Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  POLITICS  “የአፍሪካን ስርዓተ ምግብ ከቅኝ ግዛት እሳቤዎች ነፃ ማውጣት ይገባል”
POLITICS

“የአፍሪካን ስርዓተ ምግብ ከቅኝ ግዛት እሳቤዎች ነፃ ማውጣት ይገባል”

Ethioreview newsEthioreview news—July 28, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

አንዳንድ ሚዲያዎች “ኢትዮጵያ ይህን ጉባኤ እንዴት እንዳዘጋጀቸው ባይታወቅም” በማለት እየተብሰለሰሉ ሽፋን ሰጥተውታል። ከጉባኤው ጀርባ አገርና ሕዝብ የሚጎዳ አጀንዳ ያለው ለማስመሰል እየዳዳቸው እንግዶቹ ከአለባበስ ጀምሮ መሳቂያ አድርገዋቸዋል። ይህ ታላቅ ስብሰባ እንዲዘጋጅ ኢትዮጵያ ተነሳሽነቱን ስትወስድ በአፍሪካ “የምግብ ሉዓላዊነት” አጀንዳ ለመትከልና አጀንዳውን በማሳካት ልክ እንደ አደዋ ዓይነት ታሪክ ለመጻፍ መነሳቷ የገባቸው “የአፍሪካን ስርዓተ ምግብ ከቅኝ ግዛት እሳቤዎች ነፃ ማውጣት ይገባል” በሚል አሳቡን ወርቅ ሲቀቡት ታዝበናል።

ሁለተኛውን የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባዔ  ከእሁድ ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። ያዘጋጁት ደግሞ ኢትዮጵያ እና ጣሊያን በጋራ ሲሆን፣ ከአራት ዓመታት በፊት በመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ ቢሮ በኩል ተዘጋጅቶ ዕውቅና የተሰጠው ታላቅ ጉባኤ ነው። ይህ ጉባኤ የዛሬ ሁለት ዓመት የመጀመሪያው የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤ (UNFSS+2) በሮም ጣሊያን በዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት መካሄዱ የሚታወስ ነው።

በወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የ FAO አግሪኮላ ሜዳልያ መሸለማሸው የሚታወስ ነው። ሽልማቱን ያገኙት በጥር 28 ቀን 2024 ዓ.ም ነበር። ሽልማቱን የ FAO ዋና ዳይሬክተር QU Dongyu ነበር ያበረከቱላቸው። ሜዳልያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በኢትዮጵያ በገጠርና ኢኮኖሚ ልማት በተለይም በምግብ ዋስትና እና በስነ-ምግብ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋፅኦ እና በስንዴ እራስን መቻል ላሳዩት የሚጨበጥ ስራቸው እንደነበር በወቅቱ መገለጹ የሚታወስ ነው።

ዋና ዳይሬክተሩ ሽልማቱን ሲያበረክቱ እንዳሉት ሜዳሊያው የተሰጠው ለኢትዮጵያና አፍሪካ እንጂ ለተቅላይ ሚኒስትር አብይ ብቻ እንዳልሆነ ገልጸዋል። ይህን ሽልማት ሲሰጡ የተሰማቸው ደስታና ክብርም ትልቅ መሆኑ አስታውቀው ነበር። ይህን ሽልማት ተክትሎ “ተፈናቃይ አለ፤ ተረጂ አለ። ረሃብተኛ አለ” ወዘተ በማለት በሌላ ወገን ያሉ ለማናናቅ ሞክረው እንደነበር ይታወሳል።

More stories

ደቡብ ሱዳን ስድስተኛ ሀገር ሆና የናይል ስምምነት ማዕቀፍን አጸደቀች

July 12, 2024

“ትህነግ ጦሩን እስጠግቷል፤ የጦርነት ስጋት አለብን” የጠለምት ወሰንና ማንነት አስመላሽ

June 7, 2025

“የኢትዮጵያን ህልውና የሚበይኑት የተፈጥሮ ሀብቶች…”

September 2, 2024

“ዘመን ትውልድን ይገነባል ፤ ትውልድም ዘመንን ይገነባል”

September 10, 2023

“ድሃ ይሁን ሀብታም፤ ልጅ ይሁን አዋቂ በዚህ ዓለም ሁሉም ሰው ምግብ ማግኘት አለበት። ደኅንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ ሕይወት ብቻ ሳይሆን ጤና እና ተስፋም ነው” በሚል ጥልቅ እሳቤ እየተካሄደ ያለው ጉባኤ አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት አብይ አህመድ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስ ከምግብ ሥርዓት ጋር እንዲጣጣም ጥሪ ሲያቀርቡ ተሰምተዋል።

