የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት፣ በአእገራዊ የምክክር ሂደት ላይ የተለያዩ ችግሮች እንደከኖች መፈጠራቸውን አመልክቷል። ኮሚሽኑ ከዘረዝስራቸው እንከኖች መካከል፣አገራዊ ውይይቶች ሲካሄዱ በተሳተፉ ዜጎች ላይ የገጠመውን ይፋ አድርገዋል።
በሪፖርቱ እንደተመለከተው ከሆነ በብዙ ክልሎች የተካሄዱ ውይይቶች ላይ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን በነጻነት ሲገልጹ ፣ ፈቃድ ሳይጠይቁ ምስል እና ቪዲዮ መቀረጻቸው ለደህንነታቸው ስጋት መሆኑን አመልክቷል። ሳያስፈቅዱ የሚቀርጹትን “ሚዲያ ነን ባዮች” ያለው ሪፖርቱ ችግሩ በበርካቶች ላይ ስጋት መፈጠሩን አመልክቷል።
በተለይም በአማራ ክልል አንዳንድ ተሳታፊዎች፣ የታጣቂ ኃይሎች [ፋኖ] በምክክሩ መሳተፋቸውን በመገናኛ ብዙኃን ካዩዋቸው ሊያጠቋቸው እንደሚችሉ በመፍራት ፊታቸውን በመሸፈን ሃሳባቸውን ሲሰጡ፣ በጣም የሰጉ ደግሞ ሀሳባቸውን ከመግለጽ መቆጠባቸውን ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል።
ኢሰመኮ በሪፖርቱ እንደጠቆመዉ አንዳንድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የኮሚሽኑን ገለልተኝነት በመጠራጠር ከሂደቱ ራሳቸውን አግልለዋል። በተጨማሪም፣ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ውስጥ በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ከሚገኙ አካባቢዎች ተሳታፊዎችን ማካተት ባለመቻሉ፣ የምክክር ሂደቱ ሁሉን አካባቢዎች እንዳያዳርስ እንቅፋት ሆኗል።
ከ 7.8 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባወጣው የ2017 ዓ.ም. ሪፖርት መሰረት፣ በመላ ሀገሪቱ ከ7.8 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል። በተጨማሪም፣ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስተጓጎል የምግብ ዋስትና እና የጤና ችግሮችን እያባባሰ መሆኑን ይፋ አድርጓል።
በተለይ በአማራ ክልል ውስጥ ባለው ግጭት ምክንያት ከ3,700 በላይ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ የመምህራን ደመወዝ በወቅቱና በአግባቡ አለመከፈል እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች መዘጋት ችግሩን አባብሰውታል።
የሰብአዊ ድጋፎችን የሚያቀርቡ ድርጅቶች አገልግሎት መቋረጥ በተፈናቃዮች እና ድጋፍ በሚሹ ማኅበረሰቦች ላይ የምግብ ዋስትና እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዲከሰት አድርጓል። ይህ ሁኔታ በተለይም ከ5 ዓመት በታች በሆኑ ሕፃናት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ መሆኑ በሪፖርቱ ተገልጿል።
በተጨማሪም፣ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የወባ፣ ኮሌራ እና ኩፍኝ በሽታዎች በስፋት ተከስተዋል ያለዉ ኢሰመኮ ከጥር እስከ ሚያዝያ 2017 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ 1,978,505 የወባ፣ 4,056 የኮሌራ እና 3,908 የኩፍኝ ክስተቶች የተመዘገቡ ሲሆን፣ በእነዚህ በሽታዎች በድምሩ 141 ሰዎች ሞተዋል።
በግጭቶች ምክንያት የጤና ተቋማት አገልግሎት ማቆማቸው እና የመድኃኒትና የሕክምና ቁሳቁሶች እጥረት የጤና መብት ሁኔታ እንዲባባስ ማድረጉን የተቋሙ ዓመታዊ ሪፖርት አመልክቷል።
በአዲስ አበባ ብቻ 73 ሺህ ኤርትራዊያን የከተማ ስደተኞች አሉ፤ መረጃው ያልተመዘገቡትን አያካትትም
በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ80 ሺህ በላይ የከተማ ስደተኞች እንደሚገኙ፣ ከነዚህ ውስጥም 73 ሺህ የሚሆኑት ኤርትራውያን እንደህኑ ኢሰመኮ አስታወቀ።
