታችን፣ ለታላቂቱ የረቂቅ ሙዚቃ ጥበበኛ ለእማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ፣ ለኅልፈታቸው መታሰቢያ በድጋሚ አቀረብኩት።)

credit – Addis Tibeb

archive
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

ኦሮሚያ ክልል ለጤና ጣቢያዎች አንድ ሺህ ሃኪሞችን ለመቅጠር ማስታወቂያ ቢያወጣም ተመዝጋቢ ጠፋ
እጅግ ግዙፍ የበረዶ ግግር ተገምሶ ስፍራውን በመልቀቅ የሚያደርገው እንቅስቃሴ አስግቷል
Related posts
  • Related posts
  • More from author
Events

የመደመር መንግሥት አዕማዶች – የመጽሐፍ ዳሰሳ

October 8, 20250
ማህደር

የሦስት ሊቃውንት የአሻራ ቅብብሎሽ

October 5, 20250
ማህደር

“ኦሮሞ ‘ፈጣሪ ጥቁር ነው’ ይላል” የዋቄፈና እምነት

October 4, 20250
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 20260
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 20260
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 20260
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news