በዋረንጓዴ ሌጋሲ መርህ ከቀናት በሁዋላ ስልሳ ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ቀን ለመትከል ዝግጅቷን ያጠናቀቀችው ኢትዮጵያ ከጣሊያን ጋር በትብብር ባዘጋጀችው በ2ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባኤ መክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ለልማት የሚደረጉ ድጋፎች በመቀዛቀዛቸው ምክንያት አፍሪካ ጫና ውስጥ እንደምትገኝ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነቶች ፈተና እንደገጠማቸውም ገልፀዋል፡፡ አክለውም አፍሪካ በግብርና፣ የገጠር ልማት፣ መሠረተ ልማት እና ቢዝነስ ላይ ኢንቨስት እንድታደርግ ተገማች ፋይናንስ ያስፈልጋታል ብለዋል፡፡

“ከእኛ አውድ ጋር የሚስማሙ ከአየር ንብረት ጋር የተዛመኑ መሳሪያዎች፣ ባዮቴክኖሎጂ እና የዲጂታል ግብርና ያስፈልጉናል። ቴክኖሎጂዎች ተመጣጣኝ እና የጋራ ሊሆኑ እንጂ ሊደበቁ አይገባም” ሲሉ አጽዕኖት ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ እና በጣሊያን ትብብር የሚካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ቀጣይነት ያለው፣ አካታች እና የማይበገር የምግብ ስርዓት ግንባታ ላይ አተኩሮ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ድረስ ይካሄዳል፡፡

በዚሁ ጉባኤ ላይ “የአፍሪካን ስርዓተ ምግብ ከቅኝ ግዛት እሳቤዎች ነፃ ማውጣት ይገባል” ሲሉ የሳህል ድርቅ ቁጥጥር የሀገራት ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ሲልቫን ናፊባ ኦውድራጎ፤ በአሕጉሪቱ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በግብርናው ዘርፍ ያሉ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን በአግባቡ መመርመር አንደሚገባ፤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ካለው የተመድ የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

“ያለ አገር በቀል ዕውቀት የምግብ ስርዓታችንን ማሻሻል አንችልም። ምክንያቱም ከዘመናዊ ግብርና በፊት ለዘመናት ይህ ዕውቀት መሬት ላይ ነበር። ይህን አገር በቀል ዕውቀት በትክክል ልናጠናው እና እንዴት ልናስተዋውቀው እንዲሁም በሳይንስ ደረጃ ልናስቀምጠው እንደምንችል መፍትሔ ልናበጅ ይገባል” ብለዋል።

በተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓቶች ጉባኤ ላይ የተገኙ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች የአረንጓዴ ዐሻራችውን አኖሩ

ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ የመክፈቻ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ መካሔድ ጀምሯል።

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሀፊ አሚና መሀመድ ለመገናኛ ብዙሀን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በዘመናችን ካሉት እጅግ አንገብጋቢ ፈተናዎች አንዱ የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም አለም አቀፍ ቁርጠኝነት ማሳያ ነው።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ዓለማችን ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ከአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም ጂኦፖለቲካዊ ግጭቶች እና የኢኮኖሚ ተለዋዋጭነት እየገጠማት መሆኑን ገልጸዋል

እነዚህ ተግዳሮቶች የምግብ ስርዓት የሚፈለገውን ያህል የመቋቋም አቅም እንደሌለው ማረጋገጣቸውን ገልጸው፤ የጋራ ጥረትን በእጥፍ ለማሳደግ ይህ ጉባኤ ወሳኝ ነው ብለዋል።

በመስክ ጉብኝቱ ላይ የተሳተፉ ልዑካን በምግብ ስርዓት ለውጥ ግንባር ቀደም ካሉት ሰዎች በመሬት ላይ ያለውን ፈጠራ እና ተግዳሮቶች በዓይናቸው ማየት መቻላቸውን አንስተዋል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከፍተኛ እመርታ እያሳዩ ያሉ ሀገራት የ2030 የዘላቂ ልማት ግቦች ላይ ለመድረስ ጥረታችንን ማፋጠን አለብን ብለዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሀፊ አሚና መሀመድ እንደገለጹት፤በርካታ ሀገራት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተለያዩ እርምጃዎች እየወሰዱ ናቸው።

እንዲሁም መንግስታት በዚህ ላይ ፖሊሲና ስትራቴጂ ቀርጸው እየተገበሩ መሆናቸው በሪፖርት መመላከቱን ጠቁመዋል።
ትናንት ባደረጉት ጉብኝት ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እያከናወነቻቸው ያሉ ስራዎች አስደናቂ መሆናቸውን ለመመልከት መቻላቸውን አንስተዋል። የአመራሩን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሰዋል። ባለብዙ ወገን ግንኙነትን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፥ይህም አለም አቀፋዊ ቀውሶች ሲያጋጥሙ መውጫ መንገድ መሆኑን አብራርተዋል።


POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
The Nile cannot be governed by colonial-era treaties
ሀገራት በምግብ ራስን ለመቻል ለአየር ንብረት ተስማሚ የምግብ ፖሊሲ ሊተገብሩ ይገባል – የተመድ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
POLITICS

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

March 28, 2026
POLITICS

አስቸኳይ የአርበኛነት ጥሪ ለኢትዮጵያን

March 4, 2026
POLITICS

ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡ

January 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2