73 ሺህ ከኤርትራ፣ ከ2 ሺህ 4መቶ በላይ ከየመን፣ ከሶማሊያ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ከሶሪያ፣ ከኮንጎ እና ከሌሎች ሀገራት ተሰደው የመጡ መሆናቸዉን በሪፓሪቱ አመላክቷል።
ኮሚሽኑ ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ስደተኞችን በተለይም በሱዳን የሚካሄደውን ግጭት ሸሽተው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ስደተኞችን መቀበል እና ማስተናገዱን የቀጠለ መሆኑ በበጀት አመቱ ከታዩ ለውጦች መካከል ይጠቀሳሉ ብሏል።
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ስደተኞች የብሔራዊ መታወቂያ፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶችን የሚያገኙበት ሁኔታ መመቻቸቱንም አስታዉቋል።
ስደተኞች በተለያዩ ሥራዎች ላይ በመሰማራት ራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን በኢኮኖሚ የሚደግፉበት ሁኔታ እና የስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የሥራ መብት የሚደነግግ መመሪያ መጽደቁም ተገልጿል።
እነዚህ በከተማ የሚገኙ ስደተኞች በመንግሥት ዕቅድ ከመጠለያ ጣቢያ ውጭ እንዲኖሩ የተፈቀደላቸው በሚል ተለይተው የሚታወቁ ናቸው።
ምዝገባ ያልተደረገላቸው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጥገኝነት ጠያቂዎች በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚገኙም ተገልጿል።
ኢሰመኮ በጋምቤላ ክልል ስደተኞች የጸጥታ እና ደኅንነት ሥጋት እንዳለባቸው ገለፀ።
በጋምቤላ ክልል ከ395,000 በላይ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች በ7 የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ተገልፆል።
ኢሰመኮ በጋምቤላ ክልል የሚገኙ ስደተኞችን በሚመለከት የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ውትወታን ሲያከናውን ቆይቷል።
ለስደተኞች የሚቀርበው መሠረታዊ ድጋፍ በመጠንም ሆነ በዓይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ በመቀነሱ በስደተኞች የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል።
ኮምሽኑ ኦኩጉ የስደተኞች መጠለያ ይገኙ የነበሩ ደቡብ ሱዳናዊያን የሙርሌ ጎሳ ስደተኞችን በሚመለከት ከየካቲት 8 እስከ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ክትትል ማከናወኑን ተገልፃል።
በተደጋጋሚ ጥቃት እና ዘረፋ በማጋጠሙ ፤ምግብ፣ መጠለያ፣ ጤና እና ትምህርትን የመሳሰሉ አገልግሎቶች አቅርቦትም በበቂ ሁኔታ ባለመኖሩ ችግር ዉስጥ መሆናቸዉን በሪፓሪቱ አመላክቶል።
ኢሰመኮ በጉዳዩ ላይ ከስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት እንዲሁም ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጋር ምክክሮችን መደረጉ የተገለፀ ሲሆን፤
የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ስደተኞቹን ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ኛንጋቶም ወረዳ አይፓ ሳይት እንዲዘዋወሩ መደረጉን ኮምሽ ባወጣው ሪፓርት አመላክቷል፡፡
ለዚህም እንደምክንያት የተነሳዉ ለስልጠና የሚውል በጀት አለመኖሩንና በተጨማሪም ለስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት በቂ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑ ፍትሕ የማግኘት መብታቸውን በማረጋገጥ ረገድ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሰደሩ መሆኑ ተገልፆል።

