Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  POLITICS  “ይዋል ይደር እንጂ የሶማሊላንድን ተልዕኮ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ሕብረት በአዲስ አበባ እምብርት ላይ ታያላችሁ” ሶማሊላንድ
POLITICS

“ይዋል ይደር እንጂ የሶማሊላንድን ተልዕኮ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ሕብረት በአዲስ አበባ እምብርት ላይ ታያላችሁ” ሶማሊላንድ

Ethioreview newsEthioreview news—October 20, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ራስ ገዝ የሆነችውና የሶማሊያ ሪፐብሊክ መንግስት የራሴ አካል የሚላት ሶማሊላንድ ኢትዮጵያ ውስጥ ላላት የዲፕሎማቲክ ተልእኮ መገንቢያ የሚሆን ቦታ ከኢትዮጵያ መንግሥት መረከቧን ዐሳወቀች ። የመሠረት ድንጋይ መቀመጡ እውነት መሆኑን በአፍሪቃ ሕብረት እና ኢጋድ የሶማሊላንድ ልዩ መልእክተኛ የሆኑት አምባሳደር አብዱላሂ ሙሐሙድ ለዶቼ ቬለ አረጋግጠዋል።

ራስ ገዝ የሆነችውና የሶማሊያ ሪፐብሊክ መንግስት የራሴ አካል የሚላት ሶማሊላንድ ኢትዮጵያ ውስጥ ላላት የዲፕሎማቲክ ተልእኮ መገንቢያ የሚሆን ቦታ ከኢትዮጵያ መንግሥት መረከቧን ዐስታወቀች ። የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኢሳ ካይድ «ወደፊት አዲስ አበባ ውስጥ ለሚኖረው የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ኤምባሲ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል» ሲል የራስ ገዟ ሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በቀድሞው ትዊተር በ X ገጹ አስፍሯል ። 

የመሠረት ድንጋይ መቀመጡ እውነት መሆኑን በአፍሪቃ ሕብረት እና ኢጋድ የሶማሊላንድ ልዩ መልእክተኛ የሆኑት አምባሳደር አብዱላሂ ሙሐሙድ ለዶቼ ቬለ አረጋግጠዋል። የሶማሊላንድ ባለስልጣናት የመሰረት ድንጋዩን ሲያስቀምጡ የሚያሳይ ምስል የተለቀቀ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማረጋገጫ ለመጠየቅ ያደረግነው ጥረት ለጊዜው ምላሽ አላገኘም ።

ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ መንግሥት ለተልእኮዋ የሚሆን መሬት መረከቧን ግለፀች

ሶማሊያ ሊፋቅ በማይችል ሁኔታ የሉዓላዊ ግዛቴ አንድ አካል ናት የምትላት ሶማሊላንድ በፊናዋ ራስ ገዝ መሆኗን ነው የምታምነው። ይህንን መሠረት አድርጋ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችው የባህር በር ማስገኛ የመግባቢያ ስምምነት የኢትዮጵያ እና የሶማሊያን ግንኙነት በእጅጉ አሻክሯል፣  በቀጣናውም አዳዲስ ጥምረቶችን እየፈጠረ ይገኛል።

More stories

ደቡብ ሱዳን ስድስተኛ ሀገር ሆና የናይል ስምምነት ማዕቀፍን አጸደቀች

July 12, 2024

“ትህነግ ጦሩን እስጠግቷል፤ የጦርነት ስጋት አለብን” የጠለምት ወሰንና ማንነት አስመላሽ

June 7, 2025

“የኢትዮጵያን ህልውና የሚበይኑት የተፈጥሮ ሀብቶች…”

September 2, 2024

“ዘመን ትውልድን ይገነባል ፤ ትውልድም ዘመንን ይገነባል”

September 10, 2023

ከየትኛውም ሀገር እውቅና ያላገኘችው ሶማሊላንድ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖራት ወይም ላላት ተልእኮ መቀመጫ የሚሆን ግንባታ ማከናወኛ መሬት በኢትዮጵያ መንግስት በልግስና  እንደተበረከተላት ትናንት አስታውቃለች። ይህም በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ትልቅ እመርታ አለው በሚል ተገልጿል። በአፍሪቃ ኅብረት እና ኢጋድ የሶማሊላንድ ልዩ መልእክተኛ የሆኑት አምባሳደር አብዱላሂ ሞሐመድ ይህ እውነት መሆኑን ዛሬ ከዶቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አረጋግጠዋል። ምንም እንኳን ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል በዚህ ዙሪያ እስካሁን ምንም የተባለ ነገር ባይኖርም።

“ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሉት ሌሎች ተልእኮዎች መሬቱን አግኝተናል። በኢትዮጵያ የሶማሊላንድን ተልእኮ የምናከናውንበት መሬት ተሰጥቶናል። እዚህ ቀድሞውኑም ጥሩ ተልእኮ አለን። ብዙ ሰራተኞችም አሉን። ኢትዮጵያም በሀርጌሳ ጥሩ የሚባል ትልቅ ትልእኮ አላት”።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ባለፈው ጥር የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ለሁሉም የቀጣናው ሀገራት በደህንነት፣ በልማት፣ በአካባቢያዊ ውህደት እና ቀጣናውን በማሳደግ ረገድ ትልቅ ዕድል ነው ያሉት የሥራ ኃላፊው፣ ሆኖም ግብጽ ወደ አካባቢቢው ዘልቃ በመግባት  እያደረገችው ያለው እንቅስቃሴ ለቀጣናው የፖለቲካ እና የፀጥታ ሁኔታ ትልቅ አደጋ እና ሥጋት የሚጋርጥ ነው ብለዋል።

“የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንሳ ኬይስ እና እኔ –  የሶማሌላንድ የአፍሪካ ሕብረት እና የኢጋፍ ልዩ መልዕክተኛ እንደመሆኔ፣ በኢትዮጵያ ተልዕኮአችንን በምንገነባበት መሬት ላይ የመጀመሪያውን ድንጋይ አስቀምጠናል። በእርግጥም አዲስ አበባ የአፍሪካ ሕብረት ልብ እና ማዕከል እንደመሆኗ ለአፍሪካ ሕብረት ጭምር ነው። ስለዚህ እኛን በሚመለከት ለዚሁ ሥራ ሀብት እና በጀት በቅርቡ እንመድባለን። በመሆኑም ይዋል ይደር እንጂ የሶማሊላንድን ተልእኮ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ሕብረት በአዲስ አበባ እምብርት ላይ ታያላችሁ። ይህንን ቦታ ያዘጋጁትን የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናትን እና የአካባቢ መስተዳድር ኃላፊዎችን እናመሰግናለን”።

ይህ ማለት ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ እውቅና አገኘች ማለት ነውን?

ስለዚህ ይህ ማለት ሶማሊላንድ በኢትዮጵያ መንግስት በይፋ ዕውቅና አግኝታለች ማለት ነው? በሚል ላቀረብንላቸው ጥያቄ ሲመልሱ  “እንደዚያ አላልኩም። ሶማሊላንድ እስካሁን በኢትዮጵያ ዕውቅና አልተሰጣትም። ነገር ግን እንደሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የሶማሊላንድን እውቅና እንጠብቃለን። እና ደግሞ የመግባቢያ ስምምነቱ አካል የባህር በር ፣ እውቅና ማግኘት ነው። እና በእነዚህ ጉዳዮች ላይ እየሰራን ነው የምንገኘው”።

አምባሳደር አብዲላሂ በአካባቢው በግብጽ የሚመራ ጥምረት እየተፈጠረ መሆኑን ጠቅሰው “ግብጽ በድንገት የሶማሊያ ወዳጅ የሆነችበት እና ዘልቃ የገባችበት ምክንያት ምንድን ነው”? የሚለው የሁሉም ጥያቄ ነው ብለዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው ምላሽ አላገኘም። ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር የገባችበት ብርቱ ውዝግብ በሰላም እንዲፈታ ግፊት የምታደርገው ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ እና “ድንበር ዘልሎ የሚመጣ ትርምስ” ስለማትፈልግ መሆኑን የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሁኑ ርእሠ ብሔር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በቅርቡ አስታውቀው ነበር።

ኢትዮጵያ ሶማሊላንድ – ሀርጌሳ ውስጥ በልዩ መልዕክተኛ ደረጃ ለነበረው ቆንስላ ጽሕፈት ቤቷ አምባሳደር ተሾመ ሹንዴን ከወራት በፊት መሾሟ ይታወሳል።

ዘገባው የዲደብሊው ነው

POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
60 ሰርጎ ገብ የአልሻባብ የሽብር ቡድን አባላት ላይ እስከ ዕድሜ ልክ ውሳኔ የተላለፈባቸው
የእስራኤል ወደ ሶማሊላንድ መንደርደር ለኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ሩጫ ታላቅ ብስራት፣ ዩኤኢ አደራዳሪ ናት
Related posts
  • Related posts
  • More from author
POLITICS

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

March 28, 2026
POLITICS

አስቸኳይ የአርበኛነት ጥሪ ለኢትዮጵያን

March 4, 2026
POLITICS

ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡ

January 